ኦሪት ዘኊልቊ 21
21
በከነዓናውያን ላይ የተገኘ ድል
1መኖሪያው ኔጌብ የነበረ የከነዓናውያን ንጉሥ ዐራድ እስራኤላውያን በአታሪም በኩል መምጣታቸውን በሰማ ጊዜ በእነርሱ ላይ አደጋ ጥሎ ጥቂቶቹን ማረከ። #ዘኍ. 33፥40። 2በዚያን ጊዜ እስራኤላውያን “ይህን ሕዝብ ድል እንድንነሣው ብትረዳን፥ እነርሱንም ሆኑ ከተሞቻቸውን ዳግመኛ እንዳያንሰራሩ አድርገን በፍጹም እንደመስሳቸዋለን” በማለት ለእግዚአብሔር ተሳሉ። 3እግዚአብሔርም ልመናቸውን ሰምቶ ስለ ረዳቸው ከነዓናውያንን ድል ነሥተው ያዙ፤ ስለዚህ እስራኤላውያን እነርሱንና ከተሞቻቸውን ፈጽመው ደመሰሱ፤ ፈጽሞ የተደመሰሱ መሆናቸውንም ለማመልከት ያን ስፍራ “ሖርማ” ብለው ሰየሙት። #21፥3 ሖርማ፦ በዕብራይስጥ እርም አደረገ ወይም ደመሰሰ ማለት ነው።
ከነሐስ የተሠራው እባብ
4እስራኤላውያን በኤዶም ግዛት ዙሪያ ለመሄድ አስበው ከሖር ተራራ ተነሥተው ወደ ቀይ ባሕር በሚወስደው መንገድ ተጓዙ፤ ነገር ግን በመንገድ ሳሉ የሕዝቡ ትዕግሥት አለቀ፤ #ዘዳ. 2፥1። 5በእግዚአብሔርና በሙሴም ላይ ክፉ ቃል በመናገር እንዲህ ሲሉ አጒረመረሙ፤ “ምግብና ውሃ በሌለበት በዚህ በረሓ እንሞት ዘንድ ከግብጽ ምድር ለምን አወጣችሁን? ይህን አስከፊ ምግብ ሰውነታችን ተጸይፎታል!” 6ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር መርዘኛ እባብ ወደ ሕዝቡ ስለ ላከ ብዙ እስራኤላውያን ተነድፈው ሞቱ። #1ቆሮ. 10፥9። 7ሕዝቡም ወደ ሙሴ መጥተው፥ “በእግዚአብሔርና በአንተ ላይ ክፉ ቃል በመናገራችን በድለናል፤ አሁንም እነዚህ ተናዳፊ እባቦች ከእኛ እንዲወገዱ ወደ እግዚአብሔር ጸልይልን” አሉት፤ ሙሴም ለሕዝቡ ጸለየ። 8በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር ሙሴን “አንድ የነሐስ እባብ ሠርተህ በረዥም ትክል እንጨት ላይ ስቀለው፤ በእባብ የተነከሰ ሁሉ እርሱን በሚያይበት ጊዜ ይድናል” አለው። 9ሙሴም የነሐስ እባብ ሠርቶ በእንጨት ላይ ሰቀለው፤ በእባብ የተነከሰም ሁሉ ወደ ነሐሱ እባብ ቀና ብሎ ሲመለከት ዳነ። #2ነገ. 18፥4፤ ዮሐ. 3፥14።
ከሖር ተራራ ወደ ሞአባውያን ሸለቆ የተደረገ ጒዞ
10እስራኤላውያን ጒዞአቸውን ቀጥለው በኦቦት ሰፈሩ፤ 11ያንንም ስፍራ ከለቀቁ በኋላ ከሞአባውያን ግዛት በስተ ምሥራቅ ባለው በረሓ ውስጥ በተለይ “ዐባሪም” ተብሎ በሚጠራው ቦታ ሰፈሩ። 12ከዚያም አልፈው በዘሬድ ሸለቆ ሰፈሩ። 13ከዚያም ተጒዘው እስከ አሞራውያን ግዛት በሚዘልቀው ምድረ በዳ ከአርኖን ወንዝ ማዶ በሚገኘው ቦታ ሰፈሩ፤ የአርኖን ወንዝ በሞአባውያንና በዐሞራውያን ግዛት ወሰን ላይ የሚገኝ ነው። 14ከዚህም የተነሣ በእግዚአብሔር መሪነት ስለ ተደረገው ጦርነት በሚናገር የታሪክ መጽሐፍ እንዲህ ተብሎአል፦ “በሱፋ ክልልና በሸለቆዎች ውስጥ የሚገኘው ዋሄብ፥ የአርኖን ወንዝ፥ 15እስከ ዔር ከተማና እስከ ሞአብ ወሰን የሚዘልቁት ሸለቆዎች ሸንተረር” 16ከዚያም ተነሥተው “የውሃ ጒድጓዶች” ወደ ተባለው ስፍራ ሄዱ፤ በእዚያም እግዚአብሔር ሙሴን “ሕዝቡን በአንድነት ሰብስባቸውና ውሃ እሰጣቸዋለሁ” አለው። 17በዚያን ጊዜ እስራኤላውያን ይህን መዝሙር ዘመሩ “ጒድጓድ ሆይ፥ ውሃ አፍልቅ፤
ለእርሱም ዘምሩለት
18የውሃ ጒድጓዱን የቈፈሩት፥
መሳፍንትና የሕዝብ አለቆች ናቸው፤
