ትንቢተ ዳንኤል 9
9
ዳንኤል ስለ ሕዝቡ መጸለዩ
1ትውልዱ ሜዶናዊ የሆነው የአርጤክስስ ልጅ ዳርዮስ በባቢሎን ነገሠ። 2በነገሠም በመጀመሪያው ዓመት እኔ ዳንኤል ቅዱሳት መጻሕፍትን እየተመለከትኩ እግዚአብሔር ለነቢዩ ለኤርምያስ በነገረው መሠረት ኢየሩሳሌም ፍርስራሽ ሆና የምትቈይባት ዘመን ሰባ ዓመት መሆኑን ዐወቅሁ። #ኤር. 25፥11፤ 29፥10። 3ማቅ ለብሼና ዐመድ ላይ ተቀምጬ በመጾም ጸሎቴንና ልመናዬን ለማቅረብ ፊቴን ወደ ጌታ እግዚአብሔር መለስኩ። 4ወደ አምላኬ ወደ እግዚአብሔር በመናዘዝ እንዲህ ስል ጸለይኩ፦
“ለሚወዱህና ትእዛዞችህን ለሚጠብቁ ቃል ኪዳንህንና ዘለዓለማዊ ፍቅርህን የምትጠብቅ ታላቅና መፈራት የሚገባህ አንተ ጌታ እግዚአብሔር ነህ።
5“እኛ ግን ክፉዎችና ዐመፀኞች ሆነን ኃጢአት በመሥራት በድለናል፤ ሕግህንና ትእዛዞችህን ከመፈጸም ቸል ብለናል። 6ለንጉሦቻችን፥ ለገዢዎቻችን፥ ለቀደሙት አባቶቻችንና በምድሪቱ ለሚኖሩ ሕዝብ ሁሉ በስምህ የተናገሩትን አገልጋዮችህን ነቢያትን አላዳመጥንም። 7ጌታ ሆይ! አንተ እውነተኛ ነህ፤ ነገር ግን ለአንተ ታማኞች ባለመሆናችን፥ እኛ በምድር ሁሉ ላይ የበተንከን በቅርብና በሩቅ ያለን የይሁዳ ሕዝብ የኢየሩሳሌም ነዋሪዎችና መላዋ የእስራኤል ሕዝብ በአሁኑ ጊዜ ኀፍረት ደርሶብናል። 8ጌታ ሆይ! እኛ ሁላችን አንተን ስለ በደልን እኛ፥ ንጉሦቻችን፥ ገዢዎቻችንና የቀድሞ አባቶቻችን ኀፍረት ደርሶብናል። 9ጌታ አምላካችን ሆይ፥ ምንም እኛ በአንተ ላይ ብናምፅ አንተ መሐሪና ይቅር ባይ ነህ። 10እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ! ሕጎችህን በመጠበቅ ታዛዦች ሆነን አልተገኘንም፤ በአገልጋዮችህ በነቢያት አማካይነት የሰጠኸንን ትእዛዞች አልጠበቅንም። 11እስራኤላውያን ሁሉ ሕግህን ተላለፉ፤ የተናገርከውን ሁሉ ማዳመጥ እምቢ አሉ፤ አንተን ስለ በደልን በአገልጋይህ በሙሴ በኩል የተሰጠውን ሕግ በመሐላ የተገለጠውን ርግማን ሁሉ በእኛ ላይ አመጣህብን። 12በእኛና በመሪዎቻችን ላይ ታላቅ መከራ እንደምታመጣብን የተናገርከው ሁሉ እንዲፈጸምብን አደረግህ፤ ስለዚህም በምድር ላይ ካሉ አገሮች ሁሉ የኢየሩሳሌምን ያኽል ቅጣት የደረሰበት ከቶ የለም። 13በሙሴ ሕግ በተጻፈው መሠረት ይህን ሁሉ መከራ በእኛ ላይ አመጣህ፤ እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ፥ ይህም ሁሉ ሆኖ ከኃጢአታችን በመመለስና እውነትን በመከተል የአንተን ምሕረት ለማግኘት ወደ አንተ አልጸለይንም። 14አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ! አንተ በሥራህ ሁሉ እውነተኛ ነህ፤ እኛ ግን ስለ አልታዘዝንህ ይህን ሁሉ መከራ አመጣህብን።
