መጽሐፈ ኢያሱ 15
15
ለይሁዳ ነገድ ርስት ሆኖ የተመደበ ምድር
1የይሁዳ ነገድ ድርሻ በየወገናቸው እስከ ኤዶም ድንበር፥ ወደ ጺን ምድረ በዳ እስከ ደቡብ መጨረሻ ይደርሳል። 2ደቡባዊው ድንበራቸው እስከ ጨው ባሕር መጨረሻ ወደ ደቡብ ትይዩ እስከ ሆነው እስከ ልሳነ ምድሩ ነበር። 3ወደ ደቡብ አቅጣጫ ከዐቅራቢም መተላለፊያ እስከ ጺን ይደርሳል፤ በቃዴስ በርኔ ደቡብም በኩል ሔጽሮንን አልፎ ወደ አዳር ከፍ ይልና ወደ ቃርቃ አቅጣጫ ይታጠፋል። 4ወደ ዓጽሞንም በመዝለቅ፥ በግብጽ ድንበር ላይ የሚገኘው ወንዝ፥ እስከ ሜዲቴራኒያን ባሕር ይከተላል፤ ያም የድንበሩ መጨረሻ ይሆናል፤ እንግዲህ በደቡብ በኩል የይሁዳ ድንበር ይህ ነው።
5በምሥራቅ በኩልም ያለው ድንበር እስከ ጨው ባሕር፥ እስከ ዮርዳኖስ ወንዝ መጨረሻ ነበር። በሰሜንም በኩል ያለው ድንበር ከዮርዳኖስ ወንዝ መጨረሻና ከባሕሩ ልሳነ ምድር 6እስከ ቤትሆግላ ይወጣል፤ ከዚያም በሰሜን በዮርዳኖስ ሸለቆ በኩል አልፎ የሮቤል ልጅ ወደ ሆነው ወደ ቦሐን መታሰቢያ ድንጋይ ድረስ ይወጣል። 7ድንበሩም ከአኮር ሸለቆ ተነሥቶ ወደ ዳቢር ይወጣል፤ በሰሜን በኩልም አድርጎ ወደ ጌልጌላ ይመለሳል፤ እርሱ ከአዱሚም ትይዩ ይኸውም ከሸለቆው በደቡብ በኩል ነው፤ ስለዚህ ድንበሩ በኤንሼሜሽ ምንጭ በኩል ያልፋል፤ መጨረሻውም ኤን ሮጌል ነው። 8ድንበሩ በሔኖም ልጅ ሸለቆ ከደቡብ ዝቅተኛ ቦታ የኢያቡሳውያን ከተማ በሆነችው በኢየሩሳሌም በኩል ከሔኖም ሸለቆ ፊት ለፊት እስካለው ተራራ ጫፍ ድረስ በመዝለቅ በሰሜን በኩል ወደ ሬፋይም ሸለቆ ይደርሳል። 9ከዚያም ድንበሩ ከተራራው ጫፍ ተነሥቶ ወደ ኔፍቶሐ ምንጮች ይደርሳል፤ ወደ ዔፍሮንም ተራራ ከተሞች ይወጣል፤ ወደ ባዓላ ወይም ቂርያት ይዓሪም ይታጠፋል፤ 10ድንበሩም በበዓላ ዙሪያ በስተምዕራብ በኩል ወደ ኤዶም ተራራ ይዞራል፤ በይዓሪም ወይም ክሳሎን ተብሎ ወደሚጠራው ተራራ ቊልቊለት በኩል አድርጎ ያልፋል፤ ወደ ቤትሼሜሽም ይወርዳል፤ በቲምናም በኩል ያልፋል። 11ይኸው ድንበር በዔቅሮን ሰሜናዊ ኮረብታ ከፍ በማለት ወደ ሺከሮን አቅጣጫ ይታጠፍና የባዓላን ኮረብታና እንዲሁም ያብኒኤልን አልፎ ይሄዳል፤ መጨረሻውም የሜድትራኒያን ባሕር ይሆናል፤ 12የምዕራባዊው ዳርቻ እስከ ሜዲቴራኒያን ባሕርና ጠረፉ ድረስ ነው፤ ይህም የይሁዳ ልጆች እንደየወገናቸው ዙሪያ ድንበራቸው ነው።
ካሌብ ኬብሮንና ደቢርን ድል አድርጎ መያዙ
(መሳ. 1፥11-15)