እነርሱም የውሃ ጒድጓዱን የቈፈሩት
በበትረ መንግሥታቸውና በከዘራቸው ነው።”
ከዚያም ምድረ በዳ ተነሥተው ወደ ማታና ተጓዙ፤ 19ከማታናም ወደ ናሕሊኤል፥ ከናሕሊኤልም ወደ ባሞት ዘለቁ፤ 20ከባሞትም ተነሥተው በሞአባውያን ግዛት ውስጥ ወዳለው ሸለቆ ተጓዙ፤ ይህም ሸለቆ የሚገኘው ከፒስጋ ተራራ ግርጌ በበረሓው ትይዩ ነው።
የንጉሥ ሲሖንና የንጉሥ ዖግ ድል መመታት
(ዘዳ. 2፥26—3፥11)
21ከዚህ በኋላ የእስራኤል ሕዝብ ወደ አሞራውያን ንጉሥ ሲሖን እንዲህ ብለው የሚነግሩትን መልእክተኞች ላኩ፤ 22“በምድርህ አልፈን እንድንሄድ ፍቀድልን፤ እኛና ከብቶቻችን ከመንገዱ አንወጣም፤ ወደ እርሻዎችህም ሆነ ወደ ወይን ተክሎችህ አንገባም፤ ከውሃ ጒድጓዶችህም ውሃ አንጠጣም፤ ከግዛትህ እስክንወጣ ድረስ ዋናውን መንገድ አንለቅም።” 23ሲሖን ግን የእስራኤል ሕዝብ በግዛቱ አልፈው እንዲሄዱ አልፈቀደላቸውም፤ እንዲያውም ሠራዊቱን ሁሉ ሰብስቦ በበረሓ ውስጥ ወዳለችው ወደ ያሀጽ በመሄድ በእስራኤላውያን ላይ ጦርነት አደረገ። 24እስራኤላውያን ግን ድል ነሡአቸው፤ ከአርኖን ወንዝ አንሥቶ በስተሰሜን እስከ ዐሞናውያን ወሰን ማለትም እስከ ያቦቅ ወንዝ ድረስ የሚገኘውን ግዛት ያዙ፤ ይሁን እንጂ የዐሞናውያን ወሰን በብርቱ የተጠበቀ በመሆኑ ወደዚያ አልገቡም። 25በዚህ ዐይነት የእስራኤል ሕዝብ የአሞራውያንን ከተሞች ሐሴቦንንና በዙሪያ ያሉትን ታናናሽ ከተሞች ጭምር ይዘው በዚያ ተቀመጡ፤ 26ሐሴቦን የአሞራውያን ንጉሥ ሲሖን መናገሻ ከተማ ነበረች፤ እርሱም ከሞአብ የቀድሞ ንጉሥ ጋር ተዋግቶ እስከ አርኖን ወንዝ ያለውን ምድር ሁሉ ወስዶበት ነበር። 27ከዚህም የተነሣ ባለቅኔዎች እንኳ እንዲህ እያሉ ይቀኙ ነበር፦
“ወደ ሐሴቦን ኑ! ይህች ከተማ ትገንባ!
የሲሖን ከተማ ትመሥረት፤
28ከሐሴቦን እሳት ወጣ፤
ነበልባልም ከሲሖን ከተማ፥
የሞአብን ዔር አጠፋ
የአርኖንንም ከፍተኛ ቦታዎች ደመሰሰ።
29ሞአብ ሆይ! ወዮልሽ!
እናንተ የከሞሽ ሰዎች ሆይ! ትደመሰሳላችሁ፤
ወንዶች ልጆቹን ስደተኞች እንዲሆኑ አደረጋቸው፤
ሴቶች ልጆቹንም ንጉሥ ሲሖን እንዲማረኩ አደረገ። #ኤር. 48፥45-46።
30ስለዚህ ዘሮቻቸው ተደመሰሱ
ከሐሴቦን እስከ ዲቦን፥
እሳቱ እስከ ሜዴባ እስኪስፋፋ ድረስ አጠፋናቸው።”
31ስለዚህ የእስራኤል ሕዝብ በአሞራውያን ግዛት ውስጥ ተቀመጡ፤ 32ሙሴም ያዕዜርን የሚሰልሉ ሰዎች ላከ፤ እስራኤላውያንም ከተማይቱንና በዙሪያዋ ያሉትን ታናናሽ ከተሞች ያዙ፤ በዚያም ይኖሩ የነበሩትን አሞራውያን አባረሩ።
ንጉሥ ዖግ ተሸነፈ
33ከዚያም በኋላ እስራኤላውያን ተመልሰው ወደ ባሳን የሚወስደውን መንገድ ተከትለው ሄዱ፤ የባሳን ንጉሥ ዖግ በኤድረዒ ከእነርሱ ጋር ጦርነት ለመግጠም ከመላ ሠራዊቱ ጋር ወጣ። 34እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ይህን ሰው አትፍራው፤ በእርሱና በሕዝቡ በምድሪቱም ላይ ድል እንድትጐናጸፍ አደርግሃለሁ፤ በሐሴቦን ሆኖ ይገዛ በነበረው በአሞራውያን ንጉሥ በሲሖን ላይ ያደረግኸውን ሁሉ በዚህም ላይ አድርግበት።” 35ስለዚህ እስራኤላውያን ዖግን፥ ልጆቹን፥ ሕዝቡን ሁሉ አንድም ሳያስቀሩ ፈጅተው ምድሩን ወረሱ።
Currently Selected:
ኦሪት ዘኊልቊ 21: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997