መጽሐፈ መዝሙር 12
12
ርዳታ ለማግኘት የቀረበ ጸሎት
1እግዚአብሔር ሆይ! አንድም ታማኝ ሰው ስላልቀረ እባክህ እርዳን፤
ታማኞች ሰዎች በሰው ዘር መካከል ጠፍተዋል።
2አንዱ ለአንዱ ውሸትን ይናገራል፤
በሚያቈላምጥ አንደበት የሚናገሩትም
በሁለት ልብ ነው።
3እግዚአብሔር ሆይ! የሚያቈላምጡ ከንፈሮችንና
የሚመኩ አንደበቶችን ዝጋ።
4እነርሱ፦ “በመናገራችን የፈለግነውን እናገኛለን፤
እንደ ፈቀድን እንናገራለን፤
ሊከለክለን የሚችል ማን ነው?” ይላሉ።
5እግዚአብሔር ግን
“ችግረኞች ተጨቊነዋል፤
ስደተኞች በመከራ ብዛት ይቃትታሉ፤
ስለዚህ እነርሱ የሚፈልጉትን ደኅንነት ለመስጠት እነሣለሁ” ይላል።
6የእግዚአብሔር የተስፋ ቃሎች የታመኑ ናቸው፤
በእሳት ምድጃ ሰባት ጊዜ እንደ ነጠረ ብር የጠሩ ናቸው።
7እግዚአብሔር ሆይ!
አንተ ሁልጊዜ ጠብቀን፤
ክፉ ከሆኑት ከዚህ ዘመን ሰዎች አድነን።
8ክፉ ነገር በሰዎች ዘንድ በሚመሰገንበት ጊዜ
ክፉ ሰዎች በኩራት ይመላለሱበታል።
Currently Selected:
መጽሐፈ መዝሙር 12: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997
መጽሐፈ መዝሙር 12
12
ርዳታ ለማግኘት የቀረበ ጸሎት
1እግዚአብሔር ሆይ! አንድም ታማኝ ሰው ስላልቀረ እባክህ እርዳን፤
ታማኞች ሰዎች በሰው ዘር መካከል ጠፍተዋል።
2አንዱ ለአንዱ ውሸትን ይናገራል፤
በሚያቈላምጥ አንደበት የሚናገሩትም
በሁለት ልብ ነው።
3እግዚአብሔር ሆይ! የሚያቈላምጡ ከንፈሮችንና
የሚመኩ አንደበቶችን ዝጋ።
4እነርሱ፦ “በመናገራችን የፈለግነውን እናገኛለን፤
እንደ ፈቀድን እንናገራለን፤
ሊከለክለን የሚችል ማን ነው?” ይላሉ።
5እግዚአብሔር ግን
“ችግረኞች ተጨቊነዋል፤
ስደተኞች በመከራ ብዛት ይቃትታሉ፤
ስለዚህ እነርሱ የሚፈልጉትን ደኅንነት ለመስጠት እነሣለሁ” ይላል።
6የእግዚአብሔር የተስፋ ቃሎች የታመኑ ናቸው፤
በእሳት ምድጃ ሰባት ጊዜ እንደ ነጠረ ብር የጠሩ ናቸው።
7እግዚአብሔር ሆይ!
አንተ ሁልጊዜ ጠብቀን፤
ክፉ ከሆኑት ከዚህ ዘመን ሰዎች አድነን።
8ክፉ ነገር በሰዎች ዘንድ በሚመሰገንበት ጊዜ
ክፉ ሰዎች በኩራት ይመላለሱበታል።
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997