ኦሪት ዘዳግም መግቢያ
መግቢያ
ኦሪት ዘዳግም፥ የእስራኤል ሕዝብ ለብዙ ጊዜ በምድረ በዳ ከተጓዙ በኋላ ወደ ከነዓን ለመግባት ጥቂት ሲቀራቸው በሞአብ ምድር በቈዩበት ጊዜ ሙሴ በተከታታይ ያደረገላቸውን ንግግር የያዘ ነው።
በኦሪት ዘዳግም ተመዝግበው ከሚገኙት በጣም ጠቃሚ ከሆኑት ነገሮች መካከል አንዳንዶቹ የሚከተሉት ናቸው፦
1. ሙሴ ባለፉት አርባ ዓመቶች ውስጥ ስለ ተፈጸሙት ታላላቅ ድርጊቶች በማስታወስ ይናገራል፤ እግዚአብሔር በምድረ በዳ እንዴት እንደ መራቸው ሕዝቡን በማስታወስ፥ ለእግዚአብሔር ታማኞች እንዲሆኑና በቅንነት እንዲታዘዙት ያሳስባቸዋል።
2. ሙሴ ዐሥሩን ትእዛዞች እንደገና እየጠቀሰ በተለይ ስለ መጀመሪያው ትእዛዝ ፍች አብራርቶ እያስረዳ፥ ሕዝቡ እግዚአብሔርን ብቻ እንዲያመልኩ ያሳስባቸዋል፤ ከዚህም ጋር በማያያዝ እስራኤላውያን በተስፋይቱ ምድር ስለሚተዳደሩባቸው ልዩ ልዩ ሕጎች በድጋሚ እየጠቀሰ ያብራራል።
3. ሙሴ፥ እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር የገባው ቃል ኪዳን ምን ዐይነት እንደ ሆነ በመተርጐም፥ ሕዝቡ ለዚህ ቃል ኪዳን ያላቸውን ታማኝነት እንዲያድሱ ያስገነዝባቸዋል።
4. ኢያሱ በሙሴ እግር ተተክቶ የእግዚአብሔር ሕዝብ መሪ በመሆን ይሾማል፤ ሙሴ ስለ እግዚአብሔር ታማኝነት የተቀኘውን መዝሙር ከዘመረና የእስራኤልን ነገዶች በሙሉ ከባረከ በኋላ ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተ ምሥራቅ በሚገኘው በሞአብ ምድር ይሞታል።
የመጽሐፉ ዋና ርእስ እግዚአብሔር የሚወዳቸውንና የተመረጡ ሕዝቡን ስለ ማዳኑና ስለ መባረኩ ይናገራል፤ ሕዝቡም የእግዚአብሔር በረከት ሳይለያቸው በሕይወት መኖር ይችሉ ዘንድ እግዚአብሔር ያደረገላቸውን ሁሉ በማስታወስ ዘወትር እግዚአብሔርን መውደድና ለእርሱም መታዘዝ እንደሚገባቸው ያስገነዝባል።
የመጽሐፉን ዋና ሐሳብ የያዙ ጥቅሶች በዚሁ መጽሐፍ 6፥4-6 ያሉት ሲሆኑ፥ እነርሱም ኢየሱስ “ከትእዛዞች ሁሉ የምትበልጠው ታላቂቱ ትእዛዝ” ብሎ የተናገራቸውን ቃላት የያዙ ናቸው። እነዚህም፦ “እግዚአብሔር አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህ፥ በፍጹም ኀይልህ ውደድ።”
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
ሀ. የመጀመሪያው የሙሴ ንግግር 1፥1—4፥49
ለ. ሁለተኛው የሙሴ ንግግር 5፥1—26፥19
1. ዐሥሩ ትእዛዞች 5፥1—10፥22
2. ሕጎች፥ ደንቦችና ማስጠንቀቂያዎች 11፥1—26፥19
ሐ. ወደ ከነዓን ከመግባታቸው በፊት የተሰጠ መመሪያ 27፥1—28፥68
መ. የቃል ኪዳኑ መታደስ 29፥1—30፥20
ሠ. የሙሴ የመጨረሻው ንግግር 31፥1—33፥29
ረ. የሙሴ ሞት 34፥1-12
Currently Selected:
ኦሪት ዘዳግም መግቢያ: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997