ኦሪት ዘጸአት 20
20
ዐሥሩ ትእዛዞች
(ዘዳ. 5፥1-21)
1እግዚአብሔር እነዚህን ትእዛዞች ሁሉ ለሕዝቡ ተናገረ፥ 2“የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! በባርነት ከምትኖርባት ከግብጽ ምድር ያወጣሁህ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ነኝ፤
3“ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ አታምልክ፤
4“በሰማይም ሆነ በምድር ወይም ከምድር በታች ባለው ውሃ ውስጥ ከሚኖሩት ነገሮች የማንኛውንም ዐይነት ምስል ጣዖት አድርገህ አትሥራ፤ 5እኔ እግዚአብሔር አምላክህ እጅግ ቀናተኛ ስለ ሆንኩ ተቀርጾ የተሠራውን ማንኛውም ጣዖት አታምልክ፤ አትስገድለትም፤ እኔ የሚጠሉኝን ሁሉ እቀጣለሁ፤ ዘራቸውንም ሁሉ እስከ ሦስትና አራት ትውልድ ድረስ እበቀላለሁ። #ዘፀ. 34፥17፤ ዘሌ. 19፥4፤ 26፥1፤ ዘዳ. 4፥15-18፤ 27፥15። 6ለሚወዱኝና ትእዛዞቼን ለሚጠብቁ ሁሉ ግን እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ ዘለዓለማዊ ፍቅሬን አሳያቸዋለሁ። #ዘፀ. 34፥6-7፤ ዘኍ. 14፥18፤ ዘዳ. 7፥9-10።
7“የአምላክህን የእግዚአብሔርን ስም በከንቱ አታንሣ፤ እግዚአብሔር ስሙን በከንቱ የሚያነሣውን ሁሉ ሳይቀጣው አያልፍም። #ዘሌ. 19፥12።
8“የሰንበትን ቀን አክብር፤ ቀድሰውም፤ #ዘፀ. 16፥23-30። 9ሥራህን ሁሉ የምታከናውንባቸው ስድስት ቀኖች አሉልህ፤ 10ሰባተኛው ቀን ግን ለአምላክህ ለእግዚአብሔር የዕረፍት ቀን ነው፤ በዚያን ቀን ማንም ሰው ሥራ አይሥራ፤ አንተም ሆንክ ልጆችህ፥ አገልጋዮችህም ሆኑ እንስሶችህ፥ በአገርህ ውስጥ የሚኖሩ መጻተኞችም ቢሆኑ ምንም ሥራ አትሥሩበት። #ዘፀ. 23፥12፤ 31፥15፤ 34፥21፤ 35፥2፤ ዘሌ. 23፥3። 11በስድስት ቀን እግዚአብሔር ሰማይን፥ ምድርን፥ ባሕርንና በእነርሱ ውስጥ ያሉትን ነገሮች ሁሉ ፈጥሮ በሰባተኛው ቀን ዐረፈ፤ ስለዚህም እግዚአብሔር ሰባተኛውን ቀን ባረከው፤ ቀደሰውም። #ዘፍ. 2፥1-3፤ ዘፀ. 31፥17።
12“አባትህንና እናትህን አክብር፤ ይህን ብታደርግ እኔ በምሰጥህ ምድር የረዥም ዘመን ዕድሜ ይኖርሃል። #ዘዳ. 27፥16፤ ማቴ. 15፥4፤ 19፥19፤ ማር. 7፥10፤ 10፥19፤ ሉቃ. 18፥20፤ ኤፌ. 6፥2-3።
13“አትግደል፤
14“አታመንዝር፤ #ዘሌ. 20፥10፤ ማቴ. 5፥27፤ 19፥18፤ ማር. 10፥19፤ ሉቃ. 18፥20፤ ሮም 13፥9፤ ያዕ. 2፥11።
15“አትስረቅ፤ #ዘሌ. 19፥11፤ ማቴ. 19፥18፤ ማር. 10፥19፤ ሉቃ. 18፥20፤ 13፥8።
16“በማንም ሰው ላይ በሐሰት አትመስክር፤ #ዘፀ. 23፥1፤ ማቴ. 19፥18፤ ማር. 10፥19፤ ሉቃ. 18፥20።
17“የሌላውን ሰው ቤት አትመኝ፤ ሚስቱን፥ አገልጋዮቹን፥ ከብቱን፥ አህዮቹንም ሆነ ማናቸውንም ንብረቱን ሁሉ አትመኝ።” #ሮም 7፥7፤ 13፥9።
የሕዝቡ ፍርሀት
(ዘዳ. 5፥22-33)
18ሕዝቡም የነጐድጓዱንና የእምቢልታውን ድምፅ በሰሙ ጊዜ፥ እንዲሁም መብረቁ ሲብለጨለጭና ተራራው ሲጤስ ባዩ ጊዜ በፍርሃት በመንቀጥቀጥ ርቀው ቆሙ፤ 19እነርሱም ሙሴን “አንተ ተናገረን፤ እናዳምጥሃለን፤ እግዚአብሔር ቢናገረን ግን እንሞታለን ብለን እንፈራለን” አሉት። #ዕብ. 12፥18-19።
20ሙሴም “አይዞአችሁ፥ አትፍሩ፤ እግዚአብሔር በዚህ ሁኔታ ወደ እናንተ የመጣው ሊፈትናችሁና እርሱን በመፍራት ኃጢአት ከመሥራት ርቃችሁ እንድትኖሩ ነው” ሲል መለሰላቸው። 21ሕዝቡ ግን ርቀው ቆሙ፤ ሙሴ ብቻውን እግዚአብሔር ወዳለበት ጥቅጥቅ ወደ ሆነው ደመና ተጠጋ።
ስለ መሠዊያዎች የተሰጡ ሕጎች
22እግዚአብሔር ሙሴን ለእስራኤላውያን እንዲነግር እንዲህ ሲል አዘዘው፥ “እኔ እግዚአብሔር ከሰማይ እንዴት እንደ ተናገርኳችሁ አይታችኋል፤ 23እኔን ብቻ አምልኩ እንጂ፥ ከብርና ከወርቅ ጣዖቶች ሠርታችሁ አታምልኩ፤ 24ለእኔ ከጭቃ የተሠራ መሠዊያ አብጁልኝ፤ በእርሱም ላይ ከበጎቻችሁ፥ ከፍየሎቻችሁና ከከብቶቻችሁ መርጣችሁ የሚቃጠልና የአንድነት መሥዋዕት አድርጋችሁ ሠዉበት፤ ስሜ እንዲታሰብበት በወሰንኩት ስፍራ ሁሉ ወደ እናንተ መጥቼ እባርካችኋለሁ፤ 25ለእኔ የድንጋይ መሠዊያ ማበጀት ብትፈልጉ ከጥርብ ድንጋይ የተሠራ አይሁን፤ የብረት መሣሪያ ቢነካው ታረክሱታላችሁ፤ #ዘዳ. 27፥5-7፤ ኢያሱ 8፥31። 26ኀፍረተ ሥጋችሁ በእርሱ ላይ እንዳይገለጥ በመወጣጫ መሰላል አትውጡ።
Currently Selected:
ኦሪት ዘጸአት 20: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997