ወደ ዕብራውያን የተላከ መልእክት 5
5
1እያንዳንዱ የካህናት አለቃ ከሰዎች መካከል ተመርጦ ከእግዚአብሔር ጋር በሚያገናኛቸው ጉዳይ በሰዎች ፋንታ ሆኖ መባንና መሥዋዕትን ለማቅረብ ይሾማል። 2እርሱ ራሱ ድካም ያለበት ስለ ሆነ አላዋቂዎችንና ስሕተተኞችን በርኅራኄ ሊመለከታቸው ይችላል። 3እርሱ ራሱም በደካማነቱ ምክንያት የኃጢአት ይቅርታን የሚያስገኝ መሥዋዕትን ማቅረብ የሚገባው ለሕዝቡ ብቻ ሳይሆን ለራሱም ጭምር ነው። #ዘሌ. 9፥7። 4እንደ አሮን በእግዚአብሔር የተጠራ ካልሆነ በቀር ማንም ይህን ክብር በገዛ ራሱ አያገኝም። #ዘፀ. 28፥1።
5እንዲሁም ክርስቶስ የካህናት አለቃ የመሆንን ክብር በገዛ ራሱ አልወሰደም፤ ነገር ግን እርሱ የካህናት አለቃ የመሆንን ክብር ያገኘው፥
“አንተ ልጄ ነህ፤
እኔ ዛሬ ወልጄሃለሁ” ካለው ከእግዚአብሔር ነው። #መዝ. 2፥7።
6በሌላም ስፍራ እግዚአብሔር፥
“እንደ መልከጼዴቅ የክህነት ሹመት
አንተ ለዘለዓለም ካህን ነህ” ይላል። #መዝ. 110፥4።
7ኢየሱስ ሰው ሆኖ በዚህ ምድር በኖረበት ጊዜ ከሞት ሊያድነው ወደሚችል አምላክ በታላቅ ጩኸትና በብዙ እንባ ጸሎትንና ልመናን አቀረበ፤ በትሕትና ራሱን ታዛዥ በማድረጉ እግዚአብሔር ጸሎቱን ሰማው። #ማቴ. 26፥36-46፤ ማር. 14፥32-42፤ ሉቃ. 22፥39-46። 8የእግዚአብሔር ልጅ ቢሆንም እንኳ በተቀበለው መከራ መታዘዝን ተማረ። 9ፍጹም ሆኖ ከተገኘም በኋላ ለሚታዘዙት ሁሉ ለዘለዓለም መዳን ምክንያት ሆነላቸው። 10ይህም እግዚአብሔር በመልከ ጼዴቅ የክህነት ሹመት ዐይነት የካህናት አለቃ አድርጎ ሾመው።
ሰዎች እምነታቸውን እንዳይተዉ የተሰጠ ማስጠንቀቂያ
11ስለዚህ ጉዳይ የምንናገረው ብዙ ነገር አለ፤ ነገር ግን የማስተዋል ችሎታችሁ አነስተኛ ስለ ሆነ ለማስረዳት አስቸጋሪ ነው። 12እስከ አሁን በነበረው ጊዜ እናንተ አስተማሪዎች መሆን በተገባችሁ ነበር፤ ነገር ግን የእግዚአብሔርን ቃል የመጀመሪያውን ትምህርት ሌላ ሰው እንደገና እንዲያስተምራችሁ ያስፈልጋል፤ በዚህ ዐይነት የሚያስፈልጋችሁ ወተት ነው እንጂ ጠንካራ ምግብ አይደለም። 13ወተት የሚጋት ሁሉ ሕፃን ስለ ሆነ መልካም ነገርን ከክፉ የመለየት ትምህርት አልተለማመደም። #1ቆሮ. 3፥2። 14ጠንካራ ምግብ የሚያስፈልጋቸው ግን መልካሙንና ክፉውን የመለየት ልምድ ያላቸው ትላልቅ ሰዎች ናቸው።
Currently Selected:
ወደ ዕብራውያን የተላከ መልእክት 5: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997