የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትንቢተ ሕዝቅኤል 15

15
ስለ ወይን ተክል የቀረበ ምሳሌ
1እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ 2“የሰው ልጅ ሆይ! የወይን ግንድ ከሌሎች ዛፎች ግንድ ቅርንጫፎች ከዱር ዛፎች ቅርንጫፍ በምን ይበልጣል? 3አንድ ነገር እንኳ ለመሥራት ይጠቅማልን? የዕቃ መስቀያ ኩላብ እንኳ ከእርሱ ሊሠራ ይችላልን? 4የእሳት ማቀጣጠያ ከመሆን በቀር ሌላ ጥቅም የለውም፤ ጫፎቹ ነደው መካከሉ ካረረ በኋላ በእርሱ አንድ ነገር እንኳ መሥራት ይቻላልን? 5ከመቃጠሉ በፊት እንኳ ዋጋቢስ ከነበረ አሁንማ እሳቱ ካቃጠለውና ካሳረረው በኋላ የባሰውን ጥቅም የሌለው ይሆናል።”
6ስለዚህ ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በዱር ካሉ ዛፎች መካከል የወይንን ግንድ ለማገዶ እንዳደረግሁት የኢየሩሳሌምን ሕዝብ እንዲሁ አደርገዋለሁ። 7እቈጣቸዋለሁ፤ ምንም እንኳ ለጊዜው ከእሳቱ ቢያመልጡ እሳቱ ግን ይበላቸዋል፤ እነርሱንም በምትቈጣበት ጊዜ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ። 8እነርሱ በእኔ መታመናቸውን ትተዋል፤ እኔም አገራቸው ምድረ በዳ እንድትሆን አደርጋለሁ፤ ይላል ልዑል እግዚአብሔር።”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