ትንቢተ ሕዝቅኤል 14
14
እግዚአብሔር የጣዖት አምልኮን መቃወሙ
1ከእስራኤላውያን መሪዎች አንዳንዶቹ የእኔን ምክር ለመጠየቅ መጥተው በፊቴ ተቀመጡ፤ 2በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ 3“የሰው ልጅ ሆይ! እነዚህ ሰዎች ልባቸውን ለጣዖቶች ሰጥተዋል፤ በደላቸው በፊታቸው እንቅፋት እንዲሆንባቸው አድርገዋል፤ ይህ ሁሉ ከሆነ በኋላ የእኔን ፈቃድ መጠየቃቸው ተገቢ ነውን?”
4ስለዚህ ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ብለህ ንገራቸው፦ “ከእስራኤል ሕዝብ መካከል ልባቸውን ለጣዖቶች የሰጡና የጣዖት አምልኮአቸው በፊታቸው ዕንቅፋት እንዲሆንባቸው ያደረጉ አሉ፤ እነዚህ ሰዎች ወደ ነቢዩ የሚመጡ ከሆነ እኔ እግዚአብሔር እንደ ጣዖቶች ብዛት ተገቢ መልስ እሰጣቸዋለሁ። 5ይህን የማደርገው እኔን ትተው ወደ ጣዖቶቻቸው በመሄድ ከእኔ ተለይተው የነበሩትን የእስራኤላውያንን ሁሉ ልብ ለመመለስ ነው።
6“ስለዚህ ለእስራኤል ሕዝብ እንዲህ በላቸው፦ ‘እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ጣዖቶቻችሁን ትታችሁ ንስሓ ግቡ! ከአጸያፊ ተግባራችሁም ሁሉ ተመለሱ!’
7“ከእስራኤላውያን አንዱ ወይም በእነርሱ መካከል ከሚኖሩ ባዕዳን ሰዎች አንዱ ከእኔ ተለይቶ ጣዖቶችን በማምለክ ኃጢአት የሚሠራ ቢሆን፥ በደሉም በፊቱ ዕንቅፋት እንዲሆንበት ቢያደርግና እንደገና ደግሞ ምክር ለመጠየቅ ወደ ነቢያት የሚመጣ ከሆነ እኔ እግዚአብሔር ራሴ መልስ እሰጠዋለሁ! 8እኔም በእርሱ ላይ አተኲሬ መቀጣጫና መዘባበቻ አደርገዋለሁ ከሕዝቤ መካከል አስወግደዋለሁ፤ ከዚያም እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ።
9“አንድ ነቢይ ተጠይቆ ሐሰተኛ መልስ ለመስጠት ቢነሣሣ እኔ እግዚአብሔር ያን እንዲያደርግ እተወዋለሁ። ይህንንም ካደረገ ከእግዚአብሔር ሕዝብ መካከል አጠፋዋለሁ። 10ነቢዩና ከእርሱ ምክር ለመጠየቅ የሚመጣው ሁለቱም ተመሳሳይ ቅጣት ይደርስባቸዋል። 11ይህንንም የማደርገው የእስራኤል ሕዝብ ወደ እኔ የሚያደርሰውን መንገድ ከእንግዲህ ወዲህ እንዳይስቱና በበደላቸው ሁሉ ዳግመኛ ራሳቸውን እንዳያረክሱ ነው፤ በዚህም ከጸኑ እኔ አምላካቸው እሆናለሁ። እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ፤” ይላል ልዑል እግዚአብሔር።
ኖኅ፥ ዳንኤልና ኢዮብ
12እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ 13“የሰው ልጅ ሆይ! የአንድ አገር ሕዝብ በእኔ ላይ እምነተ ቢስ ሆኖ ኃጢአት ቢሠራ የምግብ ምርቱን አቋርጬ በራብ እቀጣዋለሁ፤ ሰዎችንና እንስሶችን እገድላለሁ። 14እነዚያ ሦስት ሰዎች ማለትም ኖኅ፥ ዳንኤልና ኢዮብ በውስጥዋ ቢገኙ እንኳ በደግነታቸው ማትረፍ የሚችሉት የራሳቸውን ሕይወት ብቻ ነው፤ ይህን የተናገረ ጌታ እግዚአብሔር ነው።
15“በዚያች አገር አውሬ ሰድጄ ሰው አልባ እስከሚሆንና ማንም በዚያ በኩል ማለፍ እስከማይችል ድረስ አገሪቱን ባድማ አደርጋታለሁ። 16እኔ እግዚአብሔር ሕያው አምላክ እንደ መሆኔ እነዚያ ሦስት ሰዎች እንኳ በዚያ ቢኖሩ ከራሳቸው ሕይወት በቀር የገዛ ልጆቻቸውን እንኳ ማዳን አይችሉም፤ ምድሪቱም ወደ ምድረ በዳነት ትለወጣለች።
17“ወይም በዚያች አገር ጦርነትን አምጥቼ ሰዎችና እንስሶች በአጥፊ መሣሪያ እንዲወድሙ ባደርግ፥ 18እኔ እግዚአብሔር ሕያው አምላክ እንደ መሆኔ እነዚያ ሦስት ሰዎች እንኳ በዚያ ቢገኙ ከራሳቸው ሕይወት በቀር የገዛ ልጆቻቸውን እንኳ ማዳን አይችሉም፤ ይላል ልዑል እግዚአብሔር።
19“ወይም በዚያች አገር ቸነፈር በመስደድ በቊጣዬ የብዙ ሰዎችና እንስሶች ሕይወት እንዲጠፋ አደርጋለሁ። 20ስለዚህ እኔ እግዚአብሔር ሕያው አምላክ እንደ መሆኔ ኖኅ፥ ዳንኤልና ኢዮብ እንኳ በዚያ ቢኖሩ በጽድቃቸው የራሳቸውን ሕይወት ብቻ ያድናሉ እንጂ የገዛ ልጆቻቸውን እንኳ ማዳን አይችሉም”፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
21ልዑል እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፦ “ሕዝብንና እንስሶችን በአንድነት ለመጨረስ ጦርነትን፥ ራብን፥ አራዊትንና ቸነፈርን እነዚህን እጅግ የከፉ አራት መቅሠፍቶች በኢየሩሳሌም ላይ አመጣለሁ። #ራዕ. 6፥8። 22-23ሆኖም በኢየሩሳሌም ውስጥ ከእርስዋ ወደ እናንተ የሚመጡ ቅሬታዎች ይቀሩላታል፤ አካሄዳቸውንና ተግባራቸውን በምታዩበት ጊዜ የእነርሱን ሁኔታ ትረዳላችሁ፤ እናንተም በእነርሱ ላይ ያደረስኩት መቅሠፍት ሁሉ ያለምክንያት እንዳልሆነ ታውቃላችሁ።” ይላል ልዑል እግዚአብሔር።
Currently Selected:
ትንቢተ ሕዝቅኤል 14: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997