ሁለተኛ መጽሐፈ ሳሙኤል መግቢያ
መግቢያ
መጽሐፈ ሳሙኤል ክፍል ሁለት፥ የመጽሐፈ ሳሙኤል ክፍል አንድ ተከታይ ሲሆን፤ ዳዊት በመጀመሪያ በደቡብ በኩል የይሁዳ ንጉሥ (ከም. 1-4) ዘግየት ብሎም የሰሜናዊ ክፍል የሆነውን እስራኤልን ጨምሮ የመላዋ አገሪቱ ንጉሥ ሆኖ እንደ ገዛ የሚያስረዳ ታሪክ ነው (ከም. 5-24)። መጽሐፉ፥ ዳዊት ንጉሣዊ መንግሥቱን ለማስፋፋትና ሥልጣኑንም ለማጠናከር በአገሪቱ ውስጥና ከአገሪቱ ውጪ ከነበሩት ጠላቶቹ ጋር ያደረገውን ብርቱ ፍልሚያ ዘርዝሮ ያስረዳል። ዳዊት ጠንካራ እምነት ያለውና እግዚአብሔርን የሚወድ፥ እንዲሁም ከሕዝቡ ታማኝነትን ያተረፈ ሰው እንደ ነበር ተገልጦአል፤ በተጨማሪም አንዳንድ ጊዜ የጭካኔ ሥራ ይፈጽም እንደ ነበረና የሥጋውን ፍላጎት ለማርካት አሠቃቂ የሆኑ ኃጢአቶችን እንደ ሠራ ተዘርዝሮአል። ይሁን እንጂ፥ የእግዚአብሔር ነቢይ ናታን ወደ እርሱ ቀርቦ፥ ስለ ኃጢአቱ ባስገነዘበው ጊዜ፥ ኃጢአቱን ተናዝዞ የእግዚአብሔርን ቅጣት ይቀበል ነበር።
የዳዊት ሕይወትና ያከናወናቸው ሥራዎች የእስራኤልን ሕዝብ እጅግ የማረከ ስለ ነበር፥ ከእርሱ በኋላ በነበሩት ዘመናት በአገሪቱ ላይ ችግር በደረሰ ቊጥር ሌላ ንጉሥ እንዲኖራቸው ሲፈልጉ፥ የዳዊት ልጅ ወይም የዳዊት ዘር የሆነና ልክ እንደ ዳዊት የሚያስተዳድር ሰው ለማግኘት ይመኙ ነበር።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
በይሁዳ የዳዊት መንገሥ 1፥1—4፥12
በመላ እስራኤል ላይ የዳዊት መንገሥ 5፥1—24፥25
ሀ. የመጀመሪያዎቹ ዓመቶች 5፥1—10፥19
ለ. ዳዊትና ቤርሳቤህ 11፥1—12፥25
ሐ. መከራና ችግር 12፥26—20፥26
መ. የመጨረሻዎቹ ዓመቶች 21፥1—24፥25
Currently Selected:
ሁለተኛ መጽሐፈ ሳሙኤል መግቢያ: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997