ወደ ቲቶ 3
3
ክርስቲያናዊ ተግባር
1ሰዎች ሁሉ ለገዢዎችና ለባለሥልጣኖች በትሕትና እንዲታዘዙ፥ መልካም ሥራን ሁሉ ለመሥራት ዝግጁዎች እንዲሆኑ፥ 2በማንም ላይ ክፉ ነገር እንዳይናገሩ አሳስባቸው፤ ይልቅስ ከሰው ጋር የማይጣሉና ገሮች፥ ፍጹም ትሕትናን ለሰው ሁሉ የሚያሳዩ ይሁኑ፤ 3እኛም ከዚህ በፊት ሞኞች፥ የማንታዘዝ እምቢተኞች፥ መንገዳችንን የሳትን ተላላዎች፥ ለልዩ ልዩ ፍትወትና ሥጋዊ ደስታ የተገዛን፥ በተንኰልና በምቀኝነት የምንኖር፥ የተጠላንና እርስ በርሳችንም የምንጣላ ነበርን። 4ነገር ግን የመድኀኒታችን የእግዚአብሔር ደግነትና ፍቅር የተመላ ርኅራኄ በተገለጠ ጊዜ፥ 5እኛ በሠራነው የጽድቅ ሥራ ሳይሆን ራሱ በምሕረቱ አዳነን፤ ያዳነንም በአዲስ ልደት መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት በተገኘው መታደስ ነው። 6እግዚአብሔር በለጋሥነቱ በአዳኛችን በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት መንፈሱን በብዛት አፈሰሰልን። 7ይህንንም ያደረገው በጸጋው ጸድቀን በተስፋ የምንጠባበቀውን የዘለዓለምን ሕይወት እንድንወርስ ነው። 8ይህ የታመነ አባባል ነው። በእግዚአብሔር ያመኑ ሰዎች ለመልካም ሥራ እንዲተጉ ይህን ነገር ሁሉ በጥብቅ እንድታስገነዝብ እፈልጋለሁ፤ ይህም ነገር መልካምና ለእያንዳንዱ ሰው ጠቃሚ ነው። 9ነገር ግን ከሞኞች ክርክር፥ ከትውልዶች ቈጠራ፥ ከጭቅጭቅ፥ በሕግ ምክንያት ከሚነሣው ጠብ ራቅ፤ እነዚህ ነገሮች ጥቅም የሌላቸውና ዋጋቢሶች ናቸው። 10መለያየትን የሚያመጣውን ሰው አንድ ጊዜ ወይም ሁለት ጊዜ ከመከርከው በኋላ ከእርሱ ራቅ። 11እንዲህ ያለው ሰው ጠማማና ኃጢአተኛ ነው፤ እርሱ በራሱ ላይ የፈረደ መሆኑን ዕወቅ።
የመጨረሻ ምክር
12አርጤማስን ወይም ቲኪቆስን ወደ አንተ በምልክበት ጊዜ አንተ ወደ ኒቆጵልዮን ወደ እኔ ለመምጣት ፍጠን፤ እኔ ክረምቱን እዚያ ለማሳለፍ ወስኜአለሁ። #ሐ.ሥ. 20፥4፤ ኤፌ. 6፥21-22፤ ቆላ. 4፥7-8፤ 2ጢሞ. 4፥12። 13ሕግ ዐዋቂው ዜናስና አጵሎስ ጒዞአቸውን እንዲጀምሩ አድርጋቸው፤ በሚያስፈልጋቸውም ነገር ሁሉ ርዳቸው። #ሐ.ሥ. 18፥24፤ 1ቆሮ. 16፥12። 14የእኛም ሰዎች ደግሞ ያለ ፍሬ እንዳይቀሩና የኑሮን ችግር ማቃለል እንዲችሉ መልካም ሥራን መሥራት ይማሩ።
15ከእኔ ጋር ያሉት ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡልሃል፤ በእምነት ከእኛ ጋር ተካፋይ ለሆኑ ወዳጆቻችን ሁሉ ሰላምታ አቅርብልን።
የእግዚአብሔር ጸጋ ከሁላችሁም ጋር ይሁን።
Currently Selected:
ወደ ቲቶ 3: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997