ኦሪት ዘኊልቊ 26
26
ሁለተኛው የሕዝብ ቈጠራ
1መቅሠፍቱ ከቆመ በኋላ እግዚአብሔር ሙሴንና የካህኑን የአሮንን ልጅ አልዓዛርን እንዲህ አላቸው፤ 2“በመላው የእስራኤል ማኅበር በየቤተሰቡ ዕድሜአቸው ኻያ ዓመት የሞላቸውንና ከዚያም በላይ የሆኑትን፥ ወታደር ሆነው ለማገልገል ብቃት ያላቸውን ወንዶች ልጆች ሁሉ ቊጠሩ።” 3ሙሴና ካህኑ አልዓዛር በዮርዳኖስ አጠገብ ከኢያሪኮ ትይዩ ባለው የሞአብ ሜዳ ሕዝቡን ሰብስበው እንዲህ አሉአቸው፦ 4“እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ኻያና ከኻያ ዓመት በላይ ዕድሜ ያላቸውን ሰዎች ሁሉ ቈጠሩ።”
ከግብጽ ምድር የወጡትም እስራኤላውያን እነዚህ ነበሩ፦
5የያዕቆብ የበኲር ልጅ የሮቤል ነገድ ተወላጆች ሐኖክ፥ ፋሉስ፥ #ዘኍ. 1፥1-46። 6ሔጽሮን፥ ከርሚና የእነርሱ ተወላጆች ናቸው። 7ከሮቤል ነገድ የጐሣ መሪዎች የተቈጠሩት ጠቅላላ ቊጥር አርባ ሦስት ሺህ ሰባት መቶ ሠላሳ ነበር፤ 8የፋሉ ዘሮችም ኤሊአብና 9የኤሊአብ ልጆች ነሙኤል፥ ዳታንና አቤሮን ነበሩ፤ ዳታንና አቤሮንም በማኅበሩ ተመርጠው የነበሩት ሲሆኑ እነርሱም ከቆሬና ከተከታዮቹ ጋር ተባብረው በእግዚአብሔር ላይ ባመፁ ጊዜ ሙሴንና አሮንን የተፈታተኑአቸው ናቸው። 10እነርሱንም ምድር ተከፍታ ከቆሬ ጋር ዋጠቻቸው፤ እነርሱም በሞቱ ጊዜ እሳት ወርዶ ሁለት መቶ ኀምሳውን ሰዎች አቃጠላቸው፤ ለሕዝቡም መቀጣጫ ሆኑ። 11የቆሬ ልጆች ግን አልሞቱም።
12የስምዖን ነገድ ተወላጆች፦ ነሙኤል፥ ያሚንና፥ ያኪን፥ 13ዛራ፥ ሳኡልና የእነርሱ ተወላጆች ናቸው። 14ከስምዖን ነገድ የጐሣ መሪዎች የተቈጠሩት ኻያ ሁለት ሺህ ሁለት መቶ ነበሩ። 15የጋድ ነገድ ተወላጆች ጽፎን፥ ሐጊ፥ ሹኒ፥ 16ኤስናን፥ ዔሪ፥ 17አሮድ አርኤሊና ተወላጆቻቸው ናቸው። 18ከጋድ ወገኖች የተቈጠሩት ጠቅላላ ቊጥር አርባ ሺህ አምስት መቶ ነበር። 19የይሁዳ ነገድ ተወላጆች፥ ኤርና አውናን በከነዓን ምድር ሞቱ። 20የቀሩት የይሁዳ ልጆች ሴሎም ፋሬስ ዛራና ተወላጆቻቸው ናቸው። 21የፋሬስም ልጆች፥ ኤስሮም፥ ሐሙልና ተወላጆቻቸው ናቸው። 22ከይሁዳ ነገድ የጐሣ መሪዎች የተቈጠሩት ሰባ ስድስት ሺህ አምስት መቶ ነበሩ። 23የይሳኮር ነገድ ተወላጆች ቶላ፥ ፉዋ፥ 24ያሱብ፥ ሺምሮንና ተወላጆቻቸው ናቸው። 25ከይሳኮር ነገድ የጐሣ መሪዎች የተቈጠሩት ሥልሳ አራት ሺህ ሦስት መቶ ነበሩ።
