ኦሪት ዘጸአት 30
30
የዕጣን መሠዊያ
(ዘፀ. 37፥25-28)
1“ለሚጤስ ዕጣን የሚያገለግል መሠዊያ ከግራር እንጨት ሥራ፤ 2ርዝመቱ አርባ አምስት ሳንቲ ሜትር የጐኑ ስፋት አርባ አምስት ሳንቲ ሜትር ከፍታውም ዘጠና ሳንቲ ሜትር ሆኖ የተስተካከለ አራት ማእዘን ይሁን። በአራቱም ማእዘን ያሉት ጒጦች ከእርሱ ጋር አንድ ወጥ ይሁኑ፤ 3የመሠዊያውን ጫፍ፥ አራት ጐኖቹንና ጒጦቹን ሁሉ በንጹሕ ወርቅ ለብጠው፤ የወርቅ ክፈፍም አብጅለት። 4ሁለት የወርቅ ቀለበቶችን ሠርተህ መሠዊያውን ለመሸከም የሚያገለግሉት መሎጊያዎች እንዲገቡበት ከክፈፉ ሥር አያይዛቸው። 5መሎጊያዎችንም ከግራር እንጨት ሠርተህ በወርቅ ለብጣቸው። 6ይህንንም መሠዊያ ከቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት ለፊት ከተሰቀለው መጋረጃ ውጪ አኑረው፤ እኔም በዚያ ለአንተ እገለጥልሃለሁ፤ 7አሮን በየማለዳው መብራቶችን ለማዘጋጀት በሚመጣበት ጊዜ መልካም መዓዛ ያለውን ዕጣን በመሠዊያው ላይ ይጠን። 8በየምሽቱም መብራቶቹን ሲያበራ እንዲሁ ያድርግ፤ ይህ የዕጣን መባ አቀራረብ በሚመጡት ዘመናት ሁሉ ባለማቋረጥ የሚቀጥል መሆን አለበት። 9በዚህ መሠዊያ ላይ ማናቸውም የተከለከለ ዕጣን፥ የእንስሳ መሥዋዕት፥ ወይም የእህል ቊርባን አታቅርብ፤ የወይን ጠጅ መባም አታፍስስበት። 10አሮን በዓመት አንድ ጊዜ ለኃጢአት ስርየት መሥዋዕት ከታረደው እንስሳ ደም ወስዶ በአራቱም ጒጦች ላይ በማድረግ መሠዊያው የሚነጻበትን ሥርዓት ይፈጽም፤ ይህም ሥርዓት በሚመጡት ዘመናት ሁሉ በየዓመቱ ይፈጸም፤ በዚህ ዐይነት ይህ መሠዊያ ለእግዚአብሔር በፍጹም የተቀደሰ ይሁን።”
የቤዛነት ክፍያ
11እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ 12“የእስራኤልን ሕዝብ በምትቈጥርበት ጊዜ በሕዝብ ቈጠራው ወቅት መቅሠፍት እንዳይደርስባቸው እያንዳንዱ ሰው ለሕይወቱ ቤዛ የሚሆን ዋጋ ይክፈል። 13ከሕዝብ ቈጠራ ውስጥ የሚገባ እያንዳንዱ ሰው በተቀደሰው ድንኳን በታወቀው ሚዛን ልክ አንድ ጥሬ ብር ይክፈል፤ እያንዳንዱ ሰው ይህን ለእግዚአብሔር መባ አድርጎ ያቅርብ፤ #ዘፀ. 38፥25-26፤ ማቴ. 17፥24። 14ከሕዝብ ቈጠራው ለመግባት ዕድሜው የፈቀደለት፥ ማለትም ኻያ ዓመት የሞላውና ከዚያም በላይ የሆነ ሁሉ ይህን የእግዚአብሔር መባ ያቅርብ፤ 15ለሕይወታቸው ቤዛ ይህን መባ ሲያቀርቡ ሀብታሙም ሆነ ድኻው እኩል ይክፈል እንጂ የሀብታሙ ክፍያ ብዙ የድኻው ክፍያ አነስተኛ አይሁን። 16ይህን መባ ከእስራኤል ሕዝብ ሰብስበህ ለተቀደሰው ድንኳን መንከባከቢያ እንዲውል አድርግ፤ ይህም መባ ለሕይወታቸው ቤዛ ይሆናል፤ እኔም እጠብቃቸው ዘንድ እነርሱን አስታውሳለሁ።”
ከነሐስ የተሠራ መታጠቢያ ሳሕን
17እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ 18“መታጠቢያ ገንዳ ከነሐስ ሠርተህ፥ እግሮች ባሉት ከነሐስ በተሠራ የሳሕን መቀመጫ ላይ አኑረው፤ እርሱንም በመሠዊያውና በድንኳኑ መካከል አድርገህ ውሃ ጨምርበት። #ዘፀ. 38፥8። 19አሮንና ልጆቹ በዚህ ውሃ እጃቸውንና እግራቸውን ለመታጠብ ይጠቀሙበት። 20ይህንንም ማድረግ ያለባቸው ወደ ድንኳኑ ከመግባታቸውና የሚቃጠል መሥዋዕት ከማቅረባቸው በፊት ነው፤ ይህንንም ካደረጉ ከሞት ይድናሉ፤ 21ስለዚህ እንዳይሞቱ እጃቸውንና እግራቸውን ይታጠቡ፤ ይህም እነርሱና ከእነርሱ በኋላ የሚነሡት ዘሮቻቸው ለዘለዓለም የሚጠብቁት ቋሚ ሥርዓት ነው።”
