የሐዋርያት ሥራ 20
20
የጳውሎስ ጒዞ ወደ መቄዶንያና ግሪክ አገር
1ሁከቱ ጸጥ ካለ በኋላ ጳውሎስ ምእመናኑን በአንድነት አስጠርቶ በምክር ቃል አጽናናቸው፤ ተሰናብቶአቸውም ወደ መቄዶንያ ሄደ። 2በእነዚያ በሚያልፍባቸው ስፍራዎች ምእመናንን በብዙ ምክር እያበረታታ ወደ ግሪክ አገር ሄደ። 3እዚያም ሦስት ወር ቈየ፤ ከዚህ በኋላ በመርከብ ወደ ሶርያ ለመሄድ አሰበ፤ ግን አይሁድ በእርሱ ላይ ሤራ ማድረጋቸውን ባወቀ ጊዜ በመቄዶንያ በኩል ለመመለስ ወሰነ።
4የጲርሁስ ልጅ ሶጳጥሮስ ከቤርያ፥ አርስጥሮኮስና ሲኮንዱስ ከተሰሎንቄ፥ ጋይዮስ ከደርቤ፥ ጢሞቴዎስ፥ ቲኪቆስና ጥሮፊሞስ ከእስያ አብረውት ሄዱ። 5እነርሱ ቀድመውን ሄደው በጢሮአዳ ቈዩን። 6እኛ ግን ከቂጣ በዓል በኋላ ከፊልጵስዩስ በመርከብ ተሳፍረን በአምስት ቀን እነርሱ ወዳሉበት ወደ ጢሮአዳ ደረስንና እዚያ ሰባት ቀን አሳለፍን።
የጳውሎስ መጨረሻ ጒብኝት በጢሮአዳ
7ከሳምንቱ በመጀመሪያው ቀን እንጀራ ቈርሶ በአንድነት ለመብላት ተሰበሰብን፤ ጳውሎስ በማግስቱ መሄድ ስለ ነበረበት ለተሰበሰቡት ሰዎች ይናገር ነበር፤ ንግግሩንም እስከ እኩለ ሌሊት አስረዘመ። #20፥7 ከሳምንቱ መጀመሪያ ቀን ማታ፦ ቅዳሜ ማታ ለእሑድ አጥቢያ ማለት ነው። 8እኛ በተሰበሰብንበት ፎቅ ብዙ መብራት ነበር። 9ኤውጤኪስ የተባለ አንድ ወጣት በመስኮት ላይ ተቀምጦ ነበር፤ ጳውሎስ ንግግሩን በማስረዘሙ ወጣቱ ከባድ እንቅልፍ ያዘው፤ እንቅልፍ ስላሸነፈውም ከሦስተኛው ፎቅ ወደ ታች ወደቀ፤ ሰዎች ባነሡት ጊዜ ሞቶ አገኙት። 10ነገር ግን ጳውሎስ ወርዶ በልጁ ላይ ጐንበስ በማለት አቀፈውና “ገና በሕይወት አለ፤ አትደንግጡ!” አለ። 11ጳውሎስ ወደ ፎቅ ተመልሶ ወጣና እንጀራ ቈርሶ ከአማኞች ጋር በላ፤ እስኪነጋም ድረስ ከሰዎቹ ጋር ሲነጋገር ከቈየ በኋላ ሄደ። 12ሰዎቹም የዳነውን ወጣት ወደ ቤት ወሰዱት፤ በዚህም እጅግ ተጽናኑ።
ጳውሎስ ከጢሮአዳ ወደ ሚሊጢ መሄዱ
13ጳውሎስን ለማሳፈር ስለ አሰብን እኛ ቀድመን በመርከብ ወደ አሶስ ሄድን፤ ይህንንም ያደረግነው ጳውሎስ እስከ አሶስ ድረስ በእግሩ ለመሄድ ስለ ወሰነና እንዲህ እንድናደርግ ስለ አዘዘን ነው። 14ከእርሱ ጋር በአሶስ በተገናኘን ጊዜ በመርከብ አሳፍረነው ወደ ሚጢሊኒ አብረን ሄድን። 15በማግስቱ ከዚያ ተነሥተን በኪዮስ ፊት ለፊት ወዳለው ስፍራ በመርከብ ደረስን፤ በሚቀጥለውም ቀን ወደ ሳሞስ ተሻገርንና በማግስቱ ወደ ሚሊጢ ደረስን። 16ጳውሎስ በእስያ ጊዜ እንዳያባክን ብሎ ኤፌሶንን አልፎ ለመሄድ ፈለገ፤ ይህንንም ያደረገው ለጰንጠቆስጤ በዓል በኢየሩሳሌም ለመገኘት አስቦ ስለ ነበር ነው።
ጳውሎስ ለኤፌሶን ሽማግሌዎች ያደረገው የመሰነባበቻ ንግግር
