ኦሪት ዘኊልቊ 35
35
ለሌዋውያን የተመደቡ ከተሞች
1በኢያሪኮ ትይዩ ከዮርዳኖስ ወንዝ ማዶ ባለው በሞአብ ሜዳ ላይ እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ 2“እስራኤላውያን ድርሻቸው ከሆነ ርስት ለሌዋውያን የሚኖሩባቸውን ከተሞችንና በከተሞቹም ዙሪያ የግጦሽ መሬት እንዲሰጡአቸው ንገር። 3እነዚህም ከተሞች የሌዋውያን ይዞታ ሆነው እነርሱ ይኖሩባቸዋል፤ የግጦሽ መሬቱም ለከብቶቻቸውና ለሌሎች እንስሶቻቸው ይሆናል። 4የግጦሽ መሬቱ ከከተማው ቅጽር ግንብ በሁሉ አቅጣጫ እስከ አራት መቶ ኀምሳ ሜትር ይስፋ። 5በዚህም ዐይነት ከተማው በመካከል ሆኖ በአራቱም አቅጣጫ ከማእዘን እስከ ማእዘን የሚኖረው ርቀት ዘጠኝ መቶ ሜትር ይሆናል። 6ማናቸውም ሰው፥ በስሕተት ሰውን ቢገድል ሸሽቶ የሚጠጋባቸው ስድስት ከተሞችን ለሌዋውያን ትሰጣላችሁ፤ በተጨማሪም አርባ ሁለት ከተሞችን፥ 7ከነግጦሽ መሬታቸው ትሰጣላችሁ፤ በዚህም ዐይነት በአጠቃላይ አርባ ስምንት ከተሞች ይኖራቸዋል። 8ከእስራኤላውያን ይዞታ እንደየርስታቸው መጠን፥ ብዛት ካላቸው ነገዶች ብዙ ከተሞችን፥ አነስ ካሉ ነገዶች ጥቂት ከተሞችን ወስደህ ለሌዋውያን ስጥ።” #ኢያሱ 21፥1-42።
የመማጠኛ ከተሞች
(ዘዳ. 19፥1-13፤ ኢያሱ 20፥1-9)
9እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ 10“ለእስራኤላውያን እንዲህ በላቸው፦ የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻግራችሁ ወደ ከነዓን ምድር ስትገቡ፥ 11አንድ ሰው ባለማወቅ ተሳስቶ ሰው ቢገድል አምልጦ የሚደበቅበት የመማጠኛ ከተሞችን ምረጥ። 12በዚያም የበቀል እርምጃ ለመውሰድ ከሚፈልግ ከሟቹ ዘመድ ሊሰወር ይችላል፤ በግድያ ወንጀል የተከሰሰ ሰው ለፍርድ ሳይቀርብ መገደል የለበትም፤ 13ስድስት ከተሞችን ምረጡ፤ 14ከእነርሱም ሦስቱ ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተምሥራቅ፥ ሦስቱ ደግሞ በከነዓን ምድር ይሁኑ፤ 15እነርሱም ለእስራኤላውያንና ለጊዜውም ሆነ ለዘለቄታው በእስራኤል ለሚኖሩ መጻተኞች የመማጠኛ ከተሞች ይሆናሉ፤ ባለማወቅ ተሳስቶ ሰው የሚገድል ማንኛውም ግለሰብ ከእነርሱ ወደ አንዱ አምልጦ መጠጋት ይችላል።
የነፍስ ግድያ በቀል
16“አንድ ሰው ሌላውን ሰው በብረት መሣሪያ እስኪሞት ድረስ ቢመታው ያ ሰው ነፍሰ ገዳይ ነው፤ ነፍሰ ገዳዩም ይገደል። 17አንድ ሰው ሌላውን ሰው ሊገድል በሚችል ድንጋይ ቢመታውና ያ የተመታው ሰው ቢሞት ያ የመታው ሰው ነፍሰ ገዳይ ነው፤ ነፍሰ ገዳዩም ይገደል፤ 18አንድ ሰው ሌላውን ሰው ሊገድል በሚችል የእንጨት መሣሪያ መትቶ ቢገድለው ያ ሰው ነፍሰ ገዳይ ነው፤ ነፍሰ ገዳዩም ይገደል። 19የሟቹ ቅርብ ዘመድ ነፍሰ ገዳዩን የመግደል መብት ይኖረዋል፤ ስለዚህ ባገኘው ጊዜ ሊገድለው ይችላል።
