ሁለተኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 1
1
ዳዊት የሳኦልን ሞት መስማቱ
1ሳኦል ከሞተ በኋላ ዳዊት ዐማሌቃውያንን ድል አድርጎ ተመለሰ፤ በጺቅላግም ሁለት ቀን ቈየ፤ 2በሦስተኛው ቀን አንድ ወጣት ከሳኦል ሰፈር መጣ፤ ልብሱን ቀዶ በራሱ ላይ ትቢያ ነስንሶ ነበር፤ ወደ ዳዊትም ቀርቦ በአክብሮት ወደ መሬት ለጥ ብሎ እጅ ነሣ፤ 3ዳዊትም “ከወዴት መጣህ?” ሲል ጠየቀው።
እርሱም “ከእስራኤላውያን ሰፈር አምልጬ የመጣሁ ነኝ” ሲል መለሰ።
4ዳዊትም “እስቲ የሆነውን ሁሉ ንገረኝ” አለው።
እርሱም “ሠራዊታችን ከጦር ግንባር ሸሸ፤ ከሰዎቻችንም ብዙዎቹ ሞቱ፤ ሳኦልና ልጁ ዮናታንም ሞተዋል” አለ።
5ዳዊትም ወሬ ያመጣውን ወጣት “ሳኦልና ልጁ ዮናታን መሞታቸውን እንዴት ዐወቅህ?” ሲል ጠየቀው።
6ወጣቱም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “እኔ በጊልቦዓ ተራራ ላይ ነበርኩ፤ ሳኦል ጦሩን ተደግፎ ሳለ የጠላት ሠረገሎችና ፈረሰኞች ወደ እነርሱ ሲጠጉ አየሁ፤ 7እርሱም ወደ ኋላ መለስ ሲል እኔን አየኝና ጠራኝ፤ እኔም ‘ጌታዬ፥ እነሆ አለሁ!’ አልኩት፤ 8ማን እንደ ሆንኩ በጠየቀኝ ጊዜም ዐማሌቃዊ መሆኔን ነገርኩት፤ 9እርሱም ‘ወደ እኔ ቀርበህ ግደለኝ፤ በብርቱ ስለ ቈሰልኩ መሞቴ ነው!’ አለኝ፤ 10በሚወድቅበት ጊዜ እንደሚሞት ዐውቅ ስለ ነበር ወደ እርሱ ቀርቤ ገደልኩት፤ ከዚህ በኋላ ዘውዱን ከራሱ ላይ፥ አንባሩንም ከክንዱ ላይ ወሰድኩ፤ ጌታዬ ሆይ! እነሆ፥ እነርሱን ለአንተ አመጣሁልህ።” #1ሳሙ. 31፥1-6፤ 1ዜ.መ. 10፥1-6።
11ዳዊትም በሐዘን ልብሱን ቀደደ፤ ከእርሱም ጋር የነበሩ ተከታዮቹ ሁሉ እንደዚሁ አደረጉ፤ 12በሰይፍ ስለ ተገደሉ ለሳኦል፥ ለልጁ ለዮናታንና ለእግዚአብሔር ሠራዊት ለመላው እስራኤል እስከ ምሽት ድረስ በመጾም በከባድ ሐዘን አለቀሱላቸው።
13ዳዊትም ወሬውን ይዞ የመጣውን ያንን ወጣት “የየት አገር ሰው ነህ?” ሲል ጠየቀው።
እርሱም “በሀገርህ ውስጥ በመጻተኛነት የሚኖር የዐማሌቃዊ ልጅ ነኝ” ሲል መለሰለት።
14ዳዊትም “ታዲያ እግዚአብሔር መርጦ የቀባውን ንጉሥ ለመግደል እንዴት ደፈርክ?” ሲል ጠየቀው። 15ከዚህ በኋላ ዳዊት ከተከታዮቹ አንዱን ጠርቶ “ግደለው!” ሲል አዘዘው፤ ሰውየውም ዐማሌቃዊውን መትቶ ገደለው፤ 16ዳዊትም ዐማሌቃዊውን “ይህን ጥፋት በራስህ ላይ ያመጣህ አንተው ራስህ ነህ፤ እግዚአብሔር መርጦ የቀባውን ንጉሥ ገድያለሁ ብለህ በተናገርክ ጊዜ በራስህ ላይ ፈርደሃል” አለው።
ዳዊት ስለ ሳኦልና ስለ ዮናታን ሞት የሐዘን ቅኔ በመቀኘት አለቀሰላቸው
17ዳዊት ስለ ሳኦልና ስለ ልጁም ስለ ዮናታን ይህን የሐዘን ቅኔ ተቀኘ፤ 18የይሁዳም ሕዝብ ያጠኑት ዘንድ አዘዘ፤ ቅኔውም በያሻር መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል፦ #ኢያሱ 10፥13።
19“እስራኤል ሆይ! ያንተ ጀግና
በተራሮች ላይ ተገድሎ ወደቀ!
ኀያላኑ እንዴት ወደቁ!
20የፍልስጥኤማውያን ሴቶች ልጆች እንዳይደሰቱ፥
የአሕዛብ ሴቶች ልጆች እልል እንዳይሉ፥
ይህን ወሬ በጋት አታውሩ፤
በአስቀሎናም አደባባይ አታውጁ።
21“እናንተ የጊልቦዓ ተራራዎች ሆይ! ዝንብም ሆነ ጤዛ አይውረድባችሁ!
የእርሻ መሬቶቻችሁም ምንም ነገር አይብቀልባቸው!
የጀግኖች ጋሻዎች እዚያ በውርደት ወድቀዋልና፤
የሳኦልም ጋሻ በዘይት መወልወሉ ቀርቶአልና።
22የዮናታን ቀስት ሳይገድል የማይመለስ፥
የሳኦልም ሰይፍ ጠላትን የሚቈራርጥ
ኀያላንን መትቶ የሚሰብር፥
ጠላትን የሚገድል ነበር።
23“ሳኦልና ዮናታን በአስደናቂ ፍቅር ኖሩ፤
በሕይወትም ሆነ በሞት ላለመለያየት ተባበሩ፤
እነርሱም ከንስር የፈጠኑ፥
ከአንበሳም የበረቱ ነበሩ።
24“የእስራኤል ሴቶች ሆይ!
ውድ የሆነ ሐምራዊ ቀሚስ ያለብሳችሁ ለነበረው
በወርቀ ዘቦም ላስጌጣችሁ፥
ለሳኦል አልቅሱለት!
25“በጦርነቱ መካከል
ኀያላን እንዴት ወደቁ?
ዮናታን በተራሮችህ ላይ ተገድሎ ወድቆአል።
26“ወንድሜ ዮናታን ሆይ!
እኔ ስለ አንተ በጣም አዘንኩ፤
አንተ ለእኔ በጣም ተወዳጅ ነበርክ።
ፍቅርህ ለእኔ አስደናቂ ነበር፤
ይኸውም ከሴት ፍቅር የበረታ ነበር።
27“ኀያላን እንዴት ወደቁ?
የጦር መሣሪያዎቹስ እንዴት ጠፉ?”
Currently Selected:
ሁለተኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 1: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997