መጽሐፈ መዝሙር 32
32
ኃጢአትን ተናዝዞ ይቅርታ መቀበል
1ኃጢአታቸው ይቅር የተባለላቸውና
በደላቸውም የተሰረየላቸው ሰዎች
የተባረኩ ናቸው።
2እግዚአብሔር ኃጢአቱን የማይቈጥርበት
ከሽንገላም የራቀ ሰው የተባረከ ነው። #ሮም 4፥7-8።
3ኃጢአቴን ሳልናዘዝ በቀረሁ ጊዜ
ቀኑን ሙሉ በመቃተቴ መላ ሰውነቴ ደከመ።
4ቀንና ሌሊት በብርቱ ቀጣኸኝ፤
ርጥበት ያለው ነገር በበጋ ሙቀት እንደሚደርቅ
ጒልበቴ በፍጹም አለቀ።
5በዚያን ጊዜ ኃጢአቴን ለአንተ ተናዘዝኩ፤
በደሌንም ከአንተ አልሰወርኩም፤
ኃጢአቴን ሁሉ ለአንተ ለመናዘዝ ወሰንኩ፤
አንተም ኃጢአቴን ሁሉ ይቅር አልክልኝ።
6ስለዚህ በጭንቀት ሰዓት እያንዳንዱ ለአንተ ታማኝ ሰው ወደ አንተ ይጸልይ፤
ብርቱ የመከራ ጐርፍ በሚመጣበት ጊዜ እርሱን አይነካውም።
7አንተ መሸሸጊያዬ ነህ፤
ከመከራ ትጠብቀኛለህ፤
ስላዳንከኝ በከፍተኛ ድምፅ በደስታ እዘምራለሁ።
8እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፦ “አስተምርሃለሁ፤
የምትሄድበትንም መንገድ አሳይሃለሁ፤
ምክር እሰጥሃለሁ፤ እጠብቅሃለሁ።”
9እንዲገቱ ለማድረግ
በልባብና በልጓም እንደሚመሩት
እንደ ፈረስና እንደ በቅሎ የማይገባችሁ አትሁኑ።
እንደዚያ ካላደረጋችሁ ፈረስና በቅሎ ወደ እናንተ አይቀርቡም።
10የኃጢአተኞች መከራ ብዙ ነው።
በእግዚአብሔር የሚታመኑትን ግን በዘለዓለማዊ ፍቅሩ ይሸፍናቸዋል።
11ጻድቃን ሆይ! በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፤
ሐሴትም አድርጉ፤
ልበ ቅኖች ሆይ! እልል በሉ!
Currently Selected:
መጽሐፈ መዝሙር 32: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997
መጽሐፈ መዝሙር 32
32
ኃጢአትን ተናዝዞ ይቅርታ መቀበል
1ኃጢአታቸው ይቅር የተባለላቸውና
በደላቸውም የተሰረየላቸው ሰዎች
የተባረኩ ናቸው።
2እግዚአብሔር ኃጢአቱን የማይቈጥርበት
ከሽንገላም የራቀ ሰው የተባረከ ነው። #ሮም 4፥7-8።
3ኃጢአቴን ሳልናዘዝ በቀረሁ ጊዜ
ቀኑን ሙሉ በመቃተቴ መላ ሰውነቴ ደከመ።
4ቀንና ሌሊት በብርቱ ቀጣኸኝ፤
ርጥበት ያለው ነገር በበጋ ሙቀት እንደሚደርቅ
ጒልበቴ በፍጹም አለቀ።
5በዚያን ጊዜ ኃጢአቴን ለአንተ ተናዘዝኩ፤
በደሌንም ከአንተ አልሰወርኩም፤
ኃጢአቴን ሁሉ ለአንተ ለመናዘዝ ወሰንኩ፤
አንተም ኃጢአቴን ሁሉ ይቅር አልክልኝ።
6ስለዚህ በጭንቀት ሰዓት እያንዳንዱ ለአንተ ታማኝ ሰው ወደ አንተ ይጸልይ፤
ብርቱ የመከራ ጐርፍ በሚመጣበት ጊዜ እርሱን አይነካውም።
7አንተ መሸሸጊያዬ ነህ፤
ከመከራ ትጠብቀኛለህ፤
ስላዳንከኝ በከፍተኛ ድምፅ በደስታ እዘምራለሁ።
8እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፦ “አስተምርሃለሁ፤
የምትሄድበትንም መንገድ አሳይሃለሁ፤
ምክር እሰጥሃለሁ፤ እጠብቅሃለሁ።”
9እንዲገቱ ለማድረግ
በልባብና በልጓም እንደሚመሩት
እንደ ፈረስና እንደ በቅሎ የማይገባችሁ አትሁኑ።
እንደዚያ ካላደረጋችሁ ፈረስና በቅሎ ወደ እናንተ አይቀርቡም።
10የኃጢአተኞች መከራ ብዙ ነው።
በእግዚአብሔር የሚታመኑትን ግን በዘለዓለማዊ ፍቅሩ ይሸፍናቸዋል።
11ጻድቃን ሆይ! በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፤
ሐሴትም አድርጉ፤
ልበ ቅኖች ሆይ! እልል በሉ!
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997