ኦሪት ዘኊልቊ 27
27
የጸሎፍሐድ ሴቶች ልጆች ጥያቄ
1የሔፌር፥ የገለዓድ፥ የማኪር፥ የምናሴ፥ የዮሴፍ ልጅ የሆነው ጸሎፍሐድ፥ ማሕላ፥ ኖዓ፥ ሖግላ፥ ሚልካ እና ቲርጻ ተብለው የሚጠሩ ሴቶች ልጆች ነበሩት። 2እነርሱም በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ሄደው መላው ማኅበርና የሕዝቡ መሪዎች ባሉበት በሙሴና በአልዓዛር ፊት ቆመው እንዲህ አሉ፤ 3“አባታችን አንድ እንኳ ወንድ ልጅ ሳይወልድ በምድረ በዳ ሞተ፤ እርሱ በእግዚአብሔር ላይ ካመፁት ከቆሬ ተከታዮች ጋር ተባባሪ አልነበረም፤ የሞተውም በራሱ ኃጢአት ምክንያት ነው፤ 4ታዲያ፥ ወንድ ልጅ ባለመውለዱ ብቻ የአባታችን ስም ከእስራኤል ተፍቆ መጥፋት ይገባዋልን? ስለዚህ በአባታችን ዘመዶች መካከል ለእኛ የሚገባንን የርስት ድርሻ ስጡን።”
5ሙሴም የእነርሱን አቤቱታ ወደ እግዚአብሔር አቀረበ፤ 6እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፤ 7“የጸሎፍሐድ ሴቶች ልጆች የጠየቁት ትክክል ነገር ነው፤ ስለዚህ በአባታቸው ዘመዶች መካከል ርስት ስጣቸው፤ የአባታቸው ድርሻ ወደ እነርሱ ይተላለፍ፤ #ዘኍ. 36፥2። 8ወንድ ልጅ ሳይወልድ የሚሞት ሰው ቢኖር ሴት ልጁ ንብረቱን መውረስ እንደሚገባት ለእስራኤል ሕዝብ አስታውቅ። 9ሴት ልጅም ከሌለው ወንድሞቹ ንብረቱን ይውረሱ፤ 10ወንድሞችም ከሌሉት የአባቱ ወንድሞች ይውረሱ፤ 11ወንድሞችም ሆኑ አጐቶች ከሌሉት የቅርብ ዘመዱ የሆነ ሰው ንብረቱን ወርሶ ሊጠቀምበት ይችላል፤ እኔ እግዚአብሔር ባዘዝኩህ መሠረት የእስራኤል ሕዝብ ይህን ሕግና ሥርዓት ቋሚ መመሪያ አድርገው ይጠብቁት።”
ኢያሱ በሙሴ ምትክ መመረጡ
(ዘዳ. 31፥1-8)
12እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ወደ ዐባሪም ተራራ ወጥተህ ለእስራኤላውያን ልሰጣቸው ያቀድኩትን ምድር ሁሉ እይ፤ 13እርሱንም ካየህ በኋላ ወንድምህ አሮን እንደ ሞተ አንተም ትሞታለህ፤ 14ሁለታችሁም በጺን ምድረ በዳ በትእዛዜ ላይ ዐምፃችሁ ነበር፤ መላው ማኅበር በመሪባ ውሃ ዘንድ ሳሉ በእኔ ላይ በዐመፁ ጊዜ የተቀደሰውን ኀይሌን በእነርሱ ፊት መግለጥ እምቢ ብላችኋል፤” (መሪባ በጺን ምድረ በዳ በቃዴስ የሚገኝ ምንጭ ነው።) #ዘዳ. 3፥23-27፤ 32፥48-52። 15ሙሴም ወደ ጌታ እንዲህ ሲል ጸለየ፦ 16-17“ለሰው ሁሉ ሕይወትን የምትሰጥ፥ እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፥ ሕዝብህ እረኛ እንደሌለው የበግ መንጋ እንዳይሆን፥ ሕዝብህን የሚመራ አንድ ሰው ምረጥ።” #1ነገ. 22፥17፤ ሕዝ. 34፥5፤ ማቴ. 9፥36፤ ማር. 6፥34።
18እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “በመንፈስ ጠንካራ የሆነውን የነዌን ልጅ ኢያሱን ውሰድና እጆችህን በራሱ ላይ ጫን፤ #ዘፀ. 24፥13። 19በካህኑ በአልዓዛርና በመላው ማኅበር ፊት እንዲቆም አድርገው፤ በእነርሱም ሁሉ ፊት የአንተ ተተኪ መሆኑን አስታውቅ። 20መላው የእስራኤል ማኅበር እርሱን ይታዘዙት ዘንድ የሥልጣንህ ተካፋይ አድርገው። 21ካህኑ አልዓዛር በኡሪም አማካይነት ፈቃዴን የሚያውቅ ስለ ሆነ ኢያሱ በአልዓዛር ይደገፋል፤ በዚህም ዐይነት አልዓዛር ኢያሱንና መላውን የእስራኤል ማኅበር በተግባር አፈጻጸማቸው ሁሉ ይመራቸዋል።” #ዘፀ. 28፥30፤ 1ሳሙ. 14፥41፤ 28፥6።
22ሙሴም እግዚአብሔር እንዳዘዘው አደረገ፤ ኢያሱንም ወስዶ በካህኑ በአልዓዛርና በመላው ማኅበር ፊት እንዲቆም አደረገው፤ 23እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት ሙሴ እጆቹን በኢያሱ ራስ ላይ ጭኖ ከዚያ በኋላ የእርሱ ተተኪ መሆኑን በግልጥ አስታወቀ። #ዘዳ. 31፥23።
Currently Selected:
ኦሪት ዘኊልቊ 27: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997