15“እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ! ከዚህ በፊት በብርቱ ኀይልህ ሕዝብህን ከግብጽ በማውጣት ስምህ እስከ ዛሬ ድረስ እንዲታወቅ አድርገሃል፥ እኛ ግን ኃጢአተኞችና በደለኞች ሆንን። 16ጌታ ሆይ! ስለ ፈጸምካቸው የጽድቅ ሥራዎች ሁሉ ብለህ ከተቀደሰችው ተራራህ ከኢየሩሳሌም ቊጣህንና መዓትህን እንድታነሣ እንለምንሃለን፤ በኃጢአታችንና በአባቶቻችንም በደል ምክንያት ኢየሩሳሌምና ሕዝብህ በጐረቤቶቻችን ሁሉ መካከል ተዋርደዋል። 17አምላክ ሆይ! ጸሎቴንና ልመናዬን ስማ፤ ስለ ስምህ ስትል ለፈረሰው ቤተ መቅደስህ ራራ። 18አምላክ ሆይ! እባክህ አድምጠኝ፤ የእኛን ችግርና በስምህ የምትጠራውን ከተማ ጥፋት ተመልከት፤ ወደ አንተ የምንጸልየው የአንተን ምሕረት በመተማመን እንጂ በእኛ መልካም ሥራ በመመካት አይደለም። 19እግዚአብሔር ሆይ! ስማን! እግዚአብሔር ሆይ! ይቅር በለን! እባክህ አድምጠን! ሥራህንም ግለጥ! አምላክ ሆይ! አትዘግይ፤ ይህች ከተማና ይህ ሕዝብ በስምህ የተጠሩ ናቸው።”
ገብርኤል የትንቢቱን ትርጒም መግለጡ
20የራሴንና የወገኖቼን የእስራኤላውያንን ኃጢአት እየተናዘዝኩ፥ ስለ ቅዱስ ተራራው በአምላኬ በእግዚአብሔር ፊት ጸሎቴን ቀጠልኩ። 21በዚህም ጸሎት ላይ ሳለሁ በመጀመሪያው ራእይ ያየሁት ገብርኤል እኔ ወዳለሁበት ስፍራ በፍጥነት እየበረረ መጣ፤ ጊዜውም የሠርክ መሥዋዕት የሚቀርብበት ወቅት ነበር። #ሉቃ. 1፥19፤26። 22እርሱም እንዲህ ሲል አስረዳኝ፦ “ዳንኤል ሆይ! እኔ ወደዚህ የመጣሁት የትንቢቱን ምሥጢር እንድታውቅ ጥበብንና ማስተዋልን ልሰጥህ ነው፤ 23ገና መጸለይ ስትጀምር እግዚአብሔር ልመናህን ሰምቶአል፤ አንተ በእርሱ ዘንድ የተወደድክ ስለ ሆነ የጸሎትህን መልስ ልነግርህ መጥቼአለሁ፤ እንግዲህ የምነግርህን አዳምጠህ የራእዩን ትርጒም ተረዳ።
24“ሰባት ጊዜ ሰባ ሳምንት የተባለው እግዚአብሔር ሕዝብህንና የተቀደሰ ከተማህን ከኃጢአትና ከክፋት ነጻ ለማውጣት ውሳኔ ያደረገበት ጊዜ ነው፤ በዚያን ጊዜ በደል ይሰረያል፤ ዘለዓለማዊ ፍትሕ ይሰፍናል፤ ራእይና ትንቢት ይፈጸማል፤ ቤተ መቅደሱም ይታደሳል። 25ይህን ልብ ብለህ አስተውል፤ ኢየሩሳሌም እንድትታደስ ትእዛዝ ከወጣበት ጊዜ አንሥቶ መሲሕ እስከሚመጣበት ጊዜ ድረስ ሰባት ሳምንቶች ያልፋሉ፤ እንዲሁም ለሥልሳ ሁለት ሳምንት በችግር ጊዜ ኢየሩሳሌም፥ መንገዶችዋና የመከላከያ ጒድጓድዋ ይገነባሉ። ይሁን እንጂ ይህ ሁሉ የመከራ ዘመን ይሆናል። 26ከስድሳ ሁለት ሳምንት በኋላ መሲሑ ያለ ፍትሕ ይገደላል፤ የሚገደለውም ለራሱ አይደለም፤ የሚመጣው መሪ ወታደሮች ቤተ መቅደሱንና ከተማይቱን ይደመስሳሉ፤ መጨረሻውም እንደ ጐርፍ ይመጣል፤ ውድመት ስለ ታወጀ ጦርነት እስከ መጨረሻ ይቀጥላል። 27ያም መሪ ለአንድ ሳምንት ከብዙ ሕዝቦች ጋር የጠበቀ ቃል ኪዳን ያደርጋል፤ በሳምንቱም እኩሌታ መሥዋዕቱንና ቊርባኑን ያስቀራል፤ በእነርሱም ፈንታ ጥፋት የሚያስከትለው ርኲሰት እንዲተካ ያደርጋል። ይህም የሚሆነው በዚያ አጥፊ መሪ ላይ የታወጀው ቅጣት እስኪፈጸም ድረስ ነው።” #ዳን. 11፥31፤ 12፥11፤ ማቴ. 24፥15፤ ማር. 13፥14።
Currently Selected:
ትንቢተ ዳንኤል 9: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997