ትንቢተ ሕዝቅኤል 34
34
የእስራኤል እረኞች
1እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ተናገረኝ፦ 2“የሰው ልጅ ሆይ! በእስራኤል ጠባቂዎች ላይ ትንቢት ተናገርባቸው፤ እኔ ልዑል እግዚአብሔር ስለ እነርሱ የምለውን ሁሉ በትንቢት እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘መንጋውን መንከባከብና መጠበቅ ትታችሁ ራሳችሁን የምትጠብቁ እናንተ የእስራኤል እረኞች ወዮላችሁ! 3ወተቱን ትጠጣላችሁ፤ ከጠጒራቸው የተሠራውንም ሱፍ ትለብሳላችሁ፤ የሰባውንም በግ ዐርዳችሁ ትበላላችሁ፤ ነገር ግን በጎችን በማሰማራት አትጠብቁም፤ 4የደከሙትን አላበረታቸሁም፤ የታመሙትን አላዳናችሁም፤ የተሰበሩትን አልጠገናችሁም፤ የባዘኑትን አልመለሳችሁም፤ የጠፉትን አልፈለጋችሁም፤ ይህን በማድረግ ፈንታ በግፍና በጭካኔ ገዛችኋቸው። 5በጎቹም እረኛ ስለሌላቸው ተበታተኑ፤ በመበታተናቸውም የምድር አራዊትም ቦጫጭቀው በሉአቸው። #ዘኍ. 27፥17፤ 1ነገ. 22፥17፤ ማቴ. 9፥36፤ ማር. 6፥34። 6ስለዚህም በጎቼ በከፍተኞች ኰረብቶችና ተራራዎች ተንከራተቱ፤ በምድርም ገጽ ተበተኑ፤ የሚጠብቃቸውና ፈልጎ የሚያገኛቸውም የለም።’
7“አሁንም እናንተ እረኞች! እኔ እግዚአብሔር የምላችሁን ስሙ፤ 8እኔ ልዑል እግዚአብሔር ሕያው እንደ መሆኔ እረኞቼ በጎቼን በመመገብና በመጠበቅ ፈንታ ራሳቸውን ብቻ ስለሚመግቡና የጠፉትን በጎቼን የሚፈልግና የሚጠብቅ እረኛ ስለሌላቸው የአውሬ ሲሳይ ሆነው ተበልተዋል። 9ስለዚህም እናንተ እረኞች አድምጡኝ። 10እኔ ልዑል እግዚአብሔር የበጎቹን እረኞች እቃወማለሁ፤ በጎቹን ከእረኞች እጅ ወስጄ እንዳያሰማሩአቸው አደርጋለሁ፤ ከእንግዲህ ወዲህ እረኞቹ ራሳቸውን አይመግቡም፤ ለእነርሱም ምግብ እንዳይሆኑ በጎቼን ከእነርሱ አፍ አስጥላለሁ።
መልካሙ እረኛ
11“ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ‘እኔ ራሴ በጎቼን እፈልጋለሁ፤ በጥንቃቄም እጠብቃቸዋለሁ፤ 12የበግ እረኞች ከተበታተኑት በጎቻቸው መካከል መንጋዎቻቸው እንደሚፈለጉ፥ እኔም በጎቼን እፈልጋለሁ፤ በደመናና በድቅድቅ ጨለማ ቀን ከተበታተኑበት ቦታ ሁሉ አድናቸዋለሁ። 13ከሕዝቦችና ከሀገሮች ሰብስቤ በማውጣት ወደ ሀገራቸው አመጣቸዋለሁ፤ በመኖሪያ ቦታዎችና ውሃ በሚወርድበት ቦታ ሁሉ በእስራኤል ተራራዎች ላይ እመግባቸዋለሁ። 14በመልካም መሰማሪያ ቦታ አሰማራቸዋለሁ፤ መሰማሪያቸውም በእስራኤል ተራራዎች ከፍተኛ ቦታ ይሆናል። በእስራኤል ተራራዎች ላይ ተመግበው በመልካም መሰማሪያ ቦታዎች ያርፋሉ። 15እኔ ራሴ ለበጎቼ እረኛ እሆናለሁ፤ እንዲያርፉም አደርጋቸዋለሁ፤ እኔ ልዑል እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።’
16“የጠፉትን እፈልጋለሁ፤ የባዘኑትን እመልሳለሁ፤ የተሰበሩትን እጠግናለሁ፤ ደካሞችን አበረታለሁ፤ እኔ ትክክለኛ እረኛ ስለ ሆንኩ በግፍ የሰቡትንና ብርቱዎች የሆኑትን አጠፋለሁ።
