2 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11
11
ጳውሎስና ሐሰተኞች ሐዋርያት
1ጥቂቱን ሞኝነቴን እንደምትታገሡኝ ተስፋ አደርጋለሁ፤ እባካችሁ ታገሡኝ። 2እንደ አንዲት ንጽሕት ልጃገረድ በድንግልናዋ ለአንድ ባል እንደምትታጭ እኔም እናንተን ለክርስቶስ ስላአጨኋችሁ ስለ እናንተ መንፈሳዊ ቅናት እቀናለሁ። 3እባብ ሔዋንን በተንኰሉ እንዳሳታት ምናልባት የእናንተም ሐሳብ ተበላሽቶ ለክርስቶስ ያላችሁን ቅንና ንጹሕ የሆነ ታማኝነት ትተዋላችሁ ብዬ እፈራለሁ። #ዘፍ. 3፥1-5፤13። 4አንድ ሰው ወደ እናንተ መጥቶ እኛ የሰበክነውን ሳይሆን ሌላ ኢየሱስ ቢሰብክላችሁ ወይም እናንተ የተቀበላችሁትን መንፈስ ሳይሆን ሌላ መንፈስ ብትቀበሉ፥ ወይም የተቀበላችሁትን ወንጌል ሳይሆን ሌላ ወንጌል ብትቀበሉ፥ ዝም ብላችሁ ተሸነፋችሁ ማለት ነው።
5ነገር ግን እኔ ከነዚህ ታላላቅ ሐዋርያት በምንም ነገር የማንስ አይመስለኝም። 6በአነጋገር ፈሊጥ ምሁር ባልሆንም እንኳ ዕውቀት አይጐድለኝም፤ ይህንንም ብዙ ጊዜ በብዙ መንገድ በግልጥ አስረድተናችኋል።
7እኔ የእግዚአብሔርን ወንጌል ያለ ደመወዝ ለእናንተ መስበኬና እናንተን ከፍ ለማድረግ ራሴን ማዋረዴ ምናልባት እንደ ኃጢአት ተቈጥሮብኝ ይሆን? 8እናንተን ለማገልገል ከሌሎች አብያተ ክርስቲያን ርዳታ በመቀበሌ እነርሱን ዘርፌአቸዋለሁ። 9ከእናንተ ጋር ሳለሁ ችግር በደረሰብኝ ጊዜ ከመቄዶንያ የመጡ ወንድሞች በሚያስፈልገኝ ነገር ሁሉ ይረዱኝ ስለ ነበር በማንም ሸክም አልሆንኩም፤ እስከ አሁን በእናንተ ላይ በምንም ነገር ሸክም አልሆንኩም፤ ለወደፊትም ሸክም አልሆንባችሁም። #ፊል. 4፥15-18። 10የክርስቶስ እውነት በእኔ ውስጥ በመኖሩ እንዳልመካ የሚያደርገኝ በአካይያ አገሮች ማንም የለም። 11ምክንያቱስ ምንድን ነው? ስለማልወዳችሁ ነውን? እንደምወዳችሁስ እግዚአብሔር ያውቃል።
12እነዚያ ሌሎች ሐዋርያት “እኛም እንደ እነርሱ እንሠራለን” እያሉ የሚመኩበትን ምክንያት ለማሳጣት አሁን የማደርገውን ወደፊትም ደግሞ አደርጋለሁ። 13እንደእነዚህ ያሉ ሰዎች የክርስቶስን ሐዋርያት ለመምሰል ራሳቸውን የሚለውጡ ሐሰተኞች ሐዋርያትና አታላዮች ሠራተኞች ናቸው። 14ይህም የሚያስደንቅ ነገር አይደለም፤ ሰይጣን እንኳ የብርሃን መልአክ ለመምሰል ራሱን ይለውጣል። 15ስለዚህ እነዚህ የሰይጣን አገልጋዮች የጽድቅ አገልጋዮችን ለመምሰል ራሳቸውን ቢለውጡ አያስደንቅም፤ በመጨረሻ የሥራቸውን ዋጋ ያገኛሉ።
ጳውሎስ በሐዋርያነቱ ምክንያት የደረሰበት መከራ
