ኦሪት ዘኊልቊ 15
15
ስለ መሥዋዕት አቀራረብ የተሰጠ ተጨማሪ ሕግ
1እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ 2“ለእስራኤላውያን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘እንድትኖሩባት ልሰጣችሁ ወዳቀድኩት ምድር በምትገቡበት ጊዜ፥ 3ለሚቃጠል መሥዋዕት ወይም ስለ ስእለት መፈጸም ለሚቀርብ መሥዋዕት ወይም በበጎ ፈቃድ ለሚቀርብ መሥዋዕት ወይም በተለመዱት የሃይማኖት በዓላት ላይ ለሚቀርብ መሥዋዕት፥ ከከብት ወይም ከበግ መንጋዎች ለእግዚአብሔር ታቀርባላችሁ፤ እንደዚህ ያለውም የምግብ ቊርባን መዓዛው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ይሆናል፤ 4እንግዲህ እንደዚህ ያለውን መሥዋዕት የሚያቀርብ ሰው ሁሉ በሩብ ሊትር ዘይት የተለወሰ አንድ ኪሎ ምርጥ ዱቄት የእህል ቊርባንም ማቅረብ አለበት፤ 5እንዲሁም ለያንዳንዱ ጠቦት ለመጠጥ ቊርባን የሚሆን ሩብ ሊትር የወይን ጠጅ ከሚቃጠል ቊርባን ወይም መሥዋዕት ጋር ታቀርባላችሁ። 6አውራ በግ መሥዋዕት ሆኖ በሚቀርብበት ጊዜ ደግሞ በአንድ ሊትር ተኩል የወይራ ዘይት የተለወሰ ሁለት ኪሎ ዱቄት አቅርቡ፤ 7ለመጠጥ ቊርባን የሊትር አንድ ሦስተኛ የወይን ጠጅ ታቀርባለህ፤ ይህም ሁሉ መሥዋዕት መዓዛው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ይሆናል፤ 8ስለ ስእለት ወይም ስለ አንድነት አንድ ወይፈን ለሚቃጠል ቊርባን ወይም መሥዋዕት በምታቀርብበት ጊዜ፥ 9ከወይፈኑ ጋር ሦስት ኪሎ በግማሽ ሊትር ዘይት የተለወሰ ምርጥ ዱቄት የእህል ቊርባን አቅርብ። 10እንዲሁም ግማሽ ሊትር የወይን ጠጅ የመጠጥ ቊርባን አድርገህ ታቀርባለህ፤ ይህም ለእግዚአብሔር መልካም መዓዛ የሚሆን የሚቃጠል መሥዋዕት ነው።
11“ ‘እንግዲህ ከእያንዳንዱ ወይፈን፥ አውራ በግ፥ የበግ ወይም የፍየል ጠቦት ጋር የሚቀርበው የእህል ቊርባን ይህ ነው፥ 12ከአንድ እንስሳ በላይ በሚቀርብበት ጊዜ አብሮት የሚቀርበውም የእህል ቊርባን በተመሳሳይ ሁኔታ ይጨምራል፤ 13የአገር ተወላጅ የሆነ እያንዳንዱ እስራኤላዊ መዓዛው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ የእህል ቊርባን በሚያቀርብበት ጊዜ ይህን ሁሉ ማድረግ ይኖርበታል፤ 14ከእናንተ ጋር ያለ ወይም በመካከላችሁ የሚኖር መጻተኛ መዓዛው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ የምግብ ቊርባን ለእግዚአብሔር ለማቅረብ ቢፈልግ፥ ይህንኑ የሥርዓት መመሪያ በተመሳሳይ ሁኔታ መከተል ይኖርበታል። 15እናንተም ሆናችሁ በመካከላችሁ የሚኖሩ መጻተኞች ለሚመጡት ዘመናት ሁሉ እነዚህን የሥርዓት መመሪያዎች በተመሳሳይ ሁኔታ መጠበቅ ይኖርባችኋል፤ እናንተም ሆናችሁ እነርሱ በእግዚአብሔር ፊት አንድ ናችሁ። 16ማንኛውም ሕግና የሥርዓት መመሪያ ለሁላችሁም እኩል ነው።’ ” #ዘሌ. 24፥22።
17እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ 18“ለእስራኤላውያን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ እኔ ወደምመራችሁ ምድር በምትገቡበት ጊዜ፥ 19ከምድሪቱ የሚመረተውን ነገር ሁሉ በምትመገቡበት ወቅት ከእርሱ ላይ ጥቂት በማንሣት ለእግዚአብሔር ልዩ ስጦታ አድርጋችሁ አቅርቡ፤ 20ይኸውም ከአዲስ እህል የተጋገረው የመጀመሪያው ኅብስት ለእግዚአብሔር ልዩ መባ ሆኖ ይቅረብ፤ ይህም ከምትወቁት እህል በማንሣት እንደምታመጡት ልዩ መባ በተመሳሳይ ይቅረብ፤ 21ለሚመጡት ዘመናት ሁሉ ከአዲስ እህል ከምትጋግሩት ኅብስት እየተነሣ ለእግዚአብሔር ልዩ መባ ሆኖ መቅረብ አለበት።
