ኦሪት ዘኊልቊ 36
36
ላገቡ ሴቶች የተመደበ ርስት
1የዮሴፍ ልጅ ምናሴ የወለደው የማኪር ልጅ የገለዓድ ጐሣ የሆኑት የቤተሰብ አለቆች ወደ ሙሴና ወደ ሌሎቹም የእስራኤል ሕዝብ አለቆች ቀርበው እንዲህ አሉ፤ 2“ምድሪቱን በዕጣ ለእስራኤል ሕዝብ እንድታከፋፍል እግዚአብሔር አንተን ጌታችንን አዞሃል፤ እንዲሁም የዘመዳችንን የጸሎፍሐድን ድርሻ ለሴቶች ልጆቹ እንድትሰጥ አዞሃል፤ 3ነገር ግን እነርሱ ከሌላ ነገድ የሆኑ ወንዶችን ቢያገቡ ርስታቸው የዚያ ነገድ መሆን እንደሚገባውና የእኛም ድርሻ ሊቀነስ እንደሚችል አስታውስ። 4ንብረት በሚመለስበት ዓመት የተሸጠ ንብረት ሁሉ ለባለቤቱ በሚመለስበት ጊዜ የጸሎፍሐድ ሴቶች ልጆች ርስት አግብተው ወደ ሄዱበት ነገድ ለዘለቄታው ተጨማሪ ሆኖ ይተላለፋል፤ ይህም በእኛ ነገድ ይዞታ ላይ ጒድለትን ያስከትላል።”
5ስለዚህ ሙሴ ለእስራኤል ሕዝብ ከእግዚአብሔር የተቀበለውን ትእዛዝ እንዲህ ሲል አስተላለፈ፤ “የምናሴ ነገድ የተናገሩት ሁሉ ትክክል ነው፤ 6ስለዚህ እግዚአብሔር ‘የጸሎፍሐድ ሴቶች ልጆች ከገዛ ነገዳቸው ወገን እስከ ሆነ ድረስ የወደዱትን ማግባት ይችላሉ’ ይላል። 7በዚህ ዐይነት የማንኛውም እስራኤላዊ ርስት ወደ ሌላ ነገድ አይተላለፍም፤ ከገዛ ነገዱ ጋር የተያያዘ ይሆናል፤ 8በእስራኤላዊ ነገድ መካከል ርስት የተካፈለች ማንኛይቱም ሴት ከዚያው ነገድ የሆነ ወንድ ማግባት ይኖርባታል፤ በዚህ ዐይነት እያንዳንዱ እስራኤላዊ የቀድሞ አባቶቹን ርስት በይዞታው ማቈየት ይችላል።” 9ስለዚህ ያም ርስት ከአንዱ ነገድ ወደ ሌላው ነገድ ሊተላለፍ አይቻልም፤ እያንዳንዱ ነገድ የራሱን ርስት እንደ ያዘ ይኖራል።
10የጸሎፍሐድ ሴቶች ልጆች እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው አደረጉ። 11የጸሎፍሐድ ሴቶች ልጆች ማሕላ፥ ቲርጻ፥ ሖግላ፥ ሚልካ እና ኖዓ ከአባታቸው ወንድሞች ልጆች ጋር ተጋቡ። 12ከዮሴፍ ልጅ ከምናሴ ነገድ ጐሣዎች መካከል ባሎችን አገቡ፤ ርስታቸውም በአባታቸው ነገድ የጸና ሆነ።
13ለእስራኤላውያን በኢያሪኮ ትይዩ ከዮርዳኖስ ወንዝ ባሻገር ባለው በሞአብ ሜዳ ላይ በነበሩበት ጊዜ እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት የሰጣቸው ትእዛዞችና ሥርዓቶች እነዚህ ናቸው።
Currently Selected:
ኦሪት ዘኊልቊ 36: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997