ወደ ዕብራውያን የተላከ መልእክት 4
4
1ስለዚህ እርሱ ወደሚሰጠን የዕረፍት ቦታ ለመግባት የተቀበልነው ተስፋ ገና የጸና ስለ ሆነ ከእናንተ ማንም ወደዚህ የዕረፍት ቦታ የመግባት ዕድል ሳያገኝ እንዳይቀር ሁላችንም እንጠንቀቅ። 2መልካሙን ዜና እነርሱ እንደ ሰሙት እኛም ሰምተነዋል፤ ነገር ግን እነርሱ የሰሙትን ቃል በእምነት ስላልተቀበሉት አልጠቀማቸውም። 3የእርሱ ሥራ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የተጠናቀቀ ቢሆንም እንኳ፦ “እኔ ወደምሰጣቸው የዕረፍት ቦታ ከቶ አይገቡም ብዬ በቊጣዬ ምዬአለሁ” እንዳለው አሁንም እኛ የምናምነው ወደዚያ እግዚአብሔር ወደሚሰጠን የዕረፍት ቦታ እንገባለን፤ #መዝ. 95፥11። 4ስለ ሰባተኛው ቀን በአንድ ስፍራ “እግዚአብሔር ከሥራው ሁሉ በሰባተኛው ቀን ዐረፈ” ተብሎ ተጽፎአል። #ዘፍ. 2፥2። 5እንዲሁም በዚሁ ስፍራ ላይ እንደገና
“እኔ ወደምሰጣቸው የዕረፍት ቦታ ከቶ አይገቡም” ይላል። #መዝ. 95፥11።
6እነዚያ መልካሙን ዜና በመጀመሪያ የሰሙት ባለመታዘዛቸው እግዚአብሔር ወደሚሰጣቸው የዕረፍት ቦታ አልገቡም፤ ሆኖም ወደዚያ እንዲገቡ የተፈቀደላቸው አንዳንዶች ነበሩ። 7ይህም አስቀድሞ እንደተባለው
“ዛሬ ድምፁን ስትሰሙ፥
ልባችሁን እምቢተኛ አታድርጉ።”
ሲል እግዚአብሔር ከብዙ ዘመን በኋላ በዳዊት አማካይነት በተናገረው ቃል “ዛሬ” ተብሎ የተጠራው ቀን በመወሰኑ ተረጋግጦአል። #መዝ. 95፥7-8።
8ኢያሱ የዕረፍትን ቦታ ሰጥቶአቸው ቢሆን ኖሮ እግዚአብሔር እንደገና “ዛሬ” በማለት ስለ ሌላ ቀን ባልተናገረ ነበር። #ዘዳ. 31፥7፤ ኢያሱ 22፥4። 9እንግዲህ ለእግዚአብሔር ሕዝብ የሰንበትን ዕረፍት የመሰለ ዕረፍት ገና ይቀረዋል፤ 10እግዚአብሔር ከሥራው እንዳረፈ እንዲሁም እግዚአብሔር ወደሚሰጠው ዕረፍት የሚገባ ከሥራው ያርፋል። #ዘፍ. 2፥2። 11ስለዚህ ማንም የእነዚያን ሰዎች አለመታዘዝ ተከትሎ እንዳይወድቅ ወደ እግዚአብሔር የዕረፍት ቦታ ለመግባት እንትጋ።
12የእግዚአብሔር ቃል ሕያውና የሚሠራ ነው፤ ሁለት አፍ ካለው ሰይፍ ይልቅ ስለታም ነው፤ ነፍስንና መንፈስን፥ ጅማትንና ቅልጥምን እስኪለያይ ድረስ የሚቈራርጥ ነው፤ በልብ ውስጥ የተሰወረውንም ሐሳብና ምኞት መርምሮ የሚፈርድ ነው። 13ከእግዚአብሔር ፊት የሚሰወር ምንም ፍጥረት የለም፤ በእርሱ ዐይን ፊት ሁሉ ነገር ግልጥና ዕርቃኑን ሆኖ የሚታይ ነው፤ እኛም መልስ መስጠት የሚገባን በእርሱ ፊት ነው።
ኢየሱስ ታላቁ የካህናት አለቃ
14እንግዲህ ሰማያትን ዘልቆ ወደ ላይ ወደ ሰማይ የወጣ ታላቅ የካህናት አለቃ ስላለን እምነታችንን አጥብቀን እንያዝ፤ የካህናት አለቃውም የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ነው። 15እኛ ያለን የካህናት አለቃ በድካማችን ሊራራልን የሚችል ነው፤ እርሱ በሁሉ ነገር እንደ እኛ ተፈተነ፤ ሆኖም ምንም ኃጢአት አልሠራም። 16እንግዲህ ምሕረት እንድንቀበልና ርዳታ በሚያስፈልገን ጊዜ ጸጋ እንድናገኝ ጸጋው ወደሚገኝበት ወደ እግዚአብሔር ዙፋን ያለ አንዳች ፍርሀት እንቅረብ።
Currently Selected:
ወደ ዕብራውያን የተላከ መልእክት 4: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997