የሐዋርያት ሥራ 22
22
1“ወንድሞቼና አባቶቼ ሆይ! እነሆ፥ አሁን የማቀርብላችሁን መከላከያ ስሙኝ!” 2በዕብራይስጥ ቋንቋ ሲናገር በሰሙ ጊዜ በይበልጥ ጸጥ አሉ፤ ጳውሎስም ንግግሩን በመቀጠል እንዲህ አለ፦
3“እኔ በኪልቅያ በምትገኘው በጠርሴስ ከተማ የተወለድኩ አይሁዳዊ ነኝ፤ ያደግኹት ግን በዚህች በኢየሩሳሌም ከተማ ነው። አስተማሪዬም ገማልያል ነበር፤ የአባቶችን ሕግ ጠንቅቄ የተማርኩና ልክ ዛሬ እናንተ እንደምታደርጉት እግዚአብሔርን በመንፈሳዊ ቅናት የማገለግል ነበርኩ። #ሐ.ሥ. 5፥34-39። 4የክርስትናን እምነት የሚከተሉትን ሁሉ እስከ ሞት የማሳድድ ሰው ነበርኩ፤ ወንዶችንና ሴቶችን እያሰርኩ ወደ ወህኒ ቤት እንዲገቡ አደርግ ነበርኩ። 5ይህም እውነት መሆኑን የካህናት አለቃውና የሽማግሌዎች ሸንጎ በሙሉ ይመሰክሩልኛል። እንዲያውም በደማስቆ ያሉትን እነዚህን ሰዎች አስሬ ወደ ኢየሩሳሌም ለማምጣትና ለማስቀጣት የሚያስችለኝን በደማስቆ ወደሚገኙት ወገኖቻቸው የጻፉትን ደብዳቤ የተቀበልኩት ከእነርሱ ነው። #ሐ.ሥ. 8፥3፤ 26፥9-11።
ጳውሎስ ወደ ክርስቶስ እንዴት እንደ ተመለሰ መተረኩ
(ሐ.ሥ. 9፥1-19፤ 26፥12-18)
6“እኔ ወደ ደማስቆ ስሄድና ወደ ከተማው ስቀርብ እኩለ ቀን ላይ በድንገት ታላቅ ብርሃን ከሰማይ በዙሪያዬ አንጸባረቀ። 7በዚያን ጊዜ በመሬት ላይ ወደቅኹ፤ ‘ሳውል! ሳውል! ለምን ታሳድደኛለህ?’ የሚል ድምፅ ሰማሁ። 8እኔም ‘ጌታ ሆይ! አንተ ማን ነህ?’ አልኩ፤ እርሱም ‘እኔ አንተ የምታሳድደኝ የናዝሬቱ ኢየሱስ ነኝ’ አለኝ። 9ከእኔ ጋር የነበሩት ሰዎች ብርሃኑን አዩ እንጂ እርሱ ሲያነጋግረኝ ድምፁን አልሰሙም። 10እኔም ‘ጌታ ሆይ! ምን ላድርግ?’ አልኩ። ጌታም ‘ተነሥተህ ወደ ደማስቆ ሂድ፤ ልታደርገው የሚገባህ ነገር ሁሉ እዚያ ይነገርሃል’ አለኝ። 11ከብርሃኑ ማንጸባረቅ የተነሣ ማየት ስላልቻልኩ አብረውኝ የነበሩት ሰዎች እጄን ይዘው እየመሩኝ ወደ ደማስቆ አደረሱኝ።
12“እዚያ ሐናንያ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፤ ይህ ሰው በደማስቆ በሚኖሩት አይሁድ ሁሉ የተመሰገነ፥ ሕግ አክባሪና መንፈሳዊ ሰው ነበረ። 13እርሱ ወደ እኔ መጥቶ አጠገቤ ቆመና ‘ወንድሜ ሳውል ሆይ! ዐይንህ እንደገና ይይልህ!’ አለኝ፤ በዚያኑ ቅጽበት ዐይኔ አየ፤ እርሱንም ተመለከትኩት። 14እርሱም እንዲህ አለኝ፤ ‘የአባቶቻችን አምላክ ፈቃዱን እንድታውቅ ጻድቁን እንድታይና ድምፁንም እንድትሰማ አስቀድሞ መርጦሃል። 15ይህንንም ያደረገው ስላየኸውና ስለ ሰማኸው በሰው ሁሉ ፊት የእርሱ ምስክር እንድትሆን ነው። 16ታዲያ፥ አሁን ምን ትጠብቃለህ? ተነሥና የእርሱን ስም በመጥራት ተጠመቅ፤ ከኃጢአትህም ታጠብ።’
