የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ ኢያሱ 21

21
ለሌዋውያን የተመደቡ ከተሞች
1የሌዊ ነገድ ቤተሰቦች መሪዎች ወደ ካህኑ አልዓዛር፥ ወደ ነዌ ልጅ ኢያሱና ወደ እስራኤል ሕዝብ የነገድ መሪዎች ሄዱ፤ 2በዚያም በከነዓን ምድር በምትገኘው በሴሎ ወደ እነርሱ ፊት ቀርበው፦ “እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት የምንኖርባቸው ከተሞችና በዙሪያቸውም ለከብቶቻችን ግጦሽ የሚሆን መሬት እንዲሰጠን አዞአል” አሉአቸው። #ዘኍ. 35፥1-8። 3ስለዚህም በእግዚአብሔር ትእዛዝ መሠረት የእስራኤል ሕዝብ ለሌዋውያን የሚከተሉትን ከተሞችና ለከብት ግጦሽ የሚሆን መሬት ከርስቶቻቸው ከፍለው ሰጡአቸው።
4የመጀመሪያው ዕጣ ለቀዓት ጐሣ ወጣ፤ ከሌዊ ነገድ ለካህኑ ለአሮን ልጆች ዐሥራ ሦስት ከተሞች በዕጣ ተከፋፈለ፤ እነዚህም ከተሞች የተወሰዱት ከይሁዳ፥ ከስምዖንና ከብንያም ነገዶች ይዞታዎች ነበር፤ 5ለቀሪው ለቀዓት ጐሣ ከኤፍሬም፥ ከዳንና ከምዕራብ ምናሴ ይዞታዎች ዐሥር ከተሞች በዕጣ ተመደቡለት።
6ለጌርሾን ጐሣ ከይሳኮር፥ ከአሴር፥ ከንፍታሌምና በባሳን ካለው ከምሥራቅ ምናሴ ግዛት ይዞታዎች ተከፍለው ዐሥራ ሦስት ከተሞች ተመደቡለት።
7ለመራሪ ጐሣ እንደየወገናቸው ከሮቤል፥ ከጋድና ከዛብሎን ይዞታዎች ተከፍለው ዐሥራ ሁለት ከተሞች ተመደቡላቸው።
8በሙሴ አማካይነት እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት የእስራኤል ሕዝብ እነዚህን ከተሞችና የግጦሽ ምድር ለሌዋውያን በዕጣ አካፈሉአቸው። 9ከይሁዳና ከስምዖን ነገዶች በስም የተጠቀሱትን የሚከተሉትን ከተሞች ሰጡ፤ 10የመጀመሪያው ዕጣ ለእነርሱ ስለ ወጣ ከሌዊ ነገድ የአሮን ዘሮች ለሆኑት ለቀዓት ወገኖች ተሰጠ። 11በይሁዳ ተራራማ አገር ያለችውን ቂርይትአርባቅ የምትባለውን ከተማ፥ በዙሪያዋ ካለው የግጦሽ መሬት ጋር ሰጡአቸው፤ እርስዋም ኬብሮን ናት፤ ይህም አርባቅ የዐናቅ አባት ነበር። 12ይሁን እንጂ በከተማይቱ የሚገኘው የእርሻ ቦታና በክልልዋ ውስጥ ያሉት መንደሮች አስቀድሞ ለይፉኔ ልጅ ለካሌብ ርስት ሆነው ተሰጥተዋል።
13ከመማጸኛ ከተሞች አንድዋ ከሆነችው ኬብሮን ከግጦሽ መሬትዋ ጋር በተጨማሪ ለካህኑ ለአሮን ዘሮች ከዚህ የሚከተሉት ከተሞች ተመደቡላቸው፤ እነርሱም ሊብና፥ ከግጦሽ መሬትዋ ጋር፥ 14ያቲር፥ ኤሽተሞዓ፥ 15ሖሎን ከግጦሽ መሬትዋ ጋር፥ ደቢር፥ ከግጦሽ መሬትዋ ጋር 16ዓይን ከግጦሽ መሬትዋ ጋር፥ ዩጣና ከግጦሽ መሬትዋ ጋር፥ ቤትሼሜሽ ከግጦሽ መሬትዋ ጋር ከይሁዳና ከስምዖን ምድር ተከፍለው የተሰጡ ዘጠኝ ከተሞች ናቸው። 17ከብንያም ግዛት ተከፍለው አራት ከተሞች ተሰጡአቸው። እነርሱም ከግጦሽ ምድራቸው ጋር ገባዖን፥ ጌባዕ፥ 18ዐናቶትና ዐልሞን ተብለው የሚጠሩት ናቸው። 19የአሮን ዘሮች ለሆኑት ካህናት ከግጦሽ ምድራቸው ጋር በድምሩ ዐሥራ ሦስት ከተሞች ተመደቡላቸው።
