መጽሐፈ ኢያሱ 22
22
ኢያሱ ከምሥራቅ በኩል የመጡትን ነገዶች ማሰናበቱ
1ከዚህ በኋላ ኢያሱ የሮቤልን፥ የጋድንና በምሥራቅ ያሉትን የምናሴን ነገዶች በአንድነት ጠርቶ፥ 2እንዲህ አላቸው፦ “የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ እንድታደርጉት ያዘዛችሁን ሁሉ ፈጽማችኋል፤ የእኔንም ትእዛዝ ሁሉ ጠብቃችኋል፤ #ዘኍ. 32፥20-32፤ ኢያሱ 1፥12-15። 3በዚህ ጊዜ ሁሉ ወገኖቻችሁን እስራኤላውያንን የከዳችሁበት ጊዜ የለም፤ የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ በጥንቃቄ ፈጽማችኋል። 4እነሆ አሁን አምላካችሁ እግዚአብሔር በገባው የተስፋ ቃል መሠረት ለወገኖቻችሁ ለእስራኤላውያን ሰላምን ሰጥቶአቸዋል፤ ስለዚህ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ ወደ ሰጣችሁ ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተምሥራቅ ወደሚገኘውና ርስት አድርጋችሁ ወደ ወረሳችሁት ምድር ተመልሳችሁ ሂዱ፤ 5ሙሴ የሰጣችሁን ሕግና ትእዛዞች በጥንቃቄ ፈጽሙ፤ ይኸውም አምላካችሁን እግዚአብሔርን ውደዱ፤ ፈቃዱን ፈጽሙ፤ ትእዛዙንም ጠብቁ፤ ለእርሱም ታማኞች ሆናችሁ በሙሉ ልባችሁ፥ በፍጹም ሐሳባችሁ አገልግሉት።” 6ኢያሱም ባርኮ አሰናበታቸውና ወደ ሰፈራቸው ሄዱ፤ 7ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ሙሴ ርስት በባሳን ሰጥቶአቸው ነበር፤ ለእኩሌቶቹ ደግሞ በዮርዳኖስ ምዕራብ በኩል ከወንድሞቻቸው ጋር ኢያሱ መሬት ሰጣቸው፤ ኢያሱም ባሰናበታቸው ጊዜ ባረካቸው፤ 8እንዲህም አላቸው፤ “እነሆ፥ አሁን በምርኮ ያገኛችሁትን ብዙ ከብት፥ ብር፥ ወርቅ፥ ነሐስ፥ ብረትና ብዙ ልብሶች ይዛችሁ ወደ መኖሪያችሁ ልትመልሱ ስለ ሆነ ከጠላቶቻችሁ በምርኮ ያገኛችሁትን ምርኮ ከዘመዶቻችሁ ጋር ተካፈሉ።”
9የሮቤል፥ የጋድና የምናሴ ነገድ እኩሌታ በከነዓን ምድር በሚገኘው በሴሎ ካሉት ከእስራኤላውያን ዘንድ ተነሥተው በሙሴ አማካይነት በእግዚአብሔር ትእዛዝ ወደ ተሰጣቸው ምድር ወደ ገለዓድ ተመለሱ።
በዮርዳኖስ ወንዝ አጠገብ የተሠራ መሠዊያ
10የሮቤል፥ የጋድና የምሥራቅ ምናሴ ነገዶች በዮርዳኖስ ወንዝ አጠገብ በከነዓን ምድር ወደሚገኘው ወደ ገሊሎት እንደ ደረሱ በወንዙ አጠገብ አስደናቂ የሆነ ታላቅ መሠዊያ ሠሩ፤ 11የቀሩትም የእስራኤል ሕዝብ የሮቤል፥ የጋድና በምሥራቅ ያሉት የምናሴ ነገዶች በዮርዳኖስ ወንዝ አጠገብ በከነዓን ምድር በምትገኘው በእስራኤላውያን ይዞታ በሆነችው በገሊሎት መሠዊያ መሥራታቸውን ሰሙ። 12እስራኤላውያን ይህን በሰሙ ጊዜ ሁሉም በአንድነት ወደ ሴሎ መጥተው በመሰብሰብ በምሥራቅ ነገዶች ላይ ሊዘምቱ ተዘጋጁ።
