የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

የማቴዎስ ወንጌል 28

28
የኢየሱስ ከሞት መነሣት
(ማር. 16፥1-10ሉቃ. 24፥1-12ዮሐ. 20፥1-10)
1ሰንበት ካለፈ በኋላ ከሳምንቱ በመጀመሪያው ቀን (እሑድ) ጠዋት፥ በማለዳ መግደላዊት ማርያምና ሌላይቱ ማርያም መቃብሩን ለማየት ሄዱ። #28፥1 ሰንበት፦ እዚህ ላይ ሰንበት የተባለው ቅዳሜ ነው። 2እነሆ፥ በድንገት ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ የጌታ መልአክ ከሰማይ ወርዶ መቃብሩ የተዘጋበትን ድንጋይ አንከባለለና በላዩ ተቀመጠ። 3የመልአኩ ፊት እንደ መብረቅ ያበራ ነበር፤ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ነበረ። 4ጠባቂዎቹ መልአኩን ከመፍራት የተነሣ በመንቀጥቀጥ እንደ በድን ሆኑ፤ 5መልአኩ ግን ሴቶቹን እንዲህ አላቸው፤ “እናንተስ አትፍሩ፤ የተሰቀለውን ኢየሱስን እንደምትፈልጉ ዐውቃለሁ፤ 6እርሱ እዚህ የለም ቀደም ብሎ እንደ ተናገረው ተነሥቶአል። እዚህ የለም፤ ተቀብሮበት የነበረበትን ስፍራ ኑና እዩ። 7እንግዲህ በፍጥነት ሄዳችሁ ለደቀ መዛሙርቱ ‘ከሞት ተነሥቶአል! እነሆ፥ ወደ ገሊላ ቀድሞአችሁ ይሄዳል፤ በዚያ ታገኙታላችሁ!’ ብላችሁ ንገሩአቸው፤ እነሆ፥ ነግሬአችኋለሁ።” 8ከዚህ በኋላ ሴቶቹ በፍርሃትና በታላቅ ደስታ ከመቃብሩ በፍጥነት ሄዱ፤ ለደቀ መዛሙርቱም ሊነግሩ ሮጡ።
9ኢየሱስ በመንገድ አገኛቸውና “ሰላም ለእናንተ ይሁን!” አላቸው። እነርሱም ወደ እርሱ ቀረቡና እግሮቹን ይዘው ሰገዱለት። 10በዚያን ጊዜ ኢየሱስ፦ “አትፍሩ! ሂዱና ወደ ገሊላ እንዲሄዱ ለወንድሞቼ ንገሩአቸው፤ የሚያዩኝም በዚያ ነው” አላቸው።
11ሴቶቹም ሲሄዱ ሳሉ ከወታደሮቹ አንዳንዶቹ ወደ ከተማ ሄደው የሆነውን ነገር ሁሉ ለካህናት አለቆች ነገሩ። 12የካህናት አለቆች ከሽማግሌዎች ጋር ተሰብስበው ከተማከሩ በኋላ ለወታደሮቹ ብዙ ገንዘብ ሰጡአቸውና እንዲህ አሉአቸው፤ 13“ ‘እኛ ተኝተን ሳለ ደቀ መዛሙርቱ በሌሊት መጥተው ሰርቀው ይዘውት ሄዱ’ ብላችሁ ለሕዝቡ ንገሩ። 14ይህን አገር ገዢው የሰማ እንደ ሆነ እኛ ጉዳዩን ለእርሱ አስረድተን በማሳመን በእናንተ ላይ ችግር እንዳይደርስባችሁ እናደርጋለን። ” 15ስለዚህ ወታደሮቹ ገንዘቡን ተቀብለው ልክ እንደ ተነገራቸው አደረጉ፤ ይህም ነገር እስከ ዛሬ ድረስ በአይሁድ ዘንድ ተስፋፍቶ ይነገራል።
ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንደ ተገለጠ
(ማር. 16፥14-18ሉቃ. 24፥36-49ዮሐ. 20፥19-23ሐ.ሥ. 1፥6-81ቆሮ. 15፥3-8) #ማቴ. 26፥32ማር. 14፥28
16ዐሥራ አንዱ ደቀ መዛሙርት ኢየሱስ እንዲሄዱ ወደ አመለከታቸው፥ በገሊላ ወደሚገኘው ተራራ ሄዱ። 17ባዩትም ጊዜ ሰገዱለት፤ አንዳዶቹ ግን ተጠራጠሩ፤ 18ኢየሱስ ወደ እነርሱ ቀረበና እንዲህ አላቸው፤ “ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጥቶኛል፤ 19እንግዲህ ወደ ዓለም ሕዝብ ሁሉ ሂዱ፤ በአብ፥ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው የእኔ ደቀ መዛሙርት አድርጉአቸው። #ሐ.ሥ. 1፥8። 20ያዘዝኳችሁንም ሁሉ እንዲፈጽሙ አስተምሩአቸው! እነሆ፥ እኔም እስከ ዓለም መጨረሻ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