20ለቀሩት ከሌዊ ነገድ ለሆኑት የቀዓት ጐሣዎች ከኤፍሬም ነገድ ይዞታ ተከፍሎ ተሰጣቸው። 21ለእነርሱም የተሰጡት አራት ከተሞች ከመማጸኛ ከተሞች አንድዋ የሆነችው ሴኬምና በኮረብታማው በኤፍሬም አገር የሚገኙት የግጦሽ መሬቶችዋ፥ ጌዜር፥ 22ቂብጻይምና ቤትሖሮን የተባሉት ከግጦሽ መሬቶቻቸው ጋር ናቸው። 23ከዳን ግዛት ተከፍለው የተሰጡአቸውም አራት ከተሞች ከግጦሽ ምድራቸው ጋር ኤልተቄ፥ ጊበቶን፥ 24አያሎንና ጋትሪሞን ናቸው። 25ከምዕራብ ምናሴ ግዛት ተከፍለው የተሰጡአቸውም ሁለት ከተሞች ከግጦሽ ምድራቸው ጋር ታዕናክና ጋትሪሞን ናቸው፤ 26እነዚህ የቀሩት የቀዓት ጐሣ ከግጦሽ ምድራቸው ጋር በድምሩ ዐሥር ከተሞች ተረከቡ።
27የጌርሾን ጐሣ የሆነው ሌላው የሌዋውያን ወገን ከግጦሽ ምድራቸው ጋር ከምሥራቅ ምናሴ ግዛት ተከፍለው የተሰጡት ሁለት ከተሞች በባሳን ከመማጸኛ ከተሞች አንድዋ የሆነችው ጎላን ከግጦሽ ምድራቸው ጋር በዔሽተራ ከግጦሽ ምድራቸው ጋር ናቸው፤ 28ከይሳኮር ግዛትም ተከፍለው ከግጦሽ ምድራቸው ጋር የተሰጡአቸው አራት ከተሞች፥ ቂሽዮን፥ ዳብራት፥ 29ያርሙትና ዔንጋኒም ናቸው፤ 30ከአሴር ግዛትም ተከፍለው ከግጦሽ ምድራቸው ጋር የተሰጡአቸው አራት ከተሞች፥ ሚሽአል፥ ዓብዶን፥ 31ሔልቃትና ረሖብ ናቸው፤ 32ከንፍታሌም ግዛት ተከፍለው ከግጦሽ ምድራቸው ጋር የተሰጡአቸው ሦስት ከተሞች በገሊላ ከመማጸኛ ከተሞች አንድዋ የሆነችው ቄዴሽ፥ ሐሞት፥ ዶርና ቃርታን ናቸው። 33የጌርሾን ጐሣ በሙሉ በድምሩ ዐሥራ ሦስት ከተሞችን ከግጦሽ ምድራቸው ጋር ተረከቡ።
34ከመራሪ የተወለዱትም ቀሪዎቹ ሌዋውያን ከዛብሎን ግዛት ተከፍለው ከግጦሽ ምድራቸው ጋር የተረከቡአቸው አራት ከተሞች ዮቅነዓም፥ ቃርታ፥ 35ዲምናና ናህላል ናቸው። 36ከሮቤል ግዛትም ተከፍለው ከግጦሽ ምድራቸው ጋር የተሰጡአቸው አራት ከተሞች ቤጼር፥ ያሀጽ፥ 37ቀዴሞትና ሜፋዓት ናቸው፤ 38ከጋድ ግዛት ተከፍለው ከግጦሽ ምድራቸው ጋር የተሰጡአቸው አራት ከተሞች ከመማጸኛ ከተሞች አንድዋ የሆነችው በገለዓድ ግዛት የምትገኘው ራሞት፥ ማሕናይም፥ 39ሐሴቦንና ያዕዜር ናቸው፤ 40የሌዋውያን ነገድ ለሆኑት ለቀሪዎቹ የሜራሪ ጐሣዎች የተሰጡት ዐሥራ ሁለት ከተሞች ናቸው።
41በእስራኤላውያን ይዞታ ሥር የነበሩት የሌዋውያን ከተሞች ከግጦሽ መሬታቸው ጋር አርባ ስምንት ነበሩ። 42በእነዚህም መሬቶች በእያንዳንዱ ዘሪያ የግጦሽ መሬት ነበራቸው።
እስራኤላውያን ምድሪቱን ወርሰው ሰላም ማግኘታቸው
43ስለዚህ እግዚአብሔር ለቀድሞ አባቶቻቸው ሊሰጣቸው በመሐላ ቃል የገባላቸውን ምድር ሁሉ ለእስራኤላውያን ሰጠ። ምድሪቱንም ከወረሱ በኋላ በዚያ ተደላድለው ኖሩ፤ 44እግዚአብሔርም ለቀድሞ አባቶቻቸው በገባው ቃል መሠረት በአካባቢያቸው ሁሉ ሰላምን ሰጣቸው፤ በጠላቶቻቸው ላይ ብዙ ድልን አቀዳጅቶአቸው ስለ ነበረ ከጠላቶቻቸው አንድ እንኳ በፊታቸው ሊቆም አልቻለም። 45በዚህም ዐይነት እግዚአብሔር ለእስራኤል ቤት የገባው ቃል ኪዳን ሁሉ ተፈጸመ እንጂ አንድም የቀረ የለም።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