ወደ ሮም ሰዎች መግቢያ
መግቢያ
የሐዋርያው የጳውሎስ መልእክት ወደ ሮም ሰዎች የተጻፈው ጳውሎስ በሮም የምትገኘውን ቤተ ክርስቲያን ለመጐብኘት ዕቅድ ስለ ነበረው ተዘጋጅተው እንዲጠብቁት ለማድረግ ነው። የጳውሎስ ዕቅድ በሮም ከሚገኙት ምእመናን ጋር ለጥቂት ጊዜ ከሠራ በኋላ በእነርሱ ረዳትነት ወደ ስፔን ለመሄድ ነበር፤ ስለ ክርስትና እምነት የተረዳውንና ክርስቲያኖች በሕይወታቸው ተግባራዊ ስለሚያደርጉበትም የክርስትና ትምህርት ሁኔታ በመዘርዘር ጽፎአል፤ የጳውሎስ መልእክት በተሟላ ሁኔታ የሚገኘው በዚህ መልእክት ነው።
ጳውሎስ በሮም ለሚገኙት ምእመናን ሰላምታውን ካስተላለፈና እንደሚጸልይላቸውም ተስፋ ከሰጣቸው በኋላ የመልእክቱ ማእከላዊ ሐሳብ (1፥17) “ከእግዚአብሔር የሚገኘው ጽድቅ በእምነት፥ ለእምነት እንደ ሆነ በወንጌል ተገልጦአል” የሚለው ቃል መሆኑን ያመለክታል።
ከዚህ በኋላ ጳውሎስ ይህንኑ ሐሳብ በማስፋፋት ይጽፋል፤ አይሁድም ሆኑ አሕዛብ ሰዎች ሁሉ የኃጢአት ተገዢዎች ስለ ሆኑ ከእግዚአብሔር ጋር መታረቅ ይኖርባቸዋል፤ ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር ሊታረቁ የሚችሉትም በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ነው፤ የዚህም ከእግዚአብሔር ጋር የሚመሠርቱት አዲስ ኅብረት ውጤት አዲስ ሕይወት ስለ መሆኑ ጳውሎስ በሰፊው ያስረዳል። አማኝ ከእግዚአብሔር ጋር ሰላም ይኖረዋል፤ በእግዚአብሔርም መንፈስ አማካይነት ከኃጢአትና ከሞት ኀይል ነጻ ያወጣል፤ ከም. 5 እስከ 8 ጳውሎስ የእግዚአብሔር ሕግና በአማኞች ሕይወት የሚሠራው የእግዚአብሔር መንፈስ ኀይል ዓላማው ምን እንደ ሆነ ይገልጣል፤ ከዚህም በመቀጠል ጳውሎስ “እግዚአብሔር ለሰው ዘር ባለው ዕቅድ ውስጥ አይሁድና አሕዛብ እንዴት ሊጣመሩ ይችላሉ?” ለሚለው ጥያቄ መልስ ለመስጠት ጥረት ያደርጋል።
እንደገናም ጳውሎስ እንደ ገለጠው፥ አይሁድ ኢየሱስን ሳይቀበሉ መቅረታቸው የእግዚአብሔር ዕቅድ ነው፤ ይህም የሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት እግዚአብሔር በገለጠው የመዳን ጸጋ መላውን የሰው ዘር ተሳታፊ ለማድረግ ነው። ይሁን እንጂ አይሁድ ኢየሱስን የሚቀበሉበት ጊዜ እንደሚመጣ ጳውሎስ ያምናል፤ በመጨረሻ ጳውሎስ የክርስትናን ሕይወት እንዴት መኖር እንደሚገባ፥ በተለይም ምእመናን እርስ በርስ ባላቸው ግንኙነት የፍቅርን መንገድ መከተል እንደሚገባቸው ያስረዳል፤ እግዚአብሔርን ስለ ማገልገል፥ ክርስቲያኖች ለአገራቸውና እርስ በርሳቸውም ስላላቸው ኀላፊነትና፥ በኅሊና ምክንያት ስለሚነሡ ጥያቄዎች በመዘርዘር ያስረዳል።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
የመጽሐፉ ፍሬ ሐሳብ መግቢያ 1፥1-17
መዳን ለሰው ልጅ አስፈላጊ መሆኑ 1፥18—3፥20
የእግዚአብሔር የማዳኑ መንገድ 3፥21—4፥25
በክርስቶስ የሚገኝ አዲስ ሕይወት 5፥1—8፥39
እስራኤል በእግዚአብሔር ዕቅድ 9፥1—11፥36
ክርስቲያናዊ ምግባር 12፥1—15፥13
ማጠቃለያና ሰላምታ 15፥14—16፥27
Currently Selected:
ወደ ሮም ሰዎች መግቢያ: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997