2 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12
12
የጳውሎስ ራእይ
1ምንም እንኳ በመመካት ጥቅም ባይገኝበት መመካት ካስፈለገ ጌታ በሰጠኝ መገለጥና ራእይ እመካለሁ። 2የክርስቶስ የሆነ አንድ ሰው ዐውቃለሁ፤ ይህ ሰው ከዐሥራ አራት ዓመት በፊት እስከ ሦስተኛው ሰማይ ተወሰደ፤ (የተወሰደውም ከነሥጋው ይሁን ወይም አይሁን አላውቅም፤ እግዚአብሔር ያውቃል።) 3ነገር ግን ይህ ሰው ወደ ገነት እንደ ተወሰደ ዐውቃለሁ፤ ነገር ግን ከነሥጋው ይሁን ወይም አይሁን አላውቅም፤ እግዚአብሔር ያውቃል፤ 4እርሱ ወደ ገነት ተነጥቆ በሰው ቃል ሊገለጥና ሰውም ሊናገረው የማይችለውን ነገር ሰማ። 5እንደዚህ ባለው ሰው እመካለሁ፤ ስለ ራሴ ግን ከደካማነቴ በቀር ሌላ የምመካበት ነገር የለም። 6ታዲያ፥ እኔ እውነት ስለምናገር መመካት ብፈልግም ሞኝ አልሆንም፤ ነገር ግን ማንም በእኔ ላይ ከሚያየውና ከእኔ ከሚሰማው በላይ ግምት እንዳይሰጥ ብዬ ከመመካት እቈጠባለሁ።
7ከነዚህ ከተገለጡልኝ ታላላቅ ነገሮች የተነሣ እንዳልታበይ ሥጋዬን እንደ እሾኽ የሚወጋ ሥቃይ ተሰጠኝ፤ ይህም የሰይጣን መልእክተኛ በመሆን እየጐሸመ በማሠቃየት እንዳልታበይ ያደርገኛል። 8ይህ የሚያሠቃየኝ ነገር ከእኔ እንዲወገድልኝ ጌታን ሦስት ጊዜ ለመንኩት። 9ነገር ግን እርሱ “የእኔ ኀይል ፍጹም ሆኖ የሚገለጠው በአንተ ደካማነት ስለ ሆነ ጸጋዬ ይበቃሃል” አለኝ፤ ስለዚህ የክርስቶስ ኀይል በእኔ ላይ እንዲሆን ከምን ጊዜውም ይልቅ በደካማነቴ ደስ እያለኝ ልመካ እወዳለሁ። 10ኀይል የማገኘው ደካማ በምሆንበት ጊዜ ስለ ሆነ ስለ ክርስቶስ ስደክም፥ ስሰደብ፥ ስቸገር፥ ስሰደድ፥ ስጨነቅ ደስ ይለኛል።
የጳውሎስ ስለ ቆሮንቶስ ሰዎች ማሰብ
11እንደ ሞኝ ተናገርኩ! ታዲያ፥ እንዲህ እንድናገር ያደረጋችሁኝ እናንተ ናችሁ፤ እኔን ማመስገን የሚገባችሁ እናንተ ነበራችሁ፤ እኔ ማንነቴ ያልታወቀ ሰው ብሆንም እንኳ ታላላቅ ከተባሉት ሐዋርያት በምንም አላንስም። 12እኔ እውነተኛ ሐዋርያ መሆኔን የሚያስረዱት ነገሮች እኔ በመካከላችሁ ሳለሁ በትዕግሥት የፈጸምኳቸው ሥራዎች ናቸው፤ እነዚህም ምልክቶችና ድንቅ ነገሮች ተአምራትም ናቸው። 13በእናንተ ላይ ሸክም ሳልሆን ከመቅረቴ በቀር ከሌሎች አብያተ ክርስቲያን እናንተን ያሳነስኳችሁ በምንድን ነው? ይህም ጥፋት ሆኖ ከተቈጠረ ይቅር በሉኝ!
14ወደ እናንተ ለመምጣት ስዘጋጅ አሁን ሦስተኛዬ ጊዜዬ ነው፤ እኔ ሸክም ልሆንባችሁ አልፈልግም፤ እኔ የምፈልገው እናንተን እንጂ ገንዘባችሁን አይደለም። ለልጆቻቸው ሀብት ማከማቸት የሚገባቸው ወላጆች ናቸው እንጂ ልጆች ለወላጆቻቸው ሀብት አያከማቹም። 15ስለ እናንተ እንኳን ገንዘቤን ራሴንም አሳልፌ ብሰጥ እጅግ በጣም ደስ ይለኛል፤ ታዲያ፥ እኔ ይህን ያኽል አብዝቼ ስወዳችሁ እናንተ የምትወዱኝ እንዲህ በጥቂቱ ነውን?
16ያም ሆነ ይህ ሸክም አልሆንኩባችሁም፤ ለመሆኑ በተንኰልና በማታለል የያዝኳችሁም ይመስላችኋል። 17ከላክሁላችሁ ሰዎች በአንዱ እንኳ አማካይነት ተጠቀምኩባችሁን? 18ቲቶ ወደ እናንተ እንዲመጣ ለመንኩት፤ ያንን ወንድማችንንም ከእርሱ ጋር ላክሁት፤ ታዲያ፥ ቲቶስ ተጠቀመባችሁን? እኔና እርሱ ያገለገልናችሁ በአንድ መንፈስ አልነበረምን? አካሄዳችንስ አንድ አልነበረምን?
19ሁላችሁም እስከ አሁን የምታስቡት እኛ በእናንተ ፊት ስለ ራሳችን እንደምንከላከል አድርጋችሁ ነውን? እኛ በክርስቶስ ሆነን የምንናገረው በእግዚአብሔር ፊት ነው፤ ወዳጆቼ ሆይ! እኛ ይህን ሁሉ የምንናገረው እናንተን ለማነጽ ብለን ነው። 20እኔ ወደዚያ በምመጣበት ጊዜ ምናልባት ልትሆኑ እንደምፈልገው ሳትሆኑ፥ እኔም እናንተ እንደምትፈልጉት ሳልሆን እንገናኝ ይሆናል ብዬ እፈራለሁ፤ እንዲሁም በእናንተ ዘንድ ጥል፥ ቅናት፥ ቊጣ፥ ራስ ወዳድነት፥ የሰው ስም ማጥፋት፥ ሐሜት፥ ትዕቢትና ሁከት ይኖሩ ይሆናል ብዬ እፈራለሁ። 21እንደገና ወደ እናንተ ስመጣ አምላኬ ምናልባት በእናንተ ፊት ያዋርደኛል ብዬ እፈራለሁ፤ ከዚህ ቀደም ኃጢአት ሠርተው በዚሁ በሠሩት ርኲሰት፥ ዝሙትና፥ ስድነት ንስሓ ስላልገቡት ሰዎች ሐዘን ላይ እወድቃለሁ ብዬ እፈራለሁ።
Currently Selected:
2 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997