13እግዚአብሔር ኢያሱን ባዘዘው መሠረት ለይፉኔ ልጅ ለካሌብ ከይሁዳ ነገድ ኪርያት ዐርባን ወይም ኬብሮን እርስት አድርጎ ሰጠው። (አርባ የዐናቅ አባት ነበር) 14ካሌብም የዐናቅን ሦስት ልጆች ሼሻይን፥ አሒማንና ታልማይን አባረረ፤ እነርሱም የዐናቅ ዘሮች ነበሩ። #መሳ. 1፥20። 15ከዚያም ተነሥቶ በደቢር በሚኖሩት ሕዝብ ላይ አደጋ ለመጣል ሄደ፤ ይህች ከተማ ቀድሞ ቂርያትሴፌር ተብላ ትጠራ ነበር፤ 16ካሌብም፥ “ቂርያትሴፌርን ወግቶ ለሚይዛት ሰው ልጄን ዓክሳን እድርለታለሁ” ብሎ ተናገረ፤ 17ስለዚህም የካሌብ ወንድም ከሆነው ከቀናዝ የተወለደው ዖትኒኤል ያችን ከተማ ወግቶ ያዘ፤ ካሌብም ልጁን ዓክሳን ዳረለት፤ 18ዖትኒኤልም በሠርጋቸው ቀን ዓክሳን ከአባትዋ የእርሻ መሬት እንድትለምን መከራት፤ እርስዋም ከበቅሎዋ ላይ ወረደች፤ #15፥18 መከራት፦ በዕብራይስጥ “መከረችው” ይላል። (መሳ 1፥14 ተመልከት) ካሌብም “ምን ትፈልጊአለሽ” ሲል ጠየቃት፤ 19እርስዋም “የሰጠኸኝ ምድር ደረቅ ስለ ሆነ ጥቂት የውሃ ጒድጓዶች እንድትሰጠኝ እፈልጋለሁ” አለችው። ካሌብም ከላይና ከታች በኩል ያሉትን ሁለቱን የውሃ ምንጮች ሰጣት።
የይሁዳ ከተሞች
20የይሁዳ ነገድ በየወገናቸው የተቀበሉት የርስት ድርሻ ይህ ነው፤ 21በስተደቡብ በኤዶም ዳርቻ ያሉት የይሁዳ ነገድ ከተሞች ቃብዱኤል፥ ዔዴርና ያጉር ናቸው። 22ቂና፥ ዲሞና፥ ዓድዓዳ፥ 23ቃዴስ፥ ሐጾር፥ ይትናን፥ 24ዚፍ፥ ጤሌም፥ በዓሎት፥ 25ሐጾርሐዳታ፥ ቂርዮትሔጽሮን ወይም ሐጾር፥ 26አማም፥ ሸማዕ፥ ሞላዳ፥ 27ሐጻርጋዳ፥ ሔሽሞን፥ ቤትጳሌጥ፥ 28ሐጻርሹዓል፥ ቤርሳቤህ፥ ቢዝዮትያ፥ 29በዓላ፥ ዒዩም፥ ዔጼም፥ 30ኤልቶላድ፥ ከሲል፥ ሖርማ፥ 31ጺቅላግ፥ ማድማና፥ ሳንሳና፥ 32ልባዎት፥ ሺልሒም፥ ዓይንና፥ ሪሞን ተብለው የሚጠሩት በድምሩ ኻያ ዘጠኝ ከተሞች ሲሆኑ፥ በዙሪያቸው የሚገኙት ታናናሽ ከተሞችንም ሁሉ ያጠቃልላሉ።
33በቆላማው ቦታ ያሉትም ከተሞች ኤሽታኦል፥ ጾርዓ፥ አሽና፥ 34ዛኖሐ፥ ዔንጋኒም፥ ታፑሐ፥ ዔናም፥ 35ያርሙት፥ ዐዱላም፥ ሶኮህ፥ ዐዜቃ፥ 36ሻዕራይም፥ ዐዲታይም፥ ገዴራና ገዴሮታይም ተብለው የሚጠሩ በድምሩ ዐሥራ አራት ከተሞች ሲሆኑ፥ በዙሪያቸው የሚገኙ ታናናሽ ከተሞችን ሁሉ ያጠቃልላል።
37እንዲሁም ጽናን፥ ሐዳሻ፥ ሚግዳልጋድ፥ 38ዲልዓን፥ ምጽጳ፥ ዮቅጥኤል፥ 39ላኪሽ፥ ቦጽቃት፥ ዔግሎን፥ 40ካቦን፥ ላሕማስ፥ ኪትሊሽ፥ 41ገዴሮት፥ ቤትዳጎን፥ ናዕማና ማቄዳ ተብለው የሚጠሩ በድምሩ ዐሥራ ስድስት ከተሞች ሲሆኑ በዙሪያቸው ያሉትን ታናናሽ ከተሞችን ሁሉ ያጠቃልላል።