22“ምናልባት እናንተ ሆን ብላችሁ ሳይሆን ባለማወቅ እግዚአብሔር ለሙሴ ከሰጠው ትእዛዞች መካከል አንዱን ሳትጠብቁ ብትቀሩ፥ 23ወይም ምናልባት ወደፊት ዘሮቻችሁ በሙሴ አማካይነት ያዘዘውን ትእዛዝ ሁሉ ሳይፈጽሙ ቢቀሩ፥ 24እንዲህ ዐይነቱ ስሕተት የተፈጸመው በማኅበሩ አለማወቅ ከሆነ አንድ ወይፈን አምጥተው መዓዛው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገው ያቅርቡት፤ ከእርሱም ጋር ተገቢውን የእህልና የወይን ጠጅ ቊርባን ያቅርቡ፤ በተጨማሪም አንድ ተባዕት ፍየል ስለ ኃጢአት ስርየት መሥዋዕት አድርገው ያቅርቡ። 25ካህኑም ለመላው የእስራኤል ማኅበር ያስተስርይላቸው፤ ስሕተቱን የፈጸሙት ባለማወቅ ስለ ሆነና ስለ ኃጢአት ስርየት የሚሆነውንም መሥዋዕትና የእህል ቊርባን አድርገው ለእግዚአብሔር ስላቀረቡ፥ ኃጢአታቸው ይቅር ይባልላቸዋል። 26ሁሉም በአንድነት የስሕተቱ ተካፋዮች ስለ ሆኑ መላው የእስራኤል ማኅበርና በእነርሱም መካከል የሚኖሩ መጻተኞች ኃጢአታቸው ይቅር ይባልላቸዋል።
27“አንድ ሰው በግሉ ባለማወቅ ኃጢአት ቢሠራ አንድ ዓመት የሞላት እንስት ፍየል ስለ ኃጢአቱ ስርየት መሥዋዕት አድርጎ ያቅርብ። 28ካህኑ በስሕተት ኃጢአት ለሠራው ሰው በእግዚአብሔር ፊት ያስተስርይለት፤ ኃጢአቱም ይቅር ይባልለታል። #ዘሌ. 4፥27-31። 29የአገር ተወላጅ እስራኤላዊም ሆነ ወይም በዚያ የሚኖር መጻተኛ ባለማወቅ ኃጢአት የሚሠራ ሁሉ የሚከተለው ሕግ ይኸው ነው።
30“ነገር ግን የአገሩ ተወላጅም ሆነ መጻተኛ፥ ሆን ብሎ ኃጢአት የሚሠራ ሁሉ በእግዚአብሔር ላይ የንቀት ዝንባሌ በማሳየቱ ከሕዝቡ ይለይ፤ 31ይህም የሚደርስበት እግዚአብሔር የተናገረውን ችላ ስላለና ከትእዛዞቹም አንዱን ሆን ብሎ ስለ ጣሰ ነው፤ ስለዚህ ያ ሰው ፈጽሞ ይጥፋ፤ ኀላፊነቱ የራሱ ነው።”
ሰንበትን በመሻር የተቀጣው ሰው
32እስራኤላውያን በምድረ በዳ ሳሉ አንድ ጊዜ አንድ ሰው በሰንበት ቀን የማገዶ እንጨት ሲለቅም ተያዘ፤ 33የያዙትም ሰዎች መላው ማኅበር ወዳለበት ወደ ሙሴና ወደ አሮን ወሰዱት። 34በእርሱ ላይ የሚወሰደው እርምጃ ግልጥ ሆኖ ስላልተገኘ ለጊዜው በዘብ ተጠብቆ እንዲቈይ ተደረገ፤ 35ከዚያን በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን “ሰውየው መገደል አለበት፤ መላው ማኅበር ከሰፈር አውጥተው በድንጋይ ወግረው ይግደሉት” አለው። 36ስለዚህ መላው ማኅበር ከሰፈር አውጥተው እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት በድንጋይ ወግረው ገደሉት።
ስለ ልብስ ዘርፍ የተሰጠ መመሪያ
37እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ 38“ለእስራኤላውያን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘በልብሶቻችሁ ጫፍ ላይ ሁሉ ዘርፍ አብጁ፤ እያንዳንዱም ዘርፍ ከሰማያዊ ፈትል የተሠራ ጥለት ይኑረው፤ ይህንንም ለሚመጡት ዘመናት ሁሉ አድርጉ፤ #ዘዳ. 22፥12። 39ዘርፎቹም እንደማስታወሻ ሆነው ስለሚያገለግሉ፥ እነርሱን በምታዩበት ጊዜ ሁሉ ትእዛዞቼን በማስታወስ ትፈጽማላችሁ፤ ከእኔም ርቃችሁ የገዛ ፈቃዳችሁንና ምኞታችሁን የምትፈጽሙ አትሆኑም፤ 40በልብሶቻችሁም ጫፍ ላይ የሚታዩት ዘርፎች ትእዛዞቼን ሁሉ እንድትፈጽሙ ያስታውሱአችኋል፤ እናንተም በፍጹም ለእኔ የተገዛችሁ ትሆናላችሁ። 41እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ፤ አምላካችሁ እሆን ዘንድ ከግብጽ ምድር ያወጣኋችሁ፥ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።’ ”
Currently Selected:
ኦሪት ዘኊልቊ 15: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997