17“ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ‘ስለ እናንተ ስለ መንጋዎቼ በመልካም በጎችና በክፉ በጎች በአውራ በጎችና በፍየሎች መካከል እፈርዳለሁ። 18ከመልካሙ መሰማሪያ የተመገባችሁት አንሶ ነውን? የቀረውን መሰማሪያችሁን በእግራችሁ የምትረግጡት? የጠራ ውሃ ከጠጣችሁ በኋላ የቀረውን ማደፍረስ አለባችሁን? 19በዚህም ዐይነት ሌሎች በጎቼ እናንተ የረጋገጣችሁትን ሣር ለመብላትና እናንተ ያደፈረሳችሁትንም ውሃ ለመጠጣት ተገደዋል።’
20“ስለዚህ እነሆ፥ እኔ ልዑል እግዚአብሔር በሰቡና በደካሞች በጎቼ መካከል እፈርዳለሁ። 21እናንተ በጎናችሁና በትከሻችሁ እየገፈተራችሁ ደካሞችን እንስሶች በቀንዳችሁ ወግታችሁ ወደ ሩቅ ቦታ ታባርሩአቸዋላችሁ። 22ነገር ግን እኔ በጎቼን እታደጋለሁ፤ ከእንግዲህ ወዲህ ማንም ዘርፎ እንዲወስዳቸው አልፈቅድም፤ በመልካም በግና በክፉ በግ መካከል እፈርዳለሁ፤ 23እንደ አገልጋዬ እንደ ዳዊት ያለ ንጉሥ እረኛ አድርጌ አስነሣላቸዋለሁ፤ እርሱም በእንክብካቤ ይጠብቃቸዋል። 24እኔ እግዚአብሔር አምላካቸው እሆናለሁ፤ አገልጋዬ እንደ ዳዊት ያለ ንጉሥ ይመራቸዋል፤ ይህን እኔ ተናግሬአለሁ። 25የሰላም ዋስትና የሚያገኙበትን ቃል ኪዳን ከእነርሱ ጋር እገባለሁ፤ አደገኞች የሆኑትን አራዊት ከምድሪቱ አስወግዳለሁ፤ ስለዚህ በጎቼ በየመስኩ በሰላም ተሰማርተው ሊኖሩና በየጫካውም ሊያድሩ ይችላሉ።
26“እነርሱንና በተራሮቼ አካባቢ ያሉትን ቦታዎች እባርካለሁ፤ ዝናቡንም በወቅቱ አዘንባለሁ፤ እርሱም የበረከት ዝናብ ይሆናል። 27ዛፎች ያፈራሉ፤ እርሻዎች በቂ የእህል ምርት ይሰጣሉ፤ እያንዳንዱም በገዛ ራሱ ምድር በሰላም ይኖራል፤ የሕዝቤን ቀንበር ሰብሬ ባሪያ አድርገው ከሚገዙአቸው ጨቋኞች እጅ ነጻ ሳወጣቸው እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንኩ ያውቃሉ። 28ከዚያም በኋላ አሕዛብ አይመዘብሩአቸውም፤ አራዊትም ገድለው አይቦጫጭቁአቸውም፤ የሚያስፈራቸው ሳይኖር በሰላም ይኖራሉ፤ 29ብዙ እህል የሚመረትበትን የእርሻ ቦታ አመቻችላቸዋለሁ፤ ዳግመኛ ለራብ አይጋለጡም፤ የሕዝቦች መሳለቂያም አይሆኑም። 30እነርሱ እኔ አምላካቸው እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር እንደ ሆንኩና እስራኤላውያን የእኔ ሕዝብ መሆናቸውን ያውቃሉ፤ እኔ ልዑል እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።
31“በበጎች የተመሰላችሁትና እኔ የማሰማራችሁ መንጋ እናንተ የእስራኤል ሕዝብ ናችሁ፤ እኔም አምላካችሁ ነኝ፤ ይህን የተናገርኩ እኔ ልዑል እግዚአብሔር ነኝ።”
Currently Selected:
ትንቢተ ሕዝቅኤል 34: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997