የቅባት ዘይት
22እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ አለው፦ 23“ምርጥ የሆኑ ቅመሞችን፥ ስድስት ኪሎ ግራም ፈሳሽ ከርቤ፥ ሦስት ኪሎ ግራም ጣፋጭ ሽታ ያለውን ቀረፋ፥ ሦስት ኪሎ ግራም ጣፋጭ ሽታ ያለውን የጠጅ ሣርና፥ 24ስድስት ኪሎ ግራም ብርጒድ ውሰድ ይህም ሁሉ በተቀደሰው ድንኳን በታወቀው ሚዛን ልክ ይሁን፤ በዚህም ላይ አራት ሊትር ዘይት ጨምርበትና፥ 25እንደ ሽቶ ቀላቅለህ የተቀደሰ የቅባት ዘይት ሥራ፤ 26በእርሱም የመገናኛውን ድንኳንና የቃል ኪዳኑን ታቦት ትቀባለህ፤ 27እንዲሁም ጠረጴዛውንና በእርሱ ላይ ያሉትን ዕቃዎች፥ መቅረዙንና የእርሱን ማዘጋጃ ዕቃዎች፥ የዕጣን ማዕጠንት ማቅረቢያውን መሠዊያ ትቀባለህ፤ 28ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚያገለግለውን መሠዊያና በላዩ ላይ ያሉትን ዕቃዎች ሁሉ፥ እንዲሁም የመታጠቢያውን ሳሕንና ማስቀመጫውን ትቀባለህ። 29በዚህ ዐይነት እነዚህን ሁሉ በመለየት ፍጹም የተቀደሱ ታደርጋቸዋለህ፤ እነርሱንም ፍጹም ቅዱሳን ስለ ሆኑ ሰውም ሆነ ሌላ ነገር ቢነካቸው ቅሥፈት ይደርስበታል። 30ከዚህ በኋላ አሮንና ልጆቹ በክህነት ያገለግሉኝ ዘንድ በመቀባት እንዲካኑ አድርግ፤ 31ለእስራኤልም ሕዝብ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፤ ‘ይህ የተቀደሰ የቅባት ዘይት ለሚመጡት ዘመናት ሁሉ ለእኔ አገልግሎት ይዋል፤ 32በማንኛውም ተራ ሰው ላይ አይፍሰስ፤ ይህንንም የመሰለ ቅባት ለመሥራት በዚህ ዘዴ ከመጠቀም ተጠንቀቁ፤ ቅዱስ ስለ ሆነ እናንተም ቅድስናውን ዕወቁ። 33ይህን የመሰለ ቅባት የሚሠራ ወይም ከዚህ ቅባት ወስዶ ካህን ያልሆነውን ሰው የሚቀባ ከሕዝቤ መካከል ይወገዳል።’ ”
የዕጣን ዝግጅት
34እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ “የእያንዳንዳቸው ሚዛን እኩል የሆነ ጣፋጭ ቅመሞችን ይኸውም የሚንጠባጠብ ፈሳሽነት ያለው ሙጫ፥ በዛጎል ውስጥ የሚገኝ ሽቱ፥ የሚሸት ሙጫና ጣፋጭ ሽታ ያለው ዕጣን ወስደህ፥ 35እንደ ሽቶ የተቀላቀለ ዕጣን አድርገህ ተጠቀምባቸው። ንጹሕና ቅዱስ ይሆንም ዘንድ ጨው ጨምርበት። 36ከእርሱም ጥቂቱን ወስደህ በመውቀጥ ካላምከው በኋላ ወደ ድንኳኑ ወስደህ በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት እርጨው፤ ይህንንም ዕጣን ፍጹም የተቀደሰ እንዲሆን አድርግ። 37በዚህ ዐይነት የምታደባልቁትን ዕጣን ለእግዚአብሔር የተቀደሰ አድርጉት እንጂ ለራሳችሁ መጠቀሚያ አታድርጉት። 38ይህን የመሰለ ነገር ሠርቶ በመዓዛው ሊደሰት የሚፈልግ ሰው ቢኖር፥ ከሕዝቤ መካከል ይወገዳል።” #ዘፀ. 37፥29።
Currently Selected:
ኦሪት ዘጸአት 30: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997