2 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2
2
1እንግዲህ እናንተን እንዳላሳዝናችሁ በማሰብ ለጒብኝት ወደ እናንተ ተመልሼ ላለመምጣት ቊርጥ ውሳኔ አደረግሁ። 2ምንም እንኳ እናንተን ባሳዝናችሁ ካሳዘንኳችሁ ከእናንተ በስተቀር እኔን የሚያስደስት ማን ነው? 3እንደዚያ የጻፍኩላችሁም ወደ እናንተ ስመጣ ደስ ሊያሰኙኝ የሚገባቸው ሰዎች እንዳያሳዝኑኝ ብዬ ነው፤ የእኔ ደስታ የሁላችሁም ደስታ መሆኑን አምናለሁ። 4በትልቅ ሐዘንና በልብ ጭንቀት፥ በብዙ እንባም ሆኜ የጻፍኩላችሁ በጣም የምወዳችሁ መሆኔን እንድታውቁ ብዬ ነው እንጂ ላሳዝናችሁ ብዬ አይደለም።
ለበደለኛ ይቅርታ ማድረግ
5ሰውን ያሳዘነ ማንም ቢኖር ያሳዘነው እኔን ሳይሆን በደሉን ማጋነን አይሁንብኝ እንጂ በሌላ በኩል ከእናንተ ብዙዎቹን አሳዝኖአል። 6ለእንዲህ ዐይነቱ ሰው ከእናንተ አብዛኞቹ የፈረዱበት ቅጣት ይበቃዋል። 7ስለዚህ ይህ ሰው በጣም ከማዘኑ የተነሣ ተስፋ እንዳይቈርጥ ይልቅስ ይቅርታ እንድታደርጉለትና እንድታጽናኑት ይገባል። 8እንዲሁም እርሱን የምትወዱት መሆናችሁን እንደገና እንድታረጋግጡለት እለምናችኋለሁ። 9ያንንም መልእክት የጻፍኩላችሁ ተፈትናችሁ በሁሉ ነገር ታዛዦች መሆናችሁን ለመረዳት ብዬ ነው። 10እናንተ ይቅርታ ለምታደርጉለት ሰው እኔም ይቅርታ አደርግለታለሁ፤ ይቅር የምልለት በደል ካለ እኔ በክርስቶስ ፊት ይቅርታ የማደርግለት ስለ እናንተ ብዬ ነው። 11ይህንንም የማደርገው የሰይጣንን የተንኰል ሥራ ስለምናውቅ ሰይጣን እንዳያታልለን ብዬ ነው።
በጢሮአዳ የጳውሎስ ጭንቀት
12ከዚህ በኋላ የክርስቶስን ወንጌል ለማስተማር ወደ ጢሮአዳ በሄድሁ ጊዜ ጌታ ሰፊ የአገልግሎት በር ከፍቶልኝ ነበር፤ 13ነገር ግን ወንድሜን ቲቶን ባለማግኘቴ መንፈሴ አላረፈም፤ ስለዚህ እዚያ ያሉትን ክርስቲያኖች ተሰናብቼ ወደ መቄዶንያ ሄድኩ። #ሐ.ሥ. 20፥1።
14ነገር ግን እኛን ዘወትር በክርስቶስ ድል አድራጊዎች አድርጎ ለሚመራንና መልካም መዓዛ እንዳለው ሽቶ ስለ ክርስቶስ ያለንን ዕውቀት በየስፍራው ሁሉ እንድናዳርስ ለሚያደርገን አምላክ ምስጋና ይሁን! 15እኛ ለሚድኑትም ሆነ ለሚጠፉት መልካም ሽታ እንዳለው ዕጣን በክርስቶስ ለእግዚአብሔር የቀረብን ነን። 16ለአንዱ የሚገድል የሞት ሽታ ነን፤ ለሌላው ሕይወትን የሚሰጥ የሕይወት መዓዛ ነን፤ ታዲያ፥ ለዚህ አገልግሎት ብቁ የሚሆን ማን ነው? 17እኛ የእግዚአብሔርን ቃል እንደ ንግድ ዕቃ እንደሚቸረችሩት እንደ ብዙዎቹ አይደለንም፤ ነገር ግን ከእግዚአብሔር እንደ ተላኩ ቅን መልእክተኞች በክርስቶስ ሆነን በእግዚአብሔር ፊት እንናገራለን።
Currently Selected:
2 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997