ኦሪት ዘኊልቊ 20
20
ጌታ ለሕዝቡ ከአለት ላይ ውሃ ማፍለቁ
(ዘፀ. 17፥1-7)
1በመጀመሪያው ወር መላው የእስራኤል ማኅበር ወደ ጺን ምድረ በዳ መጥተው በቃዴስ ሰፈሩ፤ ማርያምም ስለሞተች በዚያው ተቀበረች።
2በሰፈሩበት ቦታ ውሃ አልነበረም፤ ስለዚህ ሕዝቡ ሙሴንና አሮንን በመቃወም ተሰብስበው፥ 3እንዲህ በማለት ከሙሴ ጋር ተጣሉ፦ “በእግዚአብሔር ድንኳን ፊት ለፊት ከቀሩት እስራኤላውያን ወገኖቻችን ጋር ሞተን ቢሆን መልካም በሆነ ነበር። 4የእግዚአብሔርን ማኅበር ወደዚህ ምድረ በዳ ያመጣችሁት እኛና እንስሶቻችን እዚህ እንድናልቅ ለማድረግ ነውን? 5ከግብጽ አውጥታችሁ ምንም ነገር ወደማይበቅልበት ወደዚህ አስከፊ ምድር ለምን አመጣችሁን? በዚህ ስፍራ እህል፥ በለስ፥ ወይንና ሮማን አይገኝም፤ ሌላው ቀርቶ የሚጠጣ ውሃ እንኳ የለም!” 6ሙሴና አሮን ከሕዝቡ ፈቅ ብለው ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ሄዱ፤ በግንባራቸው ወደ መሬት ተደፍተው ሳሉም የእግዚአብሔር ክብር ተገለጠላቸው።
7እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ 8“በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት ለፊት ያለውን በትር ወስደህ አንተና አሮን ሆናችሁ መላውን ማኅበር በአንድነት ሰብስቡ፤ እዚያም በእነርሱ ሁሉ ፊት ሆነህ ያንን አለት ውሃውን እንዲያወጣ እዘዘው፤ በዚህ ዐይነት ከአለቱ ውስጥ ውሃ ታወጣላቸዋለህ፤ እንዲሁም እነርሱና እንስሶቻቸውም ጠጥተው ይረካሉ።” 9ሙሴም እግዚአብሔር እንዳዘዘው ከድንኳኑ ውስጥ በትሩን አመጣ።
10እርሱና አሮን መላውን ማኅበር በአለቱ ፊት ለፊት እንዲሰበሰቡ ካደረጉ በኋላ ሙሴ ሕዝቡን “እናንተ ዐመፀኞች! ከዚህ አለት ለእናንተ ውሃ እናውጣላችሁን?” አላቸው። 11ከዚህ በኋላ ሙሴ በትሩን አንሥቶ አለቱን ሁለት ጊዜ መታው፤ ታላቅ የውሃ ምንጭም ከውስጡ ፈሰሰ፤ ሕዝቡና እንስሶቹም ሁሉ ጠጡ።
12ነገር ግን እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን እንዲህ ሲል ገሠጻቸው፤ “በእስራኤላውያን ፊት የተቀደሰ ክብሬን ትገልጡ ዘንድ ስላላመናችሁብኝ፥ ልሰጣቸው ቃል ወደገባሁላቸው ምድር የዚህ ሕዝብ መሪዎች ሆናችሁ አትገቡም።”
13የእስራኤል ሕዝብ ከእግዚአብሔር ጋር የተጣሉበትና እርሱም የቅድስናውን ክብር የገለጠበት ስፍራ መሪባ ስለ ተባለ ውሃውም የመሪባ ውሃ ነው።
እስራኤላውያን በኤዶም በኩል ማለፍ መከልከላቸው
