የሐዋርያት ሥራ 28
28
ጳውሎስ በማልታ ደሴት
1ወደ ምድር በደኅና ከደረስን በኋላ የደረስንባት ደሴት ማልታ የምትባል መሆንዋን ዐወቅን። 2የዚያች ደሴት ነዋሪዎች የሚያስደንቅ ደግነት አደረጉልን፤ በዚያን ጊዜም ዝናብ ስለ ዘነበና ብርድ ስለ ሆነ እሳት አንድደው ተቀበሉን፤ 3ጳውሎስ ጭራሮ ሰብስቦ ወደ እሳቱ ሲጥል፥ ከሙቀቱ የተነሣ አንድ እባብ ወጣና በእጁ ላይ ተጣብቆ ተንጠለጠለ፤ 4የማልታ ሰዎች እባብ በጳውሎስ እጅ ላይ ተንጠልጥሎ ባዩ ጊዜ “ይህ ሰው በእርግጥ ነፍሰ ገዳይ ነው! ከባሕሩ ማዕበል በደኅና ቢወጣም ከአምላክ ፍርድ አምልጦ በሕይወት ለመኖር አልቻለም” ተባባሉ። 5ጳውሎስ ግን እባቡን ወደ እሳቱ አራግፎ ጣለውና ምንም ጒዳት ሳያገኘው ቀረ። 6ሰዎቹም “ከአሁን አሁን ሰውነቱ ያብጣል፤ ወይም በድንገት ሞቶ ይወድቃል” በማለት ይጠባበቁ ነበር። ነገር ግን ብዙ ጊዜ ተጠባብቀውት ምንም ጒዳት እንዳልደረሰበት ባዩ ጊዜ አሳባቸውን ለወጡና “ይህስ አምላክ ነው!” አሉ።
7በዚያ በነበርንበት ስፍራ አጠገብ የደሴቲቱ ገዢ የፑፕልዮስ መሬት ነበር፤ ይህ ሰው በቤቱ ተቀብሎን ሦስት ቀን በጥሩ ሁኔታ አስተናገደን። 8በዚያን ጊዜ የፑፕልዮስ አባት ትኩሳትና ተቅማጥ ይዞት ታሞ ተኝቶ ነበር፤ ጳውሎስ ወደ እርሱ ገብቶ ጸለየለት፤ እጁንም ጫነበትና ፈወሰው። 9ይህ ከሆነ በኋላ በደሴቲቱ የሚኖሩት ሌሎች በሽተኞች መጡና ተፈወሱ። 10ሰዎቹ ብዙ ስጦታ አመጡልን፤ አክብሮታቸውንም ገለጡልን፤ በመርከብ ለመሄድ በተነሣንም ጊዜ የሚያስፈልገንን ሁሉ በመርከብ ላይ ጫኑልን።
የጳውሎስ ጒዞ ከማልታ ወደ ሮም
11ሦስት ወር በማልታ ከቈየን በኋላ ክረምቱን በደሴቲቱ ባሳለፈው በእስክንድርያው መርከብ ተሳፍረን ተነሣን፤ መርከቡ ዲዮስቆሮስ የተባሉ የመንታ አማልክት አርማ ነበረበት። 12ወደ ስራኩስ ከተማ በደረስን ጊዜ እዚያ ሦስት ቀን ተቀመጥን። 13ከዚያም በባሕሩ ዞረን ወደ ሬጊዩም ከተማ ደረስን፤ እዚያ አንድ ቀን ካሳለፍን በኋላ የደቡብ ነፋስ ስለ ነፈሰ በሁለተኛው ቀን ወደ ፑቲዮሉስ ሄድን። 14እዚያ ወንድሞችን አገኘንና ከእነርሱ ጋር ሰባት ቀን እንድንቀመጥ ለመኑን፤ ከዚህ በኋላ ወደ ሮም ሄድን። 15በሮም ያሉ ምእመናን ስለ እኛ በሰሙ ጊዜ እስከ አፍዮስ ገበያና “ሦስት ማደሪያዎች” እስከሚባለው ቦታ ድረስ ሊቀበሉን መጡ፤ ጳውሎስ እነርሱን ባየ ጊዜ እግዚአብሔርን አመሰገነና ተጽናና።
ጳውሎስ በሮም
16ወደ ሮም በገባን ጊዜ ጳውሎስ አንድ የሚጠብቀው ወታደር ተሰጠውና ብቻውን እንዲኖር ተፈቀደለት።
