ትንቢተ ዳንኤል 10
10
ዳንኤል በጤግሮስ ወንዝ አጠገብ ያየው ራእይ
1የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ በነገሠ በሦስተኛው ዓመት ብልጣሶር ለተባለው ለዳንኤል ሌላ ራእይ ተገለጠለት፤ በራእዩም የተነገረው ቃል እውነት ነው፤ ነገር ግን ለማስተዋል እጅግ ከባድ ከመሆኑ የተነሣ ትርጒሙ በራእይ ተገለጠለት።
2በዚያን ጊዜ እኔ ዳንኤል ሦስት ሳምንት ሙሉ በሐዘን ላይ ነበርኩ። 3ሥጋም ሆነ ሌላ ጥሩ ምግብ አልተመገብኩም፤ የወይን ጠጅም ፈጽሞ አልቀመስኩም፤ ሦስቱ ሳምንቶች እስኪያልፉ ድረስ ራሴን ቅባት አልተቀባሁም።
4የዓመቱ የመጀመሪያ ወር በገባ በሃያ አራተኛው ቀን በታላቁ በጤግሮስ ወንዝ ዳር ቆሜ ነበር። 5ቀና ብዬ ስመለከት ቀጭን ሐር የለበሰና በወገቡም የወርቅ ቀበቶ የታጠቀ አንድ ሰው አየሁ። 6የዚህ ሰው አካል እንደ ዕንቊ ያበራ ነበር፤ ፊቱም እንደ መብረቅ ያንጸባርቅ ነበር፤ ዐይኖቹም የእሳት ነበልባል ይመስሉ ነበር፤ እጆቹና እግሮቹ እንደ ተወለወለ ነሐስ ያበሩ ነበር፤ ድምፁም የብዙ ሰዎችን ድምፅ ያኽል ያስተጋባ ነበር። #ራዕ. 1፥13-15፤ 2፥18፤ 19፥2።
7ራእዩን ያየሁ እኔ ዳንኤል ብቻ ነበርኩ፤ አብረውኝ የነበሩት ሰዎች ግን ምንም ነገር አላዩም፤ ሆኖም እጅግ ስለ ደነገጡ ሮጠው ተደበቁ። 8እኔም ይህን አስደናቂ ራእይ እየተመለከትኩ ብቻዬን ቀረሁ፤ የነበረኝን ኀይል ሁሉ በማጣት ደክሜ ነበር፤ ፊቴም በጣም ገረጣ። 9የሰውዬውን ድምፅ በሰማሁ ጊዜ በመደንገጥ ኅሊናዬን ስቼ በመሬት ላይ ወደቅኹ፤ በግንባሬም እንደ ተደፋሁ ቀረሁ። 10ከዚያ በኋላ አንዳች እጅ ዳሰሰኝ፤ ገና እየተንቀጠቀጥኩ ስለ ነበር ደግፎ በእጄና በጒልበቴ እንድቆም አደረገኝ።
11መልአኩም “በእግዚአብሔር ዘንድ እጅግ የተወደድክ ዳንኤል ሆይ! እነሆ፥ እኔ ወደ አንተ ተልኬ መጥቼአለሁ፤ ባለህበት ቀጥ ብለህ ቁም፤ የምነግርህንም በጥንቃቄ አስተውል!” አለኝ። ይህን በነገረኝ ጊዜ እየተንቀጠቀጥኩ ቆምኩ።
12ደግሞም እንዲህ አለኝ፦ “ዳንኤል ሆይ! አትፍራ! ማስተዋልን ለማግኘት ራስህን በእግዚአብሔር ፊት ለማዋረድ ከወሰንክበት ከመጀመሪያው ቀን አንሥቶ ጸሎትህ ተሰምቶአል፤ እኔም ተልኬ ወደ አንተ የመጣሁት ጸሎትህ መልስ ከማግኘቱ የተነሣ ነው። 13የፋርስ መንግሥት አለቃ የሆነው መንፈስ ኻያ አንድ ቀን ሙሉ ተቃወመኝ፤ በፋርስ ብቸኛ መሆኔን አይቶ ከመላእክት አለቆች አንዱ የሆነው ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ። #ራዕ. 12፥7። 14እኔም የመጣሁት በወገኖችህ ላይ በመጨረሻው ዘመን የሚደርስባቸውን ነገር ላስረዳህ ነው፤ ስለዚህ ከዚህም በቀር ወደፊት የሚሆነውን ነገር የሚገልጥ ሌላ ራእይ አለ።”
15ይህንንም በነገረኝ ጊዜ የምናገረውን አጥቼ ወደ መሬት አቀርቅሬ መናገር አቃተኝ። 16ከዚህ በኋላ ሰውን የሚመስለው እጁን ዘርግቶ ከንፈሮቼን ዳሰሰ፤ እኔም እንዲህ አልኩት፦ “ጌታዬ ሆይ! ይህ ራእይ በጣም ስላሳመመኝ ሰውነቴ ዛለ። 17እኔ አገልጋይህ ስሆን ከአንተ ከጌታዬ ጋር መነጋገር እንዴት እችላለሁ? መተንፈስ እስከሚያቅተኝ ድረስ እጅግ ደክሜአለሁ።”
18ያ ሰው የሚመስለው መልአክ እንደገና በዳሰሰኝ ጊዜ ብርታት አገኘሁ። 19እርሱም “አንተ በእግዚአብሔር ዘንድ የተወደድክ ሰው ሆይ! መልካም ይሆንልሃል፤ አትፍራ! አይዞህ በርታ!” አለኝ። እርሱም በተናገረኝ ጊዜ ብርታት አገኘሁና “ጌታዬ ሆይ፥ ብርታት ስለ ሰጠኸኝ እነሆ፥ ተናገር” አልኩት።
20-21እንደገናም እንዲህ አለኝ፦ “ወደ አንተ የመጣሁት ለምን እንደ ሆነ ታውቃለህን? እኔ ወደ አንተ የመጣሁት በእውነት መጽሐፍ የተጻፈውን ልገልጥልህ ነው፤ አሁንም ተመልሼ የፋርስ መንግሥት አለቃ ከሆነው መንፈስ ጋር ጦርነት አደርጋለሁ፤ እኔ ከሄድኩ በኋላ የግሪክ መንግሥት አለቃ የሆነው መንፈስ ይመጣል፤ ይሁን እንጂ የእስራኤል ጠባቂ መልአክ ከሆነው ከሚካኤል በቀር እኔን የሚረዳ የለም።
Currently Selected:
ትንቢተ ዳንኤል 10: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997