የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ መዝሙር 149

149
የምስጋና መዝሙር
1እግዚአብሔርን አመስግኑ!
ለእግዚአብሔር አዲስ መዝሙር ዘምሩ!
በምእመናን ጉባኤ አመስግኑት!
2የእስራኤል ሕዝቦች በፈጣሪያችሁ ደስ ይበላቸው!
የጽዮን ሕዝቦችም በንጉሣችሁ ሐሤት ያድርጉ!
3በማሸብሸብ ስሙን ያመስግኑት፤
ከበሮ እየመቱና በገና እየደረደሩ ያመስግኑት።
4እግዚአብሔር በሕዝቡ ደስ ይለዋል፤
ድል በማቀዳጀት ትሑታንን ያከብራቸዋል።
5የእግዚአብሔር ሕዝቦች በድል አድራጊነታቸው
ደስ ይበላቸው፤
ሌሊቱን በሙሉ በደስታ ይዘምሩ።
6ስለ ታም ሰይፍ በእጆቻቸው ይዘው
እልል እያሉ እግዚአብሔርን በከፍተኛ ድምፅ ያመስግኑት።
7እንደዚህ ቢያደርጉ
መንግሥታትን ለማሸነፍ፥
አሕዛብንም ለመቅጣት፥
8ንጉሦቻቸውን በሰንሰለት ለመያዝ፥
መኳንንቶቻቸውን በእግር ብረት ለማሰር፥
9እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ የደነገገውን በመፈጸም
የእግዚአብሔር ሕዝቦች ድልን ይጐናጸፋሉ።
እግዚአብሔር ይመስገን።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