ኦሪት ዘጸአት 31
31
በጽልኤልና ኦሆሊአብ
(ዘፀ. 35፥30—36፥1)
1እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ 2“እነሆ፥ ከይሁዳ ነገድ የሑር የልጅ ልጅ የሆነውን የኡሪን ልጅ ባጽልኤልን በስም ጠርቼአለሁ። 3ማንኛውንም የእጅ ጥበብ መሥራት እንዲችል ማስተዋልና ብልኀት የማወቅም ችሎታ ይኖረው ዘንድ በመንፈሴ እንዲሞላ አድርጌአለሁ፤ 4ስለዚህም በብልኀት የሥራ ዕቅድ እያወጣ ከወርቅ፥ ከብርና ከነሐስ ልዩ ልዩ ነገሮችን ይሠራል። 5እንዲሁም ለፈርጥ የሚሆነውን ድንጋይ ለመቅረጽ፥ እንጨትንም ለመጥረብ፥ ሌላውንም ሥራ ሁሉ በጥበብ ለማከናወን እንዲችል አድርጌዋለሁ። 6ከእርሱም ጋር እንዲሠራ ከዳን ነገድ የአሒሳማክን ልጅ ኦሆሊአብን መርጬአለሁ፤ እኔ ያዘዝኩህን ነገር ሁሉ እንዲሠሩ ሌሎችም የእጅ ጥበብ ዐዋቂዎች ሁሉ ታላቅ ችሎታ እንዲኖራቸው አድርጌአለሁ። 7እንዲሠራ ያዘዝኩትም ይህ ነው፤ የመገናኛው ድንኳን፥ የቃል ኪዳኑ ታቦትና መክደኛው፥ የድንኳኑ መገልገያ ዕቃዎች ሁሉ፥ 8ጠረጴዛውና ለእርሱ የሚያስፈልገው ዕቃ፥ የጠራ መቅረዝና ለእርሱ የሚያስፈልገው ነገር ሁሉ፥ የዕጣን መሠዊያው፥ 9ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚሆነው መሠዊያና ለእርሱ የሚያስፈልገው ነገር ሁሉ፥ የመታጠቢያው ሳሕንና ማስቀመጫው፥ 10አሮንና ልጆቹ በክህነት አገልግሎት ላይ ሲሆኑ የሚጠቀሙባቸው የተዋቡ አልባሳት፥ 11የቅባቱ ዘይትና ለተቀደሰው ስፍራ የሚሆነው መዓዛው ጣፋጭ የሆነ ዕጣን፤ ልክ እኔ አንተን ባዘዝኩት ዐይነት እነዚህን ሁሉ ነገሮች ይሠራሉ።”
ሰንበት
12እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ ብሎ አዘዘው፤ 13“ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ እኔ እግዚአብሔር እናንተን ለእኔ የተለየ ሕዝብ አድርጌ የመረጥኳችሁ መሆኔን የሚያሳይ ሆኖ በሚመጡት ዘመናት ሁሉ በእኔና በእናንተ መካከል ጸንቶ የሚኖር ምልክት ስለ ሆነ የዕረፍት ቀን አድርጌ የመረጥኩትን ሰንበትን ጠብቁ፤ 14የተቀደሰ ስለ ሆነ ሰንበትን የዕረፍት ቀን አድርጋችሁ ጠብቁት፤ ይህን የሰንበት ቀን የማይጠብቅና የሥራ ቀን አድርጎ የሚጠቀምበት ሁሉ ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ ይጥፋ። 15ሥራችሁን ሁሉ የምታከናውኑባቸው ስድስት የሥራ ቀኖች አሉላችሁ፤ ሰባተኛው ቀን ግን ለእኔ ተለይቶ የተቀደሰ የዕረፍት ቀን ነው፤ በዚህ ቀን ሥራ የሚሠራበት ሁሉ በሞት ይቀጣ። #ዘፀ. 20፥8-11፤ 23፥12፤ 34፥21፤ 35፥2፤ ዘሌ. 23፥3፤ ዘዳ. 5፥12-14። 16የእስራኤል ሕዝብ ለሚመጣው ትውልድ ሁሉ ይህ ቀን ጸንቶ የሚኖር የቃል ኪዳን ምልክት አድርገው ይጠብቁት፤ 17እኔ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን በስድስት ቀኖች ውስጥ ከፈጠርኩ በኋላ ሰባተኛው ቀን ሥራዬን አቁሜ ያረፍኩበት ስለ ሆነ በእኔና በእስራኤል ሕዝብ መካከል ለዘለዓለም ጸንቶ የሚኖር ምልክት ይሁን።” #ዘፀ. 20፥11።
18እግዚአብሔር ሙሴን በሲና ተራራ ላይ ማነጋገሩን ከፈጸመ በኋላ በእግዚአብሔር ጣት በድንጋይ ላይ የተጻፈባቸውን ሁለቱን የቃል ኪዳን ጽላቶች ሰጠው።
Currently Selected:
ኦሪት ዘጸአት 31: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997