ትንቢተ ዳንኤል 8
8
ዳንኤል በራእይ ያያቸው አውራ በግና ፍየል
1ብልጣሶር በነገሠ በሦስተኛው ዓመት እኔ ዳንኤል ከዚህ በፊት ካየሁት ሌላ ራእይ አየሁ፤ 2በዔላም አውራጃ በግንብ በታጠረው በሱሳ ከተማ ሆኜ ራሴን በራሴ በራእይ አየሁ፤ በኡላይ ወንዝ አጠገብም ቆሜ ነበር። 3በዚያም ወንዝ ዳር ሁለት ረጃጅም ቀንዶች ያሉት አንድ አውራ በግ ቆሞ ነበር፤ ከሁለቱ ቀንዶች አንደኛው ዘግይቶ የበቀለ ቢሆንም ከሌላው ቀንድ ይረዝም ነበር። 4ያም በግ በቀንዶቹ ለመጐሸም ወደ ምዕራብ፥ ወደ ሰሜን፥ ወደ ደቡብ ሲቃጣ አየሁ፤ በፊቱ ቀርቦ የሚቋቋመው ወይም ከኀይሉ ማምለጥ የሚችል አውሬ አልነበረም፤ የፈለገውን ሁሉ ያደርግ ነበር፤ ይበልጥም እየበረታ ሄደ።
5ይህንንም ራእይ በማሰላሰል ላይ ሳለሁ በዐይኖቹ መካከል ትልቅ ቀንድ ያለው አንድ አውራ ፍየል ምድርን አቋርጦ እግሮቹ መሬት ሳይነኩ ከምዕራብ በኩል እየበረረ መጣ። 6እርሱም በወንዙ አጠገብ ቆሞ ወዳየሁት ሁለት ቀንዶች ወዳሉት በግ በታላቅ ቊጣ ተንደርድሮ መጣበት። 7ወደ በጉም ሲጠጋ አየሁት፤ እርሱም በበጉ ላይ በመቈጣት መቶት ሁለት ቀንዶቹን ሰባበረበት፤ በጉም ለመቋቋም የሚያበቃው ኀይል አላገኘም፤ ስለዚህ ፍየሉ ወደ መሬት ጥሎ ረገጠው፤ ከኀይሉም ሊያድነው የሚችል አልነበረም።
8አውራው ፍየል እጅግ እየበረታ ሄደ፤ ከኀያልነቱም የተነሣ ታላቅ የነበረው ቀንዱ ተሰበረ፤ በቦታውም አራት ታላላቅ ቀንዶች ተተኩ፤ እያንዳንዱም ቀንድ ወደተለያየ አራት አቅጣጫ ያመለክት ነበር፤ 9ከነዚህ ከአራቱ ቀንዶች በአንደኛው ላይ ሌላ ትንሽ ቀንድ በቀለ፤ የዚህም የትንሽ ቀንድ ኀይል ወደ ደቡብና ወደ ምሥራቅ ወደ መልካሚቱ ምድር ተስፋፋ። 10ወደ ሰማይ ሠራዊት እስከሚደርስ ድረስ ከፍ አለ፤ እጅግ ብርቱ ሆነ፤ ከእነርሱም ጥቂቱን ወደ መሬት አውርዶ ረገጣቸው። #ራዕ. 12፥4። 11የሰማይ ሠራዊትን አለቃ ሳይቀር ተፎካከረው፤ በየቀኑ ለእርሱ የሚቀርብለትን መሥዋዕት እንዲቀር አደረገ፤ መቅደሱንም አረከሰ። 12በክፋት ምክንያት ሠራዊቱና መደበኛው የሚቃጠል መሥዋዕት ለእርሱ ተሰጠ፤ እርሱም እውነትን ወደ መሬት ጣለ፤ የሚያደርገውም ነገር ሁሉ እየተሳካለት ሄደ።
13ከዚያ በኋላ አንድ ቅዱስ ሲናገር ሰማሁ፤ ሌላው ቅዱስ ደግሞ ለተናገረው ቅዱስ እንዲህ አለው፦ “እነዚህ በራእዩ የታዩት ነገሮች የሚፈጸሙበት ጊዜ መቼ ነው? ጥፋትን የሚያስከትለው ዐመፅና የዘወትርን መሥዋዕት ተክቶ የሚቈየው እስከ መቼ ነው? ቤተ መቅደሱና የሰማይ ሠራዊት ተላልፈው በመሰጠት ተረግጠው የሚቈዩትስ እስከ መቼ ነው?”