17“ከዚህ በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሼ በቤተ መቅደስ በምጸልይበት ጊዜ በተመስጦ ራእይ አየሁ። 18ጌታም ተገልጦልኝ ‘አንተ ስለ እኔ የምትሰጠውን ምስክርነት ስለማይቀበሉ ሳትዘገይ በፍጥነት ከኢየሩሳሌም ውጣ’ አለኝ፤ 19እኔም እንዲህ አልኩ፤ ‘ጌታ ሆይ! በየምኲራቡ እየሄድኩ በአንተ ያመኑትን ሁሉ እንዳሰርኩና እንደ ደበደብኩ እነርሱ ራሳቸው ያውቃሉ። 20የአንተ ምስክር የነበረው እስጢፋኖስ በተገደለ ጊዜ እኔም ራሴ በገዳዮቹ አጠገብ ቆሜ ከእነርሱ ጋር በነገሩ ተስማምቼ ነበር፤ ልብሳቸውንም እጠብቅ ነበር፤’ #ሐ.ሥ. 7፥58። 21ጌታም ‘በሩቅ ወዳሉ ወደ አሕዛብ ስለምልክህ ተነሥና ሂድ!’ አለኝ።”
ጳውሎስ የሮም ዜጋ መሆኑን መግለጡ
22እስከዚህ ድረስ ሕዝቡ ሁሉ የጳውሎስን ንግግር ያዳምጡ ነበር፤ ከዚህ በኋላ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው፦ “እንዲህ ዐይነቱ ሰው ከምድር ላይ ይወገድ! እንዲህ ዐይነቱ ሰው በሕይወት መኖር አይገባውም!” እያሉ ጮኹ። 23እነርሱ እየጮኹ ልብሳቸውን ያውለበልቡና ዐፈር ወደ ሰማይ ይበትኑ ነበር። 24አዛዡ ይህን ባየ ጊዜ ጳውሎስን ወደ ወታደሮች ሰፈር እንዲያስገቡት አዘዘ፤ ሕዝቡ በእርሱ ላይ ስለምን ይህን ያኽል እንደሚጮኹ ለማወቅም እየተገረፈ እንዲመረመር አዘዘ። 25ነገር ግን በጠፍር ወጥረው ሊገርፉት ሲዘጋጁ ጳውሎስ አጠገቡ የቆመውን የመቶ አለቃ “የሮም ዜግነት ያለውን ሰው ያለ ፍርድ ልትገርፉት ተፈቅዶላችኋልን?” አለው።
26የመቶ አለቃው ይህን በሰማ ጊዜ ወደ አዛዡ ሄደና “ምን ልታደርግ ነው? ይህ ሰው እኮ የሮም ዜጋ ነው!” አለው።
27ስለዚህ አዛዡ ወደ ጳውሎስ ቀረብ አለና “እስቲ ንገረኝ፤ አንተ የሮም ዜጋ ነህን?” አለው፤ እርሱም “አዎ፥ ነኝ፤” አለ።
28አዛዡም “እኔ ይህን ዜግነት የገዛሁት በብዙ ገንዘብ ነው” አለ፤ ጳውሎስም “እኔ ግን በሮም ዜግነት ተወልጄአለሁ” አለ።
29ስለዚህ እነዚያ ሊመረምሩት ተዘጋጅተው የነበሩት ሰዎች ወዲያውኑ ከእርሱ ራቁ፤ አዛዡም የሮም ዜጋ የሆነውን ሰው በሰንሰለት ማሰሩን በተገነዘበ ጊዜ ፈራ።
ጳውሎስ በአይሁድ ሸንጎ ፊት መቅረቡ
30በማግስቱ አዛዡ፥ አይሁድ ጳውሎስን የከሰሱበት ትክክለኛ ምክንያት ምን እንደ ሆነ ለማወቅ ፈለገ፤ ስለዚህ የካህናት አለቆችና የሸንጎው አባሎች በሙሉ እንዲሰበሰቡ አዘዘ፤ ጳውሎስንም ከእስራቱ ፈቶ ወሰደና በፊታቸው አቀረበው።
Currently Selected:
የሐዋርያት ሥራ 22: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997