13ይህም ከመሆኑ በፊት የእስራኤል ሕዝብ የካህኑን የአልዓዛርን ልጅ ፊንሐስን በገለዓድ ምድር ወደሚገኙት ወደ ሮቤል፥ ወደ ጋድና በምሥራቅ ወደሚኖሩት የምናሴ ነገዶች ሕዝብ ላኩት፤ 14ከፊንሐስም ጋር ዐሥር ታላላቅ ሰዎች ነበሩ፤ እነዚህም እያንዳንዱ በምዕራብ ከሚገኙት ነገዶች የተውጣጡ በየጐሣቸው የቤተሰብ መሪዎች ናቸው፤ 15እነርሱም የሮቤል፥ የጋድና በምሥራቅ የሚኖሩት የምናሴ ሕዝብ ወደሚኖሩባት ወደ ገለዓድ ምድር መጥተው እንዲህ አሉአቸው፦ 16“የእግዚአብሔር ሕዝብ የሚለው እንዲህ ነው፦ ‘በእስራኤል አምላክ ላይ ያላችሁን እምነት እንዴት ታጓድላላችሁ? ለራሳችሁ መሠዊያ በመሥራት ከእግዚአብሔር ርቃችኋል፤ በእርሱም ላይ ዐምፃችኋል፤ #ዘዳ. 12፥13-14። 17በእግዚአብሔር ማኅበር ላይ መቅሠፍት የወረደበትና እስከ ዛሬ ድረስ ከእርሱ ያልነጻበት የፌጎር ኃጢአት የማይበቃን ሆኖ ነውን? #ዘኍ. 25፥1-9። 18እናንተስ ዛሬ እግዚአብሔርን ለመከተል እምቢ ብላችሁ በእርሱ ላይ ብታምፁ፥ እርሱ ነገ በመላው እስራኤል ላይ ይቈጣል፤ 19አሁን ግን ምድራችሁ የረከሰ ቢሆን የእግዚአብሔር ማደሪያ ወዳለበት ወደ እግዚአብሔር ምድር ተሻገሩ፤ በመካከላችን ርስት ይኑራችሁ፤ ነገር ግን ከእግዚአብሔር መሠዊያ ሌላ በመሥራት በእግዚአብሔር ላይ ወይም በእኛ ላይ አታምፁ። 20የዛራ ልጅ ዓካን መደምሰስ በሚገባቸው ነገሮች እምነተቢስ ሆኖ ትእዛዝ በማፍረሱ የእግዚአብሔር ቊጣ በእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ላይ አልወረደምን? በጥፋቱም የጠፋው እርሱ ብቻ አልነበረም።’ ” #ኢያሱ 7፥1-26።
21የሮቤል፥ የጋድና በምሥራቅ የሚኖሩት የምናሴ ነገዶች ሕዝብም ለምዕራብ ነገዶች የቤተሰብ መሪዎች እንዲህ ሲሉ መለሱላቸው፤ 22“ከሁሉ የሚበልጥ ኀያል እግዚአብሔር ነው! እርሱ የሁሉ ጌታ ነው! እርሱ ከሁሉ የሚበልጥ ኀያል አምላክ ነው! እኛ ስለምን ይህን እንደ ሠራን እርሱ ያውቃል፤ እናንተም ስለምን እንደ ሠራነው እንድታውቁት እንፈልጋለን፤ በእውነት ካመፅንና በእግዚአብሔር ላይ ያለንን እምነት አጓድለን ከተገኘን፥ በሕይወት እንድንኖር አትፍቀዱልን፤ 23ለእግዚአብሔር የማንታዘዝ ከሆንንና የሠራነውን መሠዊያ የሚቃጠል መሥዋዕት፥ የእህል ቊርባን፥ ወይም የአንድነት መሥዋዕት ልናቀርብበት አስበን ከሆነ ራሱ እግዚአብሔር ይቅጣን፤ 24እኛ የሠራነው ለዚህ አይደለም፤ እኛ እርሱን የሠራነው በሚመጡት ዘመናት የእናንተ ዘሮች የእኛን ልጆች ‘እናንተ ከእስራኤል አምላክ ከእግዚአብሔር ጋር ምን ግንኙነት አላችሁ? 25እርሱ በእኛና በእናንተ፥ በሮቤልና በጋድ ሕዝቦች መካከል የዮርዳኖስን ወንዝ መለያ ድንበር አድርጎአል፤ ስለዚህ ከእግዚአብሔር ጋር ምንም ግንኙነት አይኖራችሁም’ ይሉአቸው ይሆናል ብለን በመፍራት ብቻ ነው። በዚህም ዐይነት የእናንተ ዘሮች የእኛን ዘሮች ለእግዚአብሔር እንዳይሰግዱ ይከለክሉአቸው ይሆናል። 