26የዛብሎን ነገድ ተወላጆች ሴሬድ፥ ኤሎን ያሕይኤልና ተወላጆቻቸው ናቸው፥ 27ከዛብሎን ነገድ የጐሣ መሪዎች የተቈጠሩት ሥልሳ ሺህ አምስት መቶ ነበር።
28የዮሴፍ ልጆች በየወገናቸው፥ ምናሴና ኤፍሬም፥
29የምናሴ ነገድ ተወላጆች ማኪር ገለዓድን ወለደ፤
30የገለዓድ ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ኢኤዝር፥ ሔሌቅ፥ 31አስሪኤል፥ ሴኬም።
32ሸሚዳ፥ ኦፌር፥ 33የሔፌር ልጅ ጸሎፍሐድ ከሴቶች በቀር ወንዶች ልጆች አልነበሩትም፤ እነርሱም ማሕላ፥ ኖዓ፥ ሖግላ፥ ሚልካ እና ቲርጻ ተብለው የሚጠሩ ነበሩ፤ 34ከምናሴ ነገድ የጐሣ መሪዎች የተቈጠሩ ኀምሳ ሁለት ሺህ ሰባት መቶ ነበሩ።
35የኤፍሬም ነገድ ተወላጆች ሱቱላ፥ ቤኬር፥ ታሖን፥
36የሱቱላ ልጅ፦ ዔራንና የእነርሱ ተወላጆች ናቸው።
37እነዚህ የኤፍሬም ወገኖች ናቸው፤ ከእነርሱም የተቈጠሩት ሠላሳ ሁለት ሺህ አምስት መቶ ነበሩ። በየወገናቸው የዮሴፍ ተወላጆች እነዚህ ናቸው። 38የብንያም ነገድ በየትውልዳቸው ቤላ፥ አሽቤል፥ አሒራም።
39ሹፋም፥ ሑፋም፥
40የቤላም ልጆች አርድና ናዕማን ናቸው። ከናዕማናውያን ወገን ናዕማን፥ 41የብንያም ነገድ ተወላጆች እነዚህ ናቸው። ከእነርሱም የተቈጠሩት አርባ አምስት ሺህ ስድስት መቶ ነበሩ።
42የዳን ነገድ ተወላጆች ሰሜዔና፤ ተወላጆቹ፥ 43የሰምዔያውያን ወገኖች ሁሉ ከእነርሱ እንደ ተቈጠሩ ሥልሳ አራት ሺህ አራት መቶ ነበሩ።
44የአሴር ነገድ ተወላጆች ዪምና፥ የሱዋ፥ በሪዓ። 45ከበሪዓ ልጆች፦ ሔቤር፥ መልኪኤል፥ 46አሴርም ሤራሕ የምትባል ሴት ልጅ ነበረችው፤ 47እነዚህ የአሴር ተወላጆች ናቸው፤ ከእነርሱም የተቈጠሩት ኀምሳ ሦስት ሺህ አራት መቶ ነበር።
48የንፍታሌም ነገድ ተወላጆች ያሕጼል፥ ጉኒ 49ዬጽር፥ ሺሌምና የእነርሱ ተወላጆች ናቸው። 50የንፍታሌም ነገድ በየወገናቸው እነዚህ ናቸው፤ ከእነርሱም የተቈጠሩት አርባ አምስት ሺህ አራት መቶ ነበሩ። 51በዚህም ዐይነት ከእስራኤላውያን የተቈጠሩት ስድስት መቶ አንድ ሺህ ሰባት መቶ ሠላሳ ነበሩ።
52እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ 53“ምድሪቱን በስማቸው ምዝገባ መሠረት ለየነገዱ በርስትነት አከፋፍል፤ 54ብዛት ላለው ነገድ ሰፊ መሬት፥ አነስተኛ ቊጥር ለሆነ ነገድ ጠበብ ያለ መሬት ስጥ፤ የርስቱም ክፍፍል በቈጠራ በተገኘው የሕዝብ ብዛት መሠረት ነው። 55ሆኖም ክፍፍሉ የሚደረገው በዕጣ ነው፤ ዕጣውም የሚጣለው በየነገዱ መሠረት ነው። 56ዕጣ የሚጣለውም ከፍተኛ ቊጥርና አነስተኛ ቊጥር ባላቸው ቤተሰቦች መካከል ነው።” #ዘኍ. 34፥13፤ ኢያሱ 14፥1-2። 57ከሌዋውያን ነገድ ተወላጆች፦ ጌርሾን፥ ቀዓት፥ ሜራሪና የእነርሱ ተወላጆች ናቸው። የእነርሱም ዘሮች ሊብኒ፥ ኬብሮን፥ ማሕሊ፥ ሙሴ፥ ቆሬና የእነርሱ ተወላጆች ናቸው። ቀዓትም አሞራምን ወለደ። 58የእነርሱ ዘሮች የሊብናውያን ወገን፥ የኬብሮናውያን ወገን፥ የሞላውያን ወገን፥ የሙሳውያን ወገን፥ የቆሬያውያን ወገን ቀዓትም አምራምን ወለደ። 59ዓሞራም በግብጽ የተወለደችውን የሌዊን ሴት ልጅ ዮኬቤድን አግብቶ ነበር፤ እርስዋም አሮንና ሙሴ የተባሉትን ሁለት ወንዶች ልጆችንና ማርያም የተባለችውን አንዲት ሴት ልጅ ወለደችለት። 60አሮንም ናዳብ፥ አቢሁ፥ አልዓዛርና ኢታማር የተባሉ አራት ወንዶች ልጆች ነበሩት። #ዘኍ. 3፥2። 61ናዳብና አቢሁ ያልተቀደሰ እሳት ለእግዚአብሔር ከማቅረባቸው የተነሣ ተቀሥፈው ሞቱ። #ዘሌ. 10፥1-2፤ ዘኍ. 3፥4። 62ዕድሜአቸው አንድ ወርና ከዚያም በላይ የሆነ የወንዶች ሌዋውያን ጠቅላላ ቊጥር ኻያ ሦስት ሺህ ሆነ፤ እነርሱም ከሌሎቹ እስራኤላውያን ተለይተው ተመዘገቡ፤ ይህም የሆነበት ምክንያት በእስራኤል ምድር ምንም ዐይነት የርስት ድርሻ ስላልተሰጣቸው ነበር።
63ሙሴና አልዓዛር በኢያሪኮ ትይዩ ከዮርዳኖስ ወንዝ አጠገብ ባለው በሞአብ ሜዳ እስራኤላውያንን በቈጠሩበት ጊዜ የመዘገቡአቸው የጐሣ መሪዎች እነዚህ ነበሩ። 64በሲና በረሓ በመጀመሪያው የሕዝብ ቈጠራ ጊዜ ሙሴና አሮን ከመዘገቡአቸው ወንዶች አንድም ተርፎ የቀረ አልነበረም። 65ይህም የሆነው “ሁሉም በምድረ በዳ ይሞታሉ!” ብሎ እግዚአብሔር ተናግሮ ስለ ነበር ነው፤ ስለዚህም ከየፉኔ ልጅ ከካሌብና ከነዌ ልጅ ከኢያሱ በቀር ሁሉም ሞተዋል። #ዘኍ. 14፥26-35።
Currently Selected:
ኦሪት ዘኊልቊ 26: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997