20“አንድ ሰው ሌላውን ሰው በጥላቻ ቢገፋው ወይም ሸምቆ አንዳች ነገር ቢወረውርበትና ይህ አድራጎቱ ሞትን ቢያስከትል፥ 21ወይም በጠላትነት ተነሣሥቶ በቡጢ በመምታት ቢገድለው የግድያ ወንጀል ስለ ፈጸመ መገደል አለበት፤ የሟች ቅርብ ዘመድ ነፍሰ ገዳዩን የመግደል መብት ይኖረዋል፤ ስለዚህ ባገኘው ጊዜ ሊገድለው ይችላል።
22“ነገር ግን አንድ ሰው ገፍትሮ በመጣልም ሆነ አንዳች ነገር በላዩ በመወርወር ሌላ ሰው የሚገድለው ከጥላቻ የተነሣ ሳይሆን በድንገት ተሳስቶ ከሆነ፤ 23ወይም ጠላትነት ሳይኖርና ሰውን ለመጒዳት ታስቦ ሳይሆን ሞትን የሚያስከትል ድንጋይ ወርውሮ ሳይታሰብ በሌላ ሰው ላይ ቢያርፍና ሞትን ቢያስከትል፥ 24እንዲህ ያለው ሁኔታ በሚፈጸምበት ጊዜ ማኅበሩ በገዳዩና በተበቃዩ መካከል ፍርድ የሚሰጠው በሚከተለው ሥርዓት መሠረት ነው። 25ማኅበሩ በግድያ ወንጀል የተከሰሰውን ሰው ከተበቃይ እጅ በመታደግ አምልጦ ወደነበረበት ወደ መማጠኛ ከተማዋ መመለስ አለበት፤ በዘመኑ ሊቀ ካህናት የሆነው ሰው እስከሚሞትበት ድረስ እዚያው መቈየት ይኖርበታል። 26በግድያ ወንጀል የተከሰሰው ሰው አምልጦ ከመማጸኛው ከተማ ለቆ ከሄደ፥ 27የሟች ዘመድ አግኝቶ ከገደለው የዚህ ዐይነቱ የበቀል እርምጃ በነፍሰ ገዳይነት አያስጠይቅም። 28በግድያ ወንጀል የተከሰሰው ሰው ሊቀ ካህናቱ እስኪሞት ድረስ በዚያው በመማጸኛ ከተማ መቈየት አለበት፤ ሊቀ ካህናቱ ከሞተ በኋላ ግን ወደ ቤቱ መመለስ ይችላል፤ 29ይህ ሕግና ሥርዓት በምትኖሩበት አገር ሁሉ ለእናንተና ለዘሮቻችሁ መመሪያ ይሆናል።
30“በግድያ ወንጀል የተከሰሰ ማንኛውም ሰው የሞት ፍርድ ሊበየንበት የሚችለው ሁለት ወይም ከሁለት በላይ የሆኑ ሰዎች የመሰከሩበት እንደ ሆነ ነው፤ የአንድ ሰው ምስክርነት ግን ለግድያ ወንጀል የተከሰሰውን ሰው ሊያስጠይቀው አይችልም። #ዘዳ. 17፥6፤ 19፥15፤ ዘኍ. 27፥7። 31ማንኛውም ነፍሰ ገዳይ በሞት መቀጣት አለበት፤ ገንዘብ በመክፈል ከዚህ ቅጣት ሊያመልጥ አይችልም። 32አንድ ሰው ወደ መማጸኛ ከተማ ሸሽቶ ቢያመልጥ ሊቀ ካህናቱ ከመሞቱ በፊት ወደ ቤቱ መመለስ ይችል ዘንድ ገንዘብ እንዲከፍል አትፍቀዱለት። 33ይህን ብታደርጉ የምትኖሩበትን ምድር ታረክሳላችሁ፤ የነፍስ ግድያ ወንጀል ምድሪቱን ያረክሳል፤ ስለዚህ የነፍሰ ገዳዩ ደም ካልፈሰሰ በቀር ምድሪቱን ከደም ለማንጻት የሚፈጸም ሌላ ሥርዓት የለም። 34እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ስለ ሆንኩና በእናንተ በእስራኤል ሕዝብም መካከል ስለምኖር የእኔ መኖሪያ የሆነውንና እናንተ የምትኖሩበትን ምድር አታርክሱ።”
Currently Selected:
ኦሪት ዘኊልቊ 35: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997