26ስለዚህ እኛ የሠራነው መሠዊያ የሚቃጠል ወይም ሌላ መሥዋዕት ለማቅረብ አይደለም። 27እኛ እርሱን የሠራነው በእኛና በእናንተ ሕዝብ መካከል ምልክት ሆኖ እንዲኖር ነው፤ ይኸውም ከእኛ በኋላ ለሚነሡት ትውልዶች በተቀደሰ ድንኳኑ ፊት እግዚአብሔርን እንደምናመልክ የሚቃጠልና ሌላም መሥዋዕት፥ እንዲሁም የአንድነት መሥዋዕት ስናቀርብ ለመኖራችን ምስክር ይሆናል፤ ይኸውም የእናንተ ዘሮች የእኛን ልጆች ‘ከእግዚአብሔር ጋር ምንም ግንኙነት የላችሁም’ እንዳይሉአቸው ለማድረግ ይጠቅማል፤ 28እንግዲህ ምናልባት ይህ ነገር ቢሆን የእኛ ዕቅድ፥ ዘሮቻችን፦ ‘ተመልከቱ! የቀድሞ አባቶቻችን የሠሩት መሠዊያ ለእግዚአብሔር ከተሠራው መሠዊያ ጋር አንድ ዐይነት ነው፤ ይኸውም በእኛና በእናንተ ሕዝቦች መካከል ምልክት ሆኖ እንዲኖር እንጂ የሚቃጠል ወይም ሌላ መሥዋዕት እንዲቀርብበት ታስቦ አልነበረም’ ማለት እንዲችሉ ነው፤ 29እኛ በእግዚአብሔር ላይ አላመፅንም፤ የሚቃጠል መሥዋዕት ወይም የእህል መባ፥ ወይም ሌላ መሥዋዕት ለማቅረብ አስበን ሌላ መሠዊያ በመሥራት እግዚአብሔርን ማምለክ አልተውንም፤ ከእግዚአብሔር ድንኳን ፊት ለፊት ከቆመው ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ከተሠራው ሌላ የተለየ መሠዊያ መሥራት ከእኛ ይራቅ።”
30ካህኑ ፊንሐስና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሕዝቡ የላካቸው የምዕራብ ነገዶች የቤተሰብ አለቆች የሆኑት ታላላቅ ሰዎች፥ የሮቤል፥ የጋድና በምሥራቅ በሚኖሩ የምናሴ ነገዶች ሕዝብ የተናገሩትን ሰምተው መልሱ አረካቸው፤ 31ስለዚህም የአልዓዛር ልጅ ካህኑ ፊንሐስ እንዲህ አላቸው፤ “እነሆ፥ አሁን እግዚአብሔር ከእኛ ጋር መሆኑን ዐወቅን፤ እናንተ በእርሱ ላይ አላመፃችሁም፤ ስለዚህም የእስራኤልን ሕዝብ ከእግዚአብሔር ቅጣት አድናችኋል።”
32ከዚህም በኋላ የካህኑ የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስና መሪዎቹ በገለዓድ ከሚገኙት ከሮቤልና ከጋድ ሕዝቦች ዘንድ በከነዓን ምድር ወደሚገኙት ወደ እስራኤል ሕዝብ ተመልሰው በመምጣት፥ ያገኙትን ማስረጃ አቀረቡ፤ 33እስራኤላውያንም በመልሱ ረክተው እግዚአብሔርን አመሰገኑ፤ ከዚያም በኋላ የሮቤልና የጋድ ሕዝብ የሚኖሩባትን ምድር ለመደምሰስ ጦርነት ስለ ማንሣት ጉዳይ መናገር አልፈለጉም።
34የሮቤልና የጋድ ሕዝብም “ይህ መሠዊያ እግዚአብሔር ብቻ አምላክ ስለ መሆኑ ለሁላችን ምስክር ነው” አሉ፤ ከዚህም የተነሣ “ምስክር” ብለው ጠሩት።
Currently Selected:
መጽሐፈ ኢያሱ 22: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997