መጽሐፈ መዝሙር 30
30
የምስጋና ጸሎት
1አምላክ ሆይ! ስላዳንከኝና ጠላቶቼ በእኔ ላይ እንዲደሰቱ
ስላላደረግህ እጅግ አመሰግንሃለሁ።
2እግዚአብሔር አምላክ ሆይ!
እንድትረዳኝ ወደ አንተ ተጣራሁ፤
አንተም ፈወስከኝ።
3እግዚአብሔር ሆይ! ነፍሴን ከሲኦል አወጣሃት፤
ወደ ጥልቁም ከመውረድ ሕይወቴን ጠበቅኸው።
4ለእርሱ ታማኞች አገልጋዮች የሆናችሁ ሁሉ
እግዚአብሔርን በዝማሬ አመስግኑት! ለቅዱስ ስሙም ምስጋና አቅርቡለት!
5እርሱ የሚቈጣው ለጥቂት ጊዜ ነው፤
ቸርነቱ ግን ለዘለዓለም ነው፤
ሌሊት ሲለቀስ ዐድሮ
በማለዳ ደስታ ይሆናል።
6ዋስትና እንዳለኝ ስላወቅሁ
“ከቶ አልሸነፍም” አልኩ።
7እግዚአብሔር ሆይ! ሞገስን በሰጠኸኝ ጊዜ እንደማይነቃንቅ
ተራራ አበረታኸኝ፤
ፊትህን በሰወርክ ጊዜ ግን ተስፋ ቈረጥኩ።
8እግዚአብሔር ሆይ! አንተን ጠራሁህ፤
ምሕረትንም ለመንኩህ።
9እኔ ወደ መቃብር ብወርድ ምን ይጠቅምሃል?
ወደ ዐፈርነት ከተለወጥሁ በኋላ እንዴት ላመሰግንህ እችላለሁ?
ታማኝነትህንስ እንዴት መናገር ይቻለኛል?
10እግዚአብሔር ሆይ! ስማኝ፤ ማረኝም፤
እግዚአብሔር ሆይ! እርዳኝ።
11አንተ ሐዘኔን ወደ ደስታ ለወጥክልኝ፤
ትካዜዬን ከእኔ አስወገድክልኝ፤
የማቅ ልብሴን አውልቀህ ደስታን አለበስከኝ።
12ስለዚህ ዝም አልልም፤
ለአንተ የምስጋና መዝሙር አቀርባለሁ፤
እግዚአብሔር ሆይ! አንተ አምላኬ ነህ፤
ስለዚህ ለዘለዓለም አመሰግንሃለሁ።
Currently Selected:
መጽሐፈ መዝሙር 30: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997
መጽሐፈ መዝሙር 30
30
የምስጋና ጸሎት
1አምላክ ሆይ! ስላዳንከኝና ጠላቶቼ በእኔ ላይ እንዲደሰቱ
ስላላደረግህ እጅግ አመሰግንሃለሁ።
2እግዚአብሔር አምላክ ሆይ!
እንድትረዳኝ ወደ አንተ ተጣራሁ፤
አንተም ፈወስከኝ።
3እግዚአብሔር ሆይ! ነፍሴን ከሲኦል አወጣሃት፤
ወደ ጥልቁም ከመውረድ ሕይወቴን ጠበቅኸው።
4ለእርሱ ታማኞች አገልጋዮች የሆናችሁ ሁሉ
እግዚአብሔርን በዝማሬ አመስግኑት! ለቅዱስ ስሙም ምስጋና አቅርቡለት!
5እርሱ የሚቈጣው ለጥቂት ጊዜ ነው፤
ቸርነቱ ግን ለዘለዓለም ነው፤
ሌሊት ሲለቀስ ዐድሮ
በማለዳ ደስታ ይሆናል።
6ዋስትና እንዳለኝ ስላወቅሁ
“ከቶ አልሸነፍም” አልኩ።
7እግዚአብሔር ሆይ! ሞገስን በሰጠኸኝ ጊዜ እንደማይነቃንቅ
ተራራ አበረታኸኝ፤
ፊትህን በሰወርክ ጊዜ ግን ተስፋ ቈረጥኩ።
8እግዚአብሔር ሆይ! አንተን ጠራሁህ፤
ምሕረትንም ለመንኩህ።
9እኔ ወደ መቃብር ብወርድ ምን ይጠቅምሃል?
ወደ ዐፈርነት ከተለወጥሁ በኋላ እንዴት ላመሰግንህ እችላለሁ?
ታማኝነትህንስ እንዴት መናገር ይቻለኛል?
10እግዚአብሔር ሆይ! ስማኝ፤ ማረኝም፤
እግዚአብሔር ሆይ! እርዳኝ።
11አንተ ሐዘኔን ወደ ደስታ ለወጥክልኝ፤
ትካዜዬን ከእኔ አስወገድክልኝ፤
የማቅ ልብሴን አውልቀህ ደስታን አለበስከኝ።
12ስለዚህ ዝም አልልም፤
ለአንተ የምስጋና መዝሙር አቀርባለሁ፤
እግዚአብሔር ሆይ! አንተ አምላኬ ነህ፤
ስለዚህ ለዘለዓለም አመሰግንሃለሁ።
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997