42ከነዚህም ሁሉ ጋር ሊብና፥ ዔቴር፥ ዐሻን፥ 43ይፍታሕ፥ አሽና፥ ነጺብ፥ 44ቀዒላ፥ አክዚብና፥ ማሬሻ ተብለው የሚጠሩ በድምሩ ዘጠኝ ከተሞች ሲሆኑ በዙሪያቸው ያሉትንም ታናናሽ ከተሞች ያጠቃልላሉ።
45በዚያም ከታናናሽ ከተሞችዋና መንደሮችዋ ጋር ዔቅሮን የምትባል ከተማ ነበረች፤ 46በአሽዶድም አቅራቢያ ከዔቅሮን እስከ ሜዲቴራኒያን ባሕር የተሠሩ ከተሞችና መንደሮቻቸው ነበሩ።
47እንዲሁም በግብጽ ወሰን እስከሚገኘው ወንዝና እስከ ሜዲቴራኒያን ባሕር ጠረፍ ድረስ የሚደርሱ ታናናሽ ከተሞችና መንደሮች ያሉአቸው አሽዶድና ጋዛ ተብለው የሚጠሩ ከተሞች ነበሩ።
48በኮረብታማውም አገር ሻሚር፥ ያቲር፥ ሶኮህ፥ 49ዳና፥ ቂርያትሴፌር ወይም ደቢር፥ 50ዐናብ፥ ኤሽተሞዓ፥ ዐኒም፥ 51ጎሼን፥ ሖሎንና ጊሎ ተብለው የሚጠሩ በድምሩ ዐሥራ አንድ ከተሞች ሲሆኑ በዙሪያቸው ያሉትንም ትናንሽ ከተሞችን ያጠቃልላሉ።
52ደግሞም አራብ፥ ዱማ፥ ኤሽዓን፥ 53ያኒም፥ ቤትታፑሐ፥ አፌቃ፥ 54ሑምጣ፥ ኬብሮንና ጺዖር ተብለው የሚጠሩ በድምሩ ዘጠኝ ከተሞች ሲሆኑ በዙሪያቸው ያሉትን መንደሮች ያጠቃልላሉ።
55ከእነዚህም ሌላ ማዖን፥ ቀርሜሎስ፥ ዚፍ፥ ዩጣ፥ 56ኢይዝራኤል፥ ዮቅድዓም፥ ዛኖሐ፥ 57ቃይን፥ ጊብዓና ቲምና ተብለው የሚጠሩ በድምሩ ዐሥር ከተሞች ሲሆኑ በዙሪያቸው ያሉትን ትናንሽ ከተሞችን ያጠቃልላሉ።
58እንዲሁም ሐልሑል፥ ቤትጹር፥ ጌዶር፥ 59ማዕራት፥ ቤትዓኖትና ኤልትቆን ተብለው የሚጠሩ በድምሩ ስድስት ከተሞች ሲሆኑ፥ በዙሪያቸው ያሉትን መንደሮች ያጠቃልላሉ።
60ደግሞም ቂርያትባዓል ወይም ቂርያትይዓሪምና ራባ ተብለው የሚጠሩ ሁለት ከተሞች ሲሆኑ፥ በዙሪያቸው ያሉትን ትናንሽ ከተሞችን ይጨምራሉ።
61ከእነዚህም ሁሉ ጋር በበረሓማው ምድር ቤትዐራባ፥ ሚዲን፥ ሴካካ፥ 62ኒብሻን፥ የጨው ከተማና ዔንገዲ ተብለው የሚጠሩ በድምሩ ስድስት ከተሞች ሲሆኑ በዙሪያቸው የሚገኙትን መንደሮች ያጠቃልላሉ።
63ነገር ግን የይሁዳ ሕዝብ በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን ኢያቡሳውያንን ማባረር አልቻሉም፤ ስለዚህም ኢያቡሳውያን እስከ አሁን ድረስ በኢየሩሳሌም ከይሁዳ ሕዝብ ጋር ይኖራሉ። #መሳ. 1፥21፤ 2ሳሙ. 5፥6፤ 1ዜ.መ. 11፥4።
Currently Selected:
መጽሐፈ ኢያሱ 15: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997