የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትንቢተ ሆሴዕ 1

1
የሆሴዕ ሚስትና ልጆች ምሳሌነት
1ዖዝያን፥ ኢዮአታም፥ አካዝና ሕዝቅያስ በይሁዳ ተከታትለው በነገሡባቸው ዘመናት፤ እንዲሁም የዮአስ ልጅ ኢዮርብዓም የእስራኤል ንጉሥ በነበረበት ዘመን፥ እግዚአብሔር ለብኤር ልጅ ለሆሴዕ የገለጠለት የትንቢት ቃል ይህ ነው። #2ነገ. 14፥23—15፥7፤ 15፥32—16፥20፤ 18፥1—20፥21፤ 2ዜ.መ. 26፥1—27፥8፤ 28፥1—32፥33።
2እግዚአብሔር በሆሴዕ አማካይነት ለእስራኤል ሕዝብ ቃሉን ማስተላለፍ ሲጀምር ሆሴዕን እንዲህ አለው፦ “ሕዝቤ ከእኔ ተለይቶ አጸያፊ የሆነ የዝሙት ሥራ በመሥራት ላይ ይገኛል፤ እንግዲህ አንተም ሂድና ዘማዊት ሴት አግባ፤ ከእርስዋም የዝሙት ልጆችን ውለድ።”
3ስለዚህ ሆሴዕ ሄዶ የዲብላይምን ልጅ ጎሜርን አገባ፤ እርስዋም ፀንሳ ወንድ ልጅ ወለደችለት። 4ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ሆሴዕን እንዲህ አለው፦ “ኢዩና ዘሮቹ በኢይዝራኤል በገደሉአቸው ሰዎች ምክንያት የኢዩን ቤተሰብ የምቀጣበት ጊዜ ሩቅ አይደለም፤ የእስራኤልም መንግሥት እንዲያከትም አደርጋለሁ፤ #2ነገ. 10፥11። 5በዚያን ጊዜ በኢይዝራኤል ሸለቆ የእስራኤልን ጦር እደመስሳለሁ፤ ስለዚህ የልጅህን ስም ‘ኢይዝራኤል’ ብለህ ጥራው።”
6ጎሜር ዳግመኛ ፀንሳ ሴት ልጅ ወለደች፤ እግዚአብሔርም ሆሴዕን እንዲህ አለው፦ “ለእስራኤል ሕዝብ ከእንግዲህ ወዲህ ፍቅር አላሳያቸውም፤ ይቅርታም አላደርግላቸውም፤ ስለዚህ የልጅህን ስም ‘ሎሩሐማ’ ብለህ ጥራት። #1፥6 ኢይዝራኤል፦ እግዚአብሔር ይበትናል ወይም ይዘራል ማለት ነው። #1፥6 ሎሩሐማ፦ ምሕረት የማይደረግለት ሕዝብ ማለት ነው። 7ለይሁዳ ሕዝቦች ግን ፍቅር አሳያቸዋለሁ፤ እኔ አምላካቸው እግዚአብሔር አድናቸዋለሁ፤ የማድናቸውም በጦርነት ኀይል አይደለም፤ በሰይፍ፥ በቀስትና በፍላጻ ወይም በፈረስና በፈረሰኛ አይደለም።”
8ጎሜር ሎሩሐማን ጡት ካስጣለች በኋላ እንደገና ፀንሳ ወንድ ልጅ ወለደች። 9እግዚአብሔርም ሆሴዕን “ከእንግዲህ ወዲህ የእስራኤል ሕዝብ ወገኖቼ አይደሉም፤ እኔም የእነርሱ አምላክ አይደለሁም፤ ስለዚህ የልጅህን ስም ‘ሎዓሚ’ ብለህ ጥራው አለው።” #1፥9 ሎዓሚ፦ ሕዝቤ ያይደለ ማለት ነው።
ለእስራኤል ሕዝብ የተነገረ የተስፋ ቃል
10የእስራኤል ሕዝብ ብዛት ሊቈጠር ወይም ሊለካ እንደማይቻል የባሕር አሸዋ ይሆናል፤ አሁን እግዚአብሔር “ሕዝቤ አይደላችሁም” ቢላቸው በዚሁ ስፍራ “የሕያው እግዚአብሔር ልጆች!” ተብለው የሚጠሩበት ጊዜ ይመጣል፤ #ሮም 9፥26። 11በዚያን ጊዜ የይሁዳና የእስራኤል ሕዝብ አንድ ይሆናሉ፤ ሁለቱንም የሚያስተዳድር አንድ መሪ ይመርጣሉ፤ እንደገናም በገዛ ምድራቸው ላይ በዕድገትና በብልጽግና ይኖራሉ፤ የኢይዝራኤልም ቀን ታላቅ ይሆናል። #1፥11 በዕድገትና በብልጽግና፦ ዕብራውያን ከተበታተኑባቸው አገሮች ይመለሳሉ ማለት ነው።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