14ሙሴ ለኤዶም ንጉሥ እንዲህ ብለው እንዲነግሩት መልእክተኞችን ከቃዴስ ላከ፤ “ወንድምህ እስራኤል እንዲህ ይላል፦ በእኛ ላይ የደረሰውን ችግር ሁሉ ሰምተሃል፤ 15የቀድሞ አባቶቻችን እንዴት ወደ ግብጽ እንደ ወረዱና እኛም በግብጽ ለብዙ ዓመቶች እንዴት እንደ ኖርን ታውቃለህ፤ ግብጻውያን የቀድሞ አባቶቻችንም ሆነ እኛን በብርቱ አሠቃይተዋል፤ 16እኛም ይረዳን ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጮኽን፤ እርሱም ጩኸታችንን ሰምቶ ከግብጽ የሚያወጣንን መልአክ ላከልን፤ እነሆ አሁን እኛ በግዛትህ ወሰን ላይ ባለችው በቃዴስ እንገኛለን። 17ስለዚህ በምድርህ አልፈን እንድንሄድ እባክህ ፍቀድልን፤ እኛም ሆንን ከብቶቻችን ከመንገድ ውጪ አንወጣም፤ ወደ እርሻዎችህም ሆነ ወደ ወይን ተክሎችህ አንገባም፤ ከውሃ ጒድጓዶችህም አንጠጣም፤ ግዛትህን እስክናልፍ ድረስ ከዋናው መንገድ አንወጣም።”
18ኤዶማውያን ግን እንዲህ አሉ፤ “በአገራችን አልፋችሁ እንድትሄዱ አንፈቅድላችሁም! ለመግባት ብትሞክሩ ግን በሰልፍ ወጥተን እንወጋችኋለን።”
19የእስራኤል ሕዝብም “እኛ ከዋናው መንገድ አንወጣም፤ እኛ ወይም እንስሶቻችን ከውሃችሁ ብንጠጣ እንኳ ዋጋ እንከፍላችኋለን፤ እኛ የምንፈልገው በምድራችሁ አልፈን መሄድ ብቻ ነው” ሲሉ መለሱላቸው።
20ኤዶማውያን ግን “አይሆንም! አናሳልፋችሁም!” አሉ፤ ብርቱ የጦር ሠራዊትም አሰልፈው የእስራኤልን ሕዝብ ሊወጉ ወጡ። 21ኤዶማውያን እስራኤላውያን በግዛታቸው አልፈው እንዳይሄዱ በመከልከላቸው ምክንያት እስራኤላውያን መንገድ ለውጠው በሌላ በኩል ሄዱ።
የአሮን ሞት
22መላው የእስራኤል ማኅበር ከቃዴስ ተነሥተው በመጓዝ ወደ ሖር ተራራ ደረሱ፤ 23ይህም በኤዶም ወሰን ላይ የሚገኝ ስፍራ ነው፤ እዚያም እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፤ 24“አሮን ለእስራኤላውያን ልሰጣቸው ቃል ወደገባሁላቸው ምድር አይገባም፤ እናንተ ሁለታችሁ በመሪባ ውሃ ዘንድ በትእዛዜ ላይ ስላመፃችሁ አሮን ይሞታል። 25አሮንንና ልጁን አልዓዛርን ይዘህ ወደ ሖር ተራራ ውጣ። 26እዚያም የአሮንን የክህነት ልብስ አውልቀህ አልዓዛርን አልብሰው፤ አሮንም በዚያ ይሞታል።” 27ሙሴም እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ አደረገ፤ መላው ማኅበር እየተመለከታቸው ወደ ሖር ተራራ ወጡ፤ 28ሙሴም የአሮንን የክህነት ልብስ አውልቆ አልዓዛርን አለበሰው፤ እዚያም በተራራው ጫፍ ላይ አሮን ሞተ፤ ሙሴና አልዓዛርም ተመልሰው ከተራራው ወረዱ፤ #ዘፀ. 29፥29፤ ዘኍ. 33፥38፤ ዘዳ. 10፥6። 29መላው ማኅበር አሮን እንደ ሞተ ሰሙ፤ እስከ ሠላሳ ቀንም ድረስ በሐዘን አለቀሱለት።
Currently Selected:
ኦሪት ዘኊልቊ 20: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997