17ከሦስት ቀን በኋላ ጳውሎስ በሮም የሚኖሩትን የአይሁድን ታላላቅ ሰዎች አስጠራ፤ በተሰበሰቡም ጊዜ እንዲህ አላቸው፦ “ወንድሞቼ ሆይ፥ በእስራኤል ሕዝብ ላይና በአባቶች ሥርዓት ላይ ያደረግኹት ምንም በደል የለም፤ ይሁን እንጂ በኢየሩሳሌም ታስሬ ለሮማውያን ተላልፌ ተሰጠሁ። 18ሮማውያን ከመረመሩኝ በኋላ በሞት የሚያስቀጣ ምክንያት ስላላገኙብኝ በነጻ ሊለቁኝ አስበው ነበር። 19አይሁድ ግን የእኔን በነጻ መለቀቅ በተቃወሙ ጊዜ ወደ ሮም ንጉሠ ነገሥት ይግባኝ ለማለት ተገደድኩ፤ ሆኖም ሕዝቤን የምከስበት ነገር አልነበረኝም። #ሐ.ሥ. 25፥11። 20አሁንም ያስጠራኋችሁ እንዳያችሁና ይህንንም እንድነግራችሁ ነው፤ እኔ በዚህ በሰንሰለት የታሰርኩት ለእስራኤል በተሰጠው ተስፋ ምክንያት ነው።”
21እነርሱም እንዲህ ሲሉ መለሱለት፦ “ከይሁዳ ምድር ስለ አንተ ጉዳይ የተጻፈ ደብዳቤ አልደረሰንም፤ ወደዚህ ከመጡ ሰዎች ማንም ስለ አንተ ክፉ ያወራ ወይም የተናገረ የለም። 22ይህን አንተ የምትከተለውን የሃይማኖት ክፍል በየቦታው ሰዎች እንደሚቃወሙት እናውቃለን፤ ስለዚህ የአንተ አሳብ ምን እንደ ሆነ መስማት እንፈልጋለን።”
23ቀን ከቀጠሩለትም በኋላ ብዙ ሆነው ወደ መኖሪያ ቤቱ መጡ፤ እርሱም ከጧት እስከ ማታ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት በመመስከር አሳቡን ገለጠላቸው፤ እነርሱንም ለማሳመን ከሙሴ ሕግና ከነቢያት መጻሕፍት እየጠቀሰም ስለ ኢየሱስ አስረዳቸው። 24አንዳንዶቹ የተናገረውን ቃል አመኑ፤ ሌሎች ግን አላመኑም። 25እነርሱም እርስ በርሳቸው ሳይስማሙ ተለያዩ። ሆኖም ከመለያየታቸው በፊት ጳውሎስ ለመጨረሻ ጊዜ ሲናገር እንዲህ አለ፦ “መንፈስ ቅዱስ በነቢዩ በኢሳይያስ አማካይነት ለአባቶቻችሁ የተናገረው ልክ ነበር! 26የተናገረውም ቃል ይህ ነው፦
‘ወደዚህ ሕዝብ ሂድና
መስማትስ ትሰማላችሁ፤ ግን አታስተውሉም፤
ማየትስ ታያላችሁ፤ ግን ልብ አታደርጉም በላቸው፤
27የእነዚህ ሰዎች ልብ ደንድኖአል፤
ጆሮአቸውም ተጨፍኖአል፤ ዐይናቸውም ተዘግቶአል፤
እንዲህስ ባይሆን ኖሮ፥
በዐይናቸው አይተው፥
በጆሮአቸው ሰምተው፥
በልባቸውም አስተውለው፥
ወደ እኔ በተመለሱና
እኔም በፈወስኩአቸው ነበር።’ #ኢሳ. 6፥9-10።
28“እንግዲህ የእግዚአብሔር አዳኝነት መልእክት ለአሕዛብ እንደ ተላከ ዕወቁ፤ እነርሱም እሺ ብለው ይቀበሉታል።” #28፥28 አንዳንድ የጥንት የብራና ጽሑፎች ቊ. 29 አይጨምሩም። 29[“ጳውሎስ ይህን ከተናገረ በኋላ አይሁድ በብርቱ እየተከራከሩ ከዚያ ወጥተው ሄዱ።”]
30ጳውሎስ በተከራየው ቤት ሁለት ዓመት ሙሉ ተቀመጠ፤ ወደ እርሱ የሚመጡትንም ሰዎች ሁሉ ይቀበል ነበር፤ 31የእግዚአብሔርንም መንግሥት በመስበክ ስለ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ማንም ሳይከለክለው በድፍረት ያስተምር ነበር።
Currently Selected:
የሐዋርያት ሥራ 28: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997