17ጳውሎስ ከሚሊጢ ወደ ኤፌሶን ሰው ልኮ የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎችን አስጠራ፤ 18ወደ እርሱ በመጡም ጊዜ እንዲህ አላቸው፦ “ወደ እስያ ከገባሁበት ቀን ጀምሮ ዘወትር ከእናንተ ጋር እንዴት እንደ ኖርኩ እናንተ ታውቃላችሁ፤ 19በአይሁድ ሤራ ምክንያት መከራ ቢደርስብኝም እንኳ በፍጹም ትሕትናና በእንባ ጌታን አገለግል ነበር። 20በአደባባይም ሆነ በየቤታችሁ ሳስተምራችሁ የሚጠቅማችሁን ሁሉ ነገርኳችሁ እንጂ፥ ምንም ነገር አላስቀረሁባችሁም። 21አይሁድም ሆኑ አሕዛብ ንስሓ ገብተው ወደ እግዚአብሔር እንዲመለሱና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እንዲያምኑ አስጠነቀቅኋቸው። 22አሁንም እዚያ ስደርስ ምን እንደሚደርስብኝ ሳላውቅ በመንፈስ ቅዱስ ታዝዤ ወደ ኢየሩሳሌም መሄዴ ነው። 23ይሁን እንጂ በየከተማው እስራትና ችግር እንደሚገጥመኝ መንፈስ ቅዱስ ነግሮኛል። 24የእግዚአብሔርን የጸጋ ወንጌል ለማስተማር ከጌታ ከኢየሱስ የተቀበልኩትን የማገልገል ግዴታ ከፈጸምኩ ለሕይወቴ ዋጋ አልሰጠውም፤ ለነፍሴም አልሳሳለትም። #2ጢሞ. 4፥7።
25“እስከ አሁን በእናንተ ሁሉ መካከል እየተዘዋወርኩ የእግዚአብሔርን መንግሥት እሰብክ ነበር፤ ከእንግዲህ ወዲህ ግን ከእናንተ ማንም ከቶ ፊቴን እንደማያይ ዐውቃለሁ። 26ስለዚህ ከእናንተ አንድ እንኳ ቢጠፋ ኀላፊነት እንደሌለብኝ በዛሬው ቀን አስገነዝባችኋለሁ። 27የእግዚአብሔርን ሐሳብ ሁሉ ነገርኳችሁ እንጂ ምንም ያስቀረሁባችሁ ነገር የለም። 28መንፈስ ቅዱስ እናንተን ኤጲስ ቆጶሳት አድርጎ ሾሞአችኋል፤ እንግዲህ ለራሳችሁና ለመንጋው ተጠንቀቁ፤ እግዚአብሔር በገዛ ልጁ ደም የዋጃትን ቤተ ክርስቲያን ጠብቁ። 29እኔ ከሄድኩ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ እንደ ተኲላ ጨካኞች የሆኑ ሰዎች እንደሚገቡባችሁ ዐውቃለሁ። 30እንዲሁም አንዳንድ ሰዎች ከመካከላችሁ ተነሥተው ጠማማ ትምህርት በማስተማር ብዙ አማኞችን ወደ እነርሱ ይስባሉ። 31ስለዚህ እያንዳንዳችሁን ሦስት ዓመት ሌሊትና ቀን እንባዬን እያፈሰስኩ እንደ መከርኳችሁ እያስታወሳችሁ ተጠንቀቁ።
32“አሁንም ሊያንጻችሁና በቅዱሳንም መካከል ርስት ሊሰጣችሁ ለሚችለው ለእግዚአብሔርና ለጸጋው ቃልም ዐደራ ሰጥቼአለሁ። 33እኔ የማንንም ብር፥ ወርቅ ወይም ልብስ አልተመኘሁም። 34በገዛ እጆቼ እየሠራሁ ራሴንም ሆነ ጓደኞቼን እረዳ እንደ ነበር እናንተ ራሳችሁ ታውቃላችሁ። 35‘ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ የተባረከ ነው’ የሚለውን የጌታ ኢየሱስን ቃል በማስታወስ፥ በእጃችን እየሠራን ደካሞችን መርዳት እንደሚገባን በብዙ መንገድ አሳይቻችኋለሁ።”
36ከዚህ በኋላ ጳውሎስ ከሁሉም ጋር ተንበርክኮ ጸለየ። 37ሁሉም አለቀሱና ጳውሎስን ዐቅፈው ሳሙት። 38ይልቁንም በጣም ያዘኑት፥ “ከእንግዲህ ወዲህ ፊቴን አታዩም” ብሎአቸው ስለ ነበር ነው፤ እስከ መርከብ ድረስም ሸኙት።
Currently Selected:
የሐዋርያት ሥራ 20: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997