2 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3
3
የአዲስ ኪዳን አገልጋዮች
1እንደገና ራሳችንን ልናመሰግን እንጀምራለንን? ወይስ አንዳንዶች እንደሚያደርጉት ለእናንተ ወይም ከእናንተ የድጋፍ ደብዳቤ ያስፈልገን ይሆን? 2ሰው ሁሉ የሚያውቃችሁና የሚያነባችሁ በልባችን የተጻፋችሁ የድጋፍ ደብዳቤዎቻችን እናንተ ናችሁ። 3እናንተስ በእኛ አገልግሎት የመጣችሁ የክርስቶስ መልእክት መሆናችሁ ግልጥ ነው፤ ይህም መልእክት የተጻፈው በሕያው እግዚአብሔር መንፈስ እንጂ በቀለም አይደለም፤ እንዲሁም በሰው ልብ ጽላት ላይ እንጂ በድንጋይ ጽላት ላይ የተጻፈ አይደለም። #ዘፀ. 24፥12፤ ኤር. 31፥33፤ ሕዝ. 11፥19፤ 36፥26።
4ይህን የምንልበት ምክንያት በክርስቶስ አማካይነት በእግዚአብሔር ላይ እምነት ስላለን ነው። 5አገልግሎታችንን መፈጸም እንድንችል ብቁ የሚያደርገን እግዚአብሔር ነው እንጂ እኛስ በገዛ ራሳችን ምንም ለማድረግ ብቁ አይደለንም። 6የሐዲስ ኪዳኑ አገልጋዮች እንድንሆን ብቃትን የሰጠን እርሱ ነው፤ ይህም በፊደል በተጻፈው ሕግ ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ ርዳታ ነው፤ በፊደል የተጻፈው ሕግ ሞትን ያመጣል፤ መንፈስ ቅዱስ ግን ሕይወትን ይሰጣል። #ኤር. 31፥31።
7ሕግ የተቀረጸው በድንጋይ ጽላት በፊደል ነበር፤ ሕግ በተሰጠበትም ጊዜ የነበረው ብርሃን እየተወገደ የሚሄድ ቢሆንም እስራኤላውያን የሙሴን ፊት ትኲር ብለው ሊመለከቱት አልቻሉም፤ እንግዲህ ሞትን ያመጣ ሕግ በእንዲህ ዐይነት ክብር ከተገለጠ #ዘፀ. 34፥29። 8ታዲያ፥ በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት የሚገኘው አገልግሎት የበለጠ ክብር አይኖረውምን? 9ሰዎች የተኰነኑበት አገልግሎት ይህን ያኽል ክብር ካለው ሰዎች የሚጸድቁበት አገልግሎትማ እንዴት እጅግ የበለጠ ክብር አይኖረውም? 10የኋለኛው ክብር እጅግ የላቀ ከመሆኑ የተነሣ ያለፈው ክብር ምንም እንዳልነበረው ይቈጠራል። 11ያ እየደበዘዘ ይሄድ የነበረው ነገር ይህን ያኽል ክብር ከነበረው፥ ለዘለዓለም ጸንቶ የሚኖረው ነገርማ እንዴት እጅግ የበለጠ ክብር አይኖረውም!
12እንዲህ ዐይነቱ ተስፋ ስላለን በድፍረት እንናገራለን። 13ሙሴ እየከሰመ የሚሄደው የፊቱ መንጸባረቅ እስኪወገድ ድረስ እስራኤላውያን እንዳያዩ ፊቱን ይሸፍን ነበር፤ እኛ ግን እንደ እርሱ አይደለንም። #ዘፀ. 34፥33። 14የእነርሱ ልቡና በእርግጥ ደንዝዞአል፤ እስከ ዛሬም ድረስ የብሉይ ኪዳንን መጻሕፍት ሲያነብቡ ልቡናቸው በዚያው መሸፈኛ እንደ ተሸፈነ ነው። ይህም የሚሆነው ያ መሸፈኛ የሚወገደው በክርስቶስ ብቻ ስለ ሆነ ነው። 15ዛሬም እንኳ ቢሆን የሕግ መጻሕፍትን ባነበቡ ቊጥር ልቡናቸው በመሸፈኛው ይሸፈናል። 16ነገር ግን ሰው ወደ ጌታ ሲመለስ “መሸፈኛው ይወገዳል።” #ዘፀ. 34፥34። 17ጌታ መንፈስ ነው፤ የጌታም መንፈስ ባለበት ነጻነት አለ። 18እኛ ሁላችን ባልተሸፈነ ፊት ሆነን በመስታዋት እንደሚታይ ዐይነት የጌታን ክብር እናንጸባርቃለን፤ እኛም መንፈስ የሆነውን የጌታን መልክ ለመምሰል ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን።
Currently Selected:
2 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997