መጽሐፈ መሳፍንት 21
21
ለብንያም ነገድ ተወላጆች የተመደቡ ሚስቶች
1እስራኤላውያን በምጽጳ በተሰበሰቡ ጊዜ “ከእኛ መካከል ማንም ሰው ሴት ልጁን ለብንያማዊ መዳር የለበትም” በማለት ተማምለው ነበር። 2እስራኤላውያን ወደ ቤትኤል መጥተው በእግዚአብሔር ፊት እስከ ማታ ተቀምጠው ድምፃቸውን ከፍ አድርገው አለቀሱ። 3እነርሱም፦ አቤቱ፥ የእስራኤል አምላክ ሆይ! ዛሬ ከእስራኤል አንድ ነገድ መታጣቱ፥ ስለምን ይህ በእስራኤል ላይ ሆነ? አሉ። 4በማግስቱም ጧት በማለዳ ሕዝቡ በዚያ መሠዊያ ሠሩ፤ የሚቃጠልና የደኅንነት መሥዋዕትም አቀረቡ። 5“በምጽጳ በእግዚአብሔር ፊት ስንሰበሰብ ወደዚያ ያልመጣ ከእስራኤል ነገዶች መካከል አንድ ወገን እንኳ ይገኛልን?” ብለውም ጠየቁ፤ ይህንንም ያሉበት ምክንያት ወደ ምጽጳ ያልሄደ ማንም ሰው ቢገኝ በሞት ለመቅጣት ተማምለው ስለ ነበር ነው። 6የእስራኤል ሕዝብ ወንድሞቻቸው ለሆኑት ለብንያማውያን አዝነው ስለ ነበር “ዛሬ ከእስራኤል አንድ ነገድ ጠፍቷል፤ 7ከሴቶች ልጆቻችን ማንኛይቱንም ለእነርሱ እንዳንድር በመሐላ ቃል ስለ ገባን ከሞት የተረፉት ብንያማውያን ሚስት ያገኙ ዘንድ ምን እናድርግ?” አሉ።
8እነርሱ እንዲህ አሉ፦ “ከእስራኤል ነገዶች መካከል ወደ እግዚአብሔር ወደ ምጽጳ ያልመጣ አለን?” እነሆ ከያቤሽ ገለዓድ ወደ ስብሰባው ማንም አልመጣም ነበር። 9ሠራዊቱን ለመቊጠር በያንዳንዱ ስም በሚጠራበት ጊዜ ከያቤሽ ወገን አንድም ሰው አልነበረም፤ 10ስለዚህ ጉባኤው “ወደ ያቤሽ ሄዳችሁ ሴቶችና ሕፃናት ሳይቀሩ የገለዓድ ኗሪዎችን በሰይፍ ስለት ግደሉ!” ብለው ዐሥራ ሁለት ሺህ ኀያላንን ላኩ። 11ወንዶችን ሁሉና ከወንድ ጋር የተገናኙትን ሴቶች ሁሉ ግደሉ ብለው አዘዙአቸው። 12በዚህም ዐይነት በያቤሽ ገለዓድ ካሉት ኗሪዎች መካከል አራት መቶ ወንድ ያላወቁ ቆነጃጅት አገኙ፤ ስለዚህም እነርሱን በከነዓን ምድር በሴሎ ወደሚገኘው ሰፈር ይዘው መጡ።
13ከዚህ በኋላ መላው ጉባኤ የሪሞን አለት ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ወደነበሩት ብንያማውያን መልእክት ልከው ጦርነቱ እንዲቆም ተስማሙ፤ 14ብንያማውያንም ተመልሰው መጡ፤ ሌሎቹም እስራኤላውያን ከሞት በመትረፍ ከያቤሽ ተማርከው የመጡትን ልጃገረዶች ሰጡአቸው፤ ነገር ግን ቊጥራቸው ተመጣጣኝ ሆኖ አልተገኘም።
15እግዚአብሔር በእስራኤላውያን ነገዶች መካከል ያለው አንድነት እንዲቋረጥ አድርጎ ስለ ነበር ሕዝቡ ስለ ብንያማውያን እጅግ አዘኑ። 16ስለዚህም የጉባኤው መሪዎች እንዲህ አሉ፥ “በብንያም ነገድ ከእንግዲህ ሴቶች አልተገኙም፤ ታዲያ ከሞት የተረፉት ወንዶች ሚስት ማግኘት ይችሉ ዘንድ ምን እናድርግ? 17ከእስራኤል ነገድ አንዱ ጠፍቶ እንዳይቀር ብንያማውያን ወራሽ ሊኖራቸው ይገባል። 18ይሁን እንጂ ከእኛ መካከል ማንም ሰው ሴት ልጁን ለብንያማዊ ቢድር የተረገመ እንደሚሆን በመሐላ ቃል የገባን ስለ ሆነ ሴቶች ልጆቻችንን ያገቡ ዘንድ ልንፈቅድላቸው አንችልም።”
19ከዚህ በኋላ “በየዓመቱ በሴሎ ለእግዚአብሔር የሚዘጋጀው በዓል እነሆ ቀርቦአል” በማለትም አሰቡ፤ ሴሎ ከቤትኤል በስተ ሰሜን፥ ከለቦና በስተ ደቡብ፥ በቤትኤልና በሴኬም መካከል ካለው መንገድ በስተ ምሥራቅ ነበረች። 20ስለዚህ ብንያማውያንን እንዲህ አሉአቸው፥ “ሂዱና በወይን ተክል ውስጥ ሸምቁ፤ 21ተጠባበቁ፤ በበዓሉ ዕለት የሴሎ ልጃገረዶች ለመጨፈር ሲመጡ እናንተም ከወይኑ ተክል ውስጥ ውጡ፤ እያንዳንዳችሁ ከእነዚያ ልጃገረዶች መካከል እየጠለፋችሁ ሚስት አድርጋችሁ ውሰዱ፤ ወደ ብንያም ግዛትም ይዛችኋቸው ሂዱ። 22አባቶቻቸውም ሆኑ ወንድሞቻቸው ወደ እናንተ መጥተው ሊቃወሙአችሁ ቢፈልጉ ‘ሚስቶች ለማድረግ የወሰድናቸው በጦርነት አስገድደን ስላልሆነ እባካችሁ ምሕረት አድርጉልን፤ እናንተም በፈቃዳችሁ ስላልሰጣችሁን መሐላችሁን በማፍረስ በደለኞች አትሆኑም’ ብላችሁ መልስ መስጠት ትችላላችሁ።”
23ብንያማውያንም እንደዚሁ አደረጉ፤ በብዛታቸው ልክ እያንዳንዱ በሴሎ ከሚጨፍሩት ልጃገረዶች መካከል እየጠለፈ በሚስትነት ይዞ ሄደ፤ ወደ ግዛታቸውም ተመልሰው ከተሞቻቸውን በማደስ በዚያ ኖሩ። 24በዚያኑ ጊዜ ሌሎቹም እስራኤላውያን በሙሉ ለመሄድ ተነሡ፤ እያንዳንዱም ወደ ራሱ ነገድና ቤተሰብ እንዲሁም ወደራሱ ቤት ንብረት ተመለሰ።
25በዚያም ዘመን በእስራኤል ንጉሥ አልነበረም፤ እያንዳንዱም ሰው ለራሱ ደስ ያለውን ነገር ሁሉ እንደ ፈለገ ያደርግ ነበር። #መሳ. 17፥6።
Currently Selected:
መጽሐፈ መሳፍንት 21: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997