ወደ ዕብራውያን የተላከ መልእክት 6
6
1እንግዲህ ስለ ክርስቶስ የተሰጠውን የመጀመሪያ ትምህርት ትተን ፍጹም ወደህ ኦነው ትምህርት እንለፍ፤ ከሞተ ሥራ ንስሓ የመግባትንና በእግዚአብሔር የማመንን መሠረት እንደገና አንመሥርት፤ 2እንዲሁም የጥምቀትን፥ የእጅ መጫንን፥ ከሞት የመነሣትን፥ የዘለዓለም ፍርድን ትምህርት እንደገና አንመሥርት። 3እግዚአብሔር ቢፈቅድልን ይህን እናደርጋለን።
4እምነታቸውን የካዱትን ሰዎች ወደ ንስሓ መመለስ እንዴት ይቻላል? እነዚህ ሰዎች ከዚህ በፊት ብርሃን በርቶላቸው ነበር፤ ሰማያዊውንም ስጦታ ቀምሰው ነበር፤ ከመንፈስ ቅዱስም ጋር ተካፋዮች ሆነው ነበር፤ 5የእግዚአብሔርን መልካም ቃልና የሚመጣውን ዓለም ኀይል ቀምሰው ነበር፤ 6ከዚህ ሁሉ በኋላ እምነታቸውን ቢክዱ እነርሱ ለራሳቸው የእግዚአብሔርን ልጅ እንደገና ስለሚሰቅሉትና በይፋ ስለሚያዋርዱት እነርሱን ወደ ንስሓ መመለስ አይቻልም።
7ብዙ ጊዜ በእርስዋ ላይ የሚወርደውን ዝናብ የምትጠጣ ተክል ለተከለባትም ሰው ጥቅም የምትሰጥ መሬት ከእግዚአብሔር በረከትን ታገኛለች። 8እሾኽና አሜከላ ብታበቅል ግን ዋጋቢስ ትሆናለች፤ በቅርብ ጊዜም ትረገማለች፤ መጨረሻዋም በእሳት መቃጠል ነው። #ዘፍ. 3፥17-18።
9ተወዳጆች ሆይ! ይህን ብንናገርም እንኳ እናንተ መዳናችሁን በሚያመጣ የተሻለ አቋም ላይ ለመሆናችሁ እርግጠኞች ነን። 10እግዚአብሔር ቅን ፈራጅ ነው፤ ስለዚህ ሥራችሁንና በፊትም ሆነ አሁን ቅዱሳንን በመርዳት ስለ ስሙ ያሳያችሁትን ፍቅር አይረሳም። 11እናንተ ሁላችሁም በተስፋ የምትጠባበቁትን ነገር እስክትጨብጡ ድረስ ትጋታችሁን እስከ መጨረሻ እንድታሳዩ እንመኛለን፤ 12የምንመኘውም በእምነትና በትዕግሥት ጸንተው ተስፋ የተሰጣቸውን ነገር የሚወርሱትን ሰዎች እንድትመስሉ እንጂ ዳተኞች እንድትሆኑ አይደለም።
የእግዚአብሔር ተስፋ አስተማማኝነት
13እግዚአብሔር ለአብርሃም ተስፋ በሰጠው ጊዜ የሚምልበት ከእርሱ የበለጠ ሌላ ማንም ስለሌለ እንዲህ ሲል በራሱ ማለ፤ 14“በእርግጥ እባርክሃለሁ፤ ዘርህንም አበዛዋለሁ።” #ዘፍ. 22፥16-17። 15አብርሃም በትዕግሥት ጠብቆ ተስፋ የተደረገለትን ነገር አገኘ። 16ሰዎች ሲምሉ ከራሳቸው በሚበልጥ ስም ይምላሉ፤ ንግግራቸውንም በመሐላ በማጽናት በመካከላቸው ያለውን ክርክር ሁሉ ያስወግዳሉ። 17በዚህ ዐይነት እግዚአብሔር ውሳኔው የማይለወጥ መሆኑን ለማስረዳት ፈልጎ ለተስፋው ወራሾች ተስፋውን በመሐላ አጸናላቸው። 18በዚሁ ዐይነት እግዚአብሔር የማይለወጡትንና የማይዋሽባቸውን ሁለቱን ነገሮች፥ ማለትም ተስፋውንና መሐላውን ሰጥቶናል፤ በእነዚህም በሁለቱ ነገሮች አማካይነት በፊታችን ያለውን ተስፋ አጥብቀን መያዝ እንድንችል መጠጊያ ለማግኘት ወደ እርሱ የሸሸን እኛ ታላቅ መጽናናትን እናገኛለን። 19ይህ ተስፋ ለሕይወታችን እንደማይነቃነቅ አስተማማኝ መልሕቅ ነው፤ በኢየሱስ ያለን ተስፋ መጋረጃውን አልፎ ወደ መቅደስ ይገባል። #ዘሌ. 16፥2። 20ወደዚህም መቅደስ ኢየሱስ እንደ መልከጼዴቅ የክህነት ሹመት ለዘለዓለም የካህናት አለቃ ሆኖ ስለ እኛ ቀድሞ ገብቶአል።
Currently Selected:
ወደ ዕብራውያን የተላከ መልእክት 6: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997