14የተጠየቀውም ቅዱስ “የጠዋትና የማታ መሥዋዕት የማይቀርብባቸው ሁለት ሺህ ሦስት መቶ ቀኖች ይሆናሉ፤ ከዚያን በኋላ ቤተ መቅደሱ ይነጻል” ብሎ ሲመልስለት ሰማሁ።
መልአኩ ገብርኤል የራእዩን ትርጒም ማስረዳቱ
15እኔ ዳንኤል የራእዩ ትርጒም ምን እንደ ሆነ በማሰላሰል ላይ ሳለሁ በድንገት አንድ ሰው የሚመስል አካል በፊቴ ቆመ። 16ከኡላይ ወንዝ ማዶ “ገብርኤል ሆይ! ይህ ሰው የራእዩን ትርጒም እንዲረዳው አድርግ!” የሚል የሰው ድምፅ ሰማሁ። #ሉቃ. 1፥19፤26። 17ገብርኤልም መጥቶ በአጠገቤ በቆመ ጊዜ ደንግጬ ወደ መሬት ወደቅኹ። እርሱም “የሰው ልጅ ሆይ! ራእዩ የሚያመለክተው ስለ ዓለም መጨረሻ መሆኑን ተረዳ” አለኝ። 18እርሱም በሚናገርበት ጊዜ ኅሊናዬን ስቼ በግንባሬ ወደ መሬት ተደፋሁ፤ እርሱ ግን ዳሰሰኝና ከመሬት አንሥቶ በእግሮቼ አቆመኝ። 19እንዲህም አለኝ፦ “ራእዩ የሚያመለክተው ስለ ዓለም መጨረሻ ስለ ሆነ በቊጣ ቀን ምን እንደሚሆን አስረዳሃለሁ።
20“ሁለት ቀንዶች ያሉት አውራ በግ የሜዶንንና የፋርስን ነገሥታት ያመለክታል፤ 21አውራው ፍየል የሚያመለክተው የግሪክን ንጉሥ ነው፤ በዐይኖቹ መካከል ያለው ትልቅ ቀንድ ደግሞ የመጀመሪያውን የግሪክ ንጉሥ ያመለክታል። 22የመጀመሪያው ቀንድ ሲሰበር የወጡት አራት ቀንዶች ያ መንግሥት ለአራት መከፈሉን ያመለክታሉ፤ እያንዳንዱም መንግሥት የመጀመሪያውን መንግሥት ያኽል ብርቱ አለመሆኑን ይገልጣል።
23“የእነዚያ ነገሥታት ዘመነ መንግሥት ፍጻሜ ሲደርስ ጨካኝና ተንኰለኛ የሆነ ንጉሥ ይነሣል። 24ይህም ንጉሥ እጅግ ብርቱ ይሆናል፤ ይሁን እንጂ በራሱ ኀይል አይደለም፤ እጅግ አሠቃቂ የሆነ ጥፋት ይፈጽማል፤ የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል፤ በኃያላን ሰዎችና በተቀደሱት ሕዝብ ላይ ጥፋትን ያስከትላል። 25እጅግም ተንኰለኛ ስለ ሆነ በማታለል ይበለጽጋል፤ ራሱንም ከሁሉ በላይ ከፍ ከፍ ያደርጋል፤ ብዙ ሰዎችን ያለ ምንም ማስጠንቀቂያ ይገድላል፤ የልዑላንን ልዑል እንኳ ይፈታተናል፤ በመጨረሻም እርሱ ራሱ ይጠፋል፤ የሚጠፋውም በሰው ኀይል አይደለም። 26ስለ ጠዋትና ስለ ማታ መሥዋዕት የተነገረው ራእይ እውነት ነው፤ አንተ ግን ይህ ራእይ የሚፈጸምበት ጊዜ ሩቅ ስለ ሆነ በምሥጢር ያዘው” አለኝ።
27እኔ ዳንኤል እጅግ ደከመኝና ሕመም ስለ ተሰማኝ ለብዙ ቀኖች ተኛሁ፤ ከዚያም በኋላ ተነሥቼ ንጉሡ በመደበልኝ ሥራ ላይ ተሰማራሁ፤ በራእዩ እጅግ ተጨነቅሁ፤ ላስተውለውም አልቻልኩም ነበር።
Currently Selected:
ትንቢተ ዳንኤል 8: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997