16“ማንም ሰው እኔ ሞኝ የሆንኩ አይምሰለው” ብዬ እንደገና እናገራለሁ። ሞኝ ብመስላችሁም እንኳ ጥቂት እንድመካ እንደ ሞኝ አድርጋችሁ ቊጠሩኝ። 17እንደዚሁ በትምክሕት ስናገር የምናገረው እንደ ጌታ ፈቃድ ሳይሆን እንደ ሞኝ ሆኜ ነው። 18ብዙዎች በሥጋዊ ነገር ስለሚመኩ እኔም እመካለሁ። 19እናንተ አስተዋዮች እንደ መሆናችሁ መጠን ሞኞችን በደስታ ትታገሣላችሁ። 20እንዲሁም ማንም እንደ ባሪያ ቢያደርጋችሁ፥ ማንም ቢበዘብዛችሁ፥ ማንም ቢጠቀምባችሁ፥ ማንም ቢንቃችሁ፥ ማንም ፊታችሁን በጥፊ ቢመታችሁ ትታገሣላችሁ። 21የሚያሳፍረኝ ቢሆንም እንኳ እነዚህን ነገሮች ለማድረግ ብርቱዎች አለመሆናችንን እገልጥላችኋለሁ፤
ነገር ግን ማንም ለመመካት ቢደፍር እኔም እንደ እርሱ ደፍሬ እመካለሁ፤ ይህን የምለው አሁንም እንደ ሞኝ ሆኜ ነው። 22እነርሱ ዕብራውያን ናቸውን? እኔም ዕብራዊ ነኝ፤ እነርሱ እስራኤላውያን ናቸውን? እኔም እስራኤላዊ ነኝ፤ እነርሱ የአብርሃም ዘር ናቸውን? እኔም የአብርሃም ዘር ነኝ። 23እነርሱ የክርስቶስ አገልጋዮች ናቸውን? እኔ ከእነርሱ ይበልጥ የክርስቶስ አገልጋይ ነኝ፤ ይህንንም ስል እንደ እብድ ሆኜ ነው የምናገረው፤ ከእነርሱ ይበልጥ ብዙ ጊዜ በሥራ ደክሜአለሁ፤ ብዙ ጊዜ ታስሬአለሁ፤ ብዙ ጊዜ ተገርፌአለሁ፤ ብዙ ጊዜ ለሞት አደጋ ደርሼአለሁ፤ #ሐ.ሥ. 16፥23። 24ሠላሳ ዘጠኝ፥ ሠላሳ ዘጠኝ ጅራፍ አምስት ጊዜ በአይሁድ ተገርፌአለሁ፤ #ዘዳ. 25፥3። 25ሦስት ጊዜ በዱላ ተደብድቤአለሁ፤ አንድ ጊዜ በድንጋይ ተወግሬአለሁ፤ ሦስት ጊዜ የመርከብ አደጋ ደርሶብኛል፤ አንድ ሌሊትና አንድ ቀን በባሕር ላይ ነበርኩ፤ #ሐ.ሥ. 16፥22፤ 14፥19። 26በጒዞዬ ብዛት የወንዝና የጐርፍ፥ የሽፍቶችም አደጋ ደርሶብኛል፤ ከአይሁድ ወገኖቼና ከአሕዛብ አደጋ ደርሶብኛል፤ በከተማና በበረሓ በባሕርም አደጋ ደርሶብኛል፤ እንዲሁም ከሐሰተኞች አማኞች አደጋ ደርሶብኛል። #ሐ.ሥ. 9፥23፤ 14፥15። 27ብዙ ሥራና ድካም ነበረብኝ፤ ብዙ ጊዜ እንቅልፍ አጥቻለሁ፤ በራብና በውሃ ጥም ተጨንቄአለሁ፤ ብዙ ጊዜም የምግብ እጦት ደርሶብኛል፤ ብርድና መራቆትም ደርሶብኛል። 28ሌላውንም ሁሉ ነገር ሳልቈጥር ስለ አብያተ ክርስቲያን ሁሉ በየቀኑ በማሰብ እጨነቅ ነበር። 29አንድ ሰው ሲደክም እኔ አብሬው ያልደከምኩት መቼ ነው? አንድ ሰው በኃጢአት ሲሰናከል እኔም ያልተናደድኩት መቼ ነው?
30መመካት የሚያስፈልግ ቢሆን እኔ የምመካው ደካማነቴን በሚያሳዩ ነገሮች ነው። 31ለዘለዓለም የተመሰገነው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር እንደማልዋሽ ያውቃል። 32በደማስቆ ከተማ በነበርኩበት ጊዜ ከንጉሡ ከአሬታስ በታች የነበረው አገረ ገዥ እኔን ለመያዝ ፈልጎ የከተማውን በሮች በዘበኞች ያስጠብቅ ነበር። 33ነገር ግን ሰዎች በቅጥሩ መስኮት በኩል በቅርጫት አድርገው አወረዱኝና ከእጁ አመለጥኩ። #ሐ.ሥ. 9፥23-25።
Currently Selected:
2 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997