ኦሪት ዘዳግም 24
24
ስለ ፍችና ስለ ዳግም ጋብቻ የተሰጠ መመሪያ
1“አንድ ሰው አንዲት ሴት ካገባ በኋላ እርስዋን የማይወድበትን ነገር በማግኘቱ ቢጠላት የፍች የምስክር ወረቀት ጽፎ በመስጠት ከቤቱ ያባርራታል፤ #ማቴ. 5፥31፤ 19፥7፤ ማር. 10፥4። 2እንደገናም ሌላ ባል ታገባ ይሆናል፤ 3ሁለተኛውም ባል ስለሚጠላት የተፈታችበትን ምክንያት የሚገልጥ የፍች ደብዳቤ ጽፎ በመስጠት ከቤቱ ያባርራታል፤ ወይም ሁለተኛው ባልዋ ይሞት ይሆናል፤ 4በሁለቱም መንገድ ቢሆን ያ የመጀመሪያ ባልዋ እንደገና ሊያገባት አይፈቀድለትም፤ እንደ ረከሰች አድርጎ ይቊጠራት፤ እርስዋን እንደገና ቢያገባ ይህ ድርጊት በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ ነው፤ እግዚአብሔር አምላካችሁ በሚሰጣችሁ ምድር ስትኖሩ እንደዚህ ያለውን አስከፊ ኃጢአት መፈጸም አይገባችሁም።
ልዩ ልዩ ሕጎች
5“አዲስ ሚስት ያገባ ሰው ወታደር ሆኖ ለማገልገል አይገደድ፤ ሌላም ተጽዕኖ አይደረግበት፤ ለአንድ ዓመት ከማናቸውም ግዴታ ነጻ ሆኖ በቤቱ ሚስቱን ደስ ያሰኛት።
6“ለአንድ ሰው ብድር በምታበድርበት ጊዜ የእህል ወፍጮውን ወይም መጁን መያዣ አድርገህ አትውሰድበት፤ ይህን ማድረግ ሕይወትን እንደ መያዣ አድርጎ እንደ መውሰድ ይቈጠራል።
7“እስራኤላዊ ወገኑን አፍኖ በመውሰድ ባሪያ አድርጎ የሚጠቀምበትና ወይም ለሌላ ሰው በባርነት አሳልፎ የሚሸጠው ማንም ሰው በሞት ይቀጣ፤ በዚህም ዐይነት ክፉ ነገርን ታስወግዳላችሁ። #ዘፀ. 21፥16።
8“ብርቱ ጥንቃቄ በማድረግ ከሥጋ ደዌ በሽታ ተጠበቁ፤ እኔ ባዘዝኳቸው መሠረት ሌዋውያን ካህናት የሚሰጡአችሁን መመሪያ በጥንቃቄ ጠብቁ። #ዘሌ. 13፥1—14፥54። 9ከግብጽ ወጥታችሁ በጒዞ ላይ ሳላችሁ፥ አምላካችሁ እግዚአብሔር በማርያም ላይ ያደረገውን አስታውሱ። #ዘኍ. 12፥10።
10“ለአንድ ሰው አንዳች ነገር በምታበድርበት ጊዜ መያዣ ይሰጥህ ዘንድ ዘለህ ወደ ቤቱ አትግባ። 11አንተ ውጪ ቈይ፤ እርሱ ራሱ መያዣውን ያምጣልህ። 12ድኻ ከሆነ ደግሞ ልብሱን በመያዣነት ይዘህ አትደር። 13ለብሶት ያድር ዘንድ ፀሐይ ሳትጠልቅ መልስለት፤ እርሱም ያመሰግንሃል፤ በእግዚአብሔርም ዘንድ ጽድቅ ሆኖ ይቈጠርልሃል። #ዘፀ. 22፥26-27።
14“እስራኤላዊውም ሆነ ወይም ከአገርህ ከተማዎች በአንዱ የሚኖር የውጪ አገር ተወላጅ ድኻና ችግረኛ ሆኖ የተቀጠረውን ማናቸውንም ሰው አትበዝብዘው። 15እርሱ ድኻ በመሆኑ ያን ገንዘብ ለማግኘት በብርቱ ጒጉት ስለሚጠብቅ በየቀኑ የሠራበትን ገንዘብ ፀሐይ ከመጥለቅዋ በፊት ስጠው፤ ባትከፍለው ግን ወደ እግዚአብሔር በመጮኽ ያሳጣሃል፤ አንተም በደለኛ ሆነህ ትገኛለህ። #ዘሌ. 19፥13።
16“ልጆቻቸው በሠሩት ወንጀል ወላጆች በሞት መቀጣት የለባቸውም፤ ወላጆችም በፈጸሙት ወንጀል ልጆቻቸው በሞት አይቀጡ፤ እያንዳንዱ ሰው በሠራው ወንጀል በሞት ይቀጣ። #2ነገ. 14፥6፤ 2ዜ.መ. 25፥4፤ ሕዝ. 18፥20።
17“መጻተኞችና ወላጆቻቸው የሞቱባቸውን ልጆች ፍትሕ አትከልክላቸው፤ ስለ ብድርም መያዣ አድርገህ ባል የሞተባትን ሴት ልብስ አትውሰድ። 18እናንተም በግብጽ ባርያዎች እንደ ነበራችሁና አምላካችሁ እግዚአብሔር ነጻ እንዳወጣችሁ አስታውሱ፤ እኔም ይህን ትእዛዝ የምሰጣችሁ በዚህ ምክንያት ነው። #ዘፀ. 23፥9፤ ዘሌ. 19፥33-34፤ ዘዳ. 27፥19።
19“እህልህን በምትሰበስብበት ጊዜ የረሳኸው ነዶ ቢኖር እርሱን ለማምጣት ወደ ኋላ አትመለስ፤ እርሱ ለመጻተኞች፥ ወላጆቻቸው ለሞቱባቸው ልጆችና ባሎቻቸው ለሞቱባቸው መበለቶች ይቅርላቸው፤ ይህን ብታደርግ በምትሠራው ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ይባርክሃል። 20የወይራ ዛፍ ፍሬህንም አንድ ጊዜ ከለቀምክ በኋላ የቀረውን ፍሬ ለመውሰድ እንደገና ወደ እርሱ አትመለስ፤ እርሱን ለመጻተኞች፥ ወላጆቻቸው ለሞቱባቸው ልጆችና ባሎቻቸው ለሞቱባቸው ሴቶች ተውላቸው። 21የወይንህንም ዘለላ በምትሰበስብበት ጊዜ የቀረውን ፍሬ ለመውሰድ ወደ ወይኑ ሐረግ ዳግመኛ አትመለስ፤ የቀሩትን ዘለላዎች ለመጻተኞች፥ ወላጆቻቸው ለሞቱባቸው ልጆችና ባሎቻቸው ለሞቱባቸው ሴቶች ተውላቸው። #ዘሌ. 19፥9-10፤ 23፥22። 22አንተም በግብጽ ባሪያ እንደ ነበርክ አትርሳ፤ እኔም ይህን ትእዛዝ የሰጠሁህ በዚህ ምክንያት ነው።
Currently Selected:
ኦሪት ዘዳግም 24: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997