የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ወደ ፊልሞና መግቢያ

መግቢያ
ፊልሞና የታወቀ ክርስቲያን ነበር፤ የቆላስይስ ቤተ ክርስቲያን አባል እንደ ነበረ ይገመታል። ፊልሞና ኦኔሲሞስ የሚባል ባሪያ ነበረው፤ ይህም አገልጋይ ከጌታው ኰብልሎ በሄደበት ጊዜ በእስር ቤት ከነበረው ከጳውሎስ ጋር ተገናኘ፤ በጳውሎስም አማካይነት ኦኔሲሞስ የክርስትናን እምነት ተቀበለ፤ ጳውሎስ ወደ ፊልሞና የጻፈው መልእክት ፊልሞና ተመልሶ ወደ እርሱ በመምጣት ላይ ካለው አገልጋዩ ጋር እንዲታረቅ የሚያሳስብ ነበር፤ በተጨማሪም አሁን ኦኔሲሞስ ክርስቲያን ስለ ሆነ ከእንግዲህ ወዲህ እንደ ክርስቲያን ወንድም እንዲቀበለው እንጂ እንደ ባሪያ እንዳይቈጥረው ይነግረዋል።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
መግቢያ 1-3
የጳውሎስ ምስጋና ለፊልሞና 4-7
ጳውሎስ ስለ ኦኔሲሞስ ያቀረበው ጥብቅ ልመና 8-22
ማጠቃለያ 23-25

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