ኦሪት ዘኊልቊ 34
34
የምድሪቱ አዋሳኞች
1እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ 2“እስራኤላውያንን እንዲህ ብለህ እዘዝ፦ እኔ ወደምሰጣችሁ ወደ ከነዓን ምድር በምትገቡበት ጊዜ የርስታችሁ ወሰን እንደሚከተለው ይሆናል፦ 3የደቡብ ድንበር ከጺን ምድረ በዳ ተነሥቶ የኤዶምን ጠረፍ እያዋሰነ ያልፋል፤ ይኸውም በስተ ምሥራቅ በኩል የሚጀምረው ከሙት ባሕር በስተ ደቡብ ጫፍ ላይ ነው። 4ከዚያም ወደ ዐቅራቢም መተላለፊያ ወደ ደቡብ በማምራት በጺን አልፎ እስከ ቃዴስ በርኔ ይደርሳል፤ ከዚያም በሐጻርአዳር ሰሜናዊ ምዕራብ አልፎ እስከ ዓጽሞን ይደርሳል። 5ከዓጽሞን ተነሥቶ የግብጽን ሸለቆ በመዞር በሜዲትራኒያን ባሕር ይቆማል።
6“የምዕራቡ ወሰን የሜድትራኒያን ባሕር ጠረፍ ይሆናል።
7“የሰሜኑ ወሰን የሜዲቴራኒያንን ባሕር በመከተል እስከ ሖር ተራራ ይሆናል፤ 8ከሖርም ተራራ ወደ ሐማት መግቢያ ምልክት ይደርሳል፤ የድንበሩም መጨረሻ ጸዳድ ይሆናል። 9ወደ ዚፍሮን ከተሻገረም በኋላ በሐጻርዔናን ይቆማል፤ ይህም የሰሜን ድንበራችሁ ይሆናል።
10“የምሥራቁ ወሰናችሁን ከሐጻርዔናን እስከ ሸፋም ምልክት ታደርጋላችሁ 11ወሰኑም ከሴፋም ተነሥቶ ከዓይን በስተምሥራቅ በኩል ወደ ሪብላ ይቀጥልና በገሊላ ባሕር በስተ ምሥራቅ ወዳሉት ኮረብታዎች ይደርሳል። 12ወሰኑም ወደ ዮርዳኖስ ይወርዳል፤ መጨረሻውም የሙት ባሕር ይሆናል። እነዚህም የምድራችሁ ዙሪያ አዋሳኞች ይሆናሉ።”
13ሙሴ እስራኤላውያንን እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፦ “ለዘጠኝ ተኩል ነገዶች እንዲሰጥ እግዚአብሔር ያዘዘው በዕጣ የምትካፈሉት ርስት ይህ ነው። 14የሮቤልና የጋድ ነገዶች፥ እንዲሁም የምናሴ ነገድ እኩሌታ በየቤተሰባቸው በመከፋፈል፥ 15በዮርዳኖስ ማዶ ከኢያሪኮ በስተምሥራቅ፥ በፀሐይ መውጫ በኩል ርስታቸውን ተቀብለዋል።” #ኢያሱ 14፥1-5።
ምድሪቱን ለማከፋፈል ኀላፊነት የተሰጣቸው መሪዎች
16እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ 17“ካህኑ አልዓዛርና የነዌ ልጅ ኢያሱ ምድሪቱን በሕዝቡ መካከል ያከፋፍሉ፤ 18ምድሪቱን ለማከፋፈል ይረዱ ዘንድ ከየነገዱ አንድ አንድ መሪ ውሰድ።” 19የሰዎቹም ስም ይህ ነው፤ ከይሁዳ ነገድ የይፉኔ ልጅ ካሌብ፥ 20ከስምዖን ነገድ የአሚሁድ ልጅ ሰላሚኤል፥ 21ከብንያም ነገድ የኪስሎን ልጅ ኤልዳድ፥ 22ከዳን ነገድ የዮግሊ ልጅ ቡቂ፥ 23ከዮሴፍ ልጆች፥ ከምናሴ ነገድ የሱፊድ ልጅ አኒኤል፥ 24ከኤፍሬም ነገድ የሺፍጣን ልጅ ቀሙኤል፥ 25ከዛብሎን ነገድ የፈርናክ ልጅ ኤሊሳፈን፥ 26ከይሳኮር ነገድ የሖዛ ልጅ ፖልቲኤል፥ 27ከአሴር ነገድ የሴሌሚ ልጅ አሒሁድ፥ 28ከንፍታሌም ነገድ የአሚሁድ ልጅ ፔዳሄል፥
29እንግዲህ ለእስራኤል ሕዝብ በከነዓን ምድር ርስት እንዲያካፍሉ እግዚአብሔር የመረጣቸው ሰዎች እነዚህ ናቸው።
Currently Selected:
ኦሪት ዘኊልቊ 34: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997