መጽሐፈ መዝሙር 41
41
የሕመም ጊዜ ጸሎት
1ድኾችን የሚረዱ የተባረኩ ናቸው፤
እነርሱም በተቸገሩ ጊዜ እግዚአብሔር ይረዳቸዋል።
2እግዚአብሔር ይጠብቃቸዋል፤
በሕይወትም ያኖራቸዋል፤
በምድር ላይ ይባርካቸዋል፤
ለጠላቶቻቸውም አሳልፎ አይሰጣቸውም።
3ታመውም በተኙበት አልጋ ላይ እግዚአብሔር ይረዳቸዋል፤
ጤንነታቸውንም ይመልስላቸዋል።
4እኔም “እግዚአብሔር ሆይ!
አንተን ስለ በደልኩ ምሕረትን አድርግልኝ፤
ከሕመም ፈውሰኝ” አልኩ።
5ጠላቶቼ ብዙ ክፉ ነገር በእኔ ላይ በመናገር
“መቼ ይሞታል? መቼስ ስሙ ተረስቶ ይቀራል?” ይላሉ።
6እኔን ለመጐብኘት የሚመጡት ከልባቸው አይደለም፤
በእኔ ላይ መጥፎ ወሬ ይሰበስባሉ፤
በየቦታውም እየዞሩ ስሜን ያጠፋሉ።
7የሚጠሉኝ ሁሉ በእኔ ላይ በሹክሹክታ ይናገራሉ፤
ክፉ ነገር እንዲደርስብኝም ያቅዳሉ።
8“ጽኑ ደዌ አድሮበት ለመሞት ተቃርቦአል፤
ከእንግዲህ ወዲህ ከተኛበት አልጋ አይነሣም” ይላሉ።
9እንጀራዬን ከእኔ ጋር አብሮ የበላ
ከልብ የምተማመንበት ወዳጄ እንኳ
በእኔ ላይ በጠላትነት ተነሥቶአል። #ማቴ. 26፥23፤ ማር. 14፥18፤ ሉቃ. 22፥21፤ ዮሐ. 13፥18።
10እግዚአብሔር ሆይ! ማረኝ፤
በጠላቶቼም ላይ ብድሬን እመልስ ዘንድ
ጤንነቴንም መልስልኝ፤
11እኔን ድል በማድረጋቸው እንደ ተደሰቱ አይቀሩም፤
አንተም በእኔ ደስ እንደ ተሰኘህ ዐውቃለሁ።
12ስለ ቅንነቴ እኔን ትረዳኛለህ፤
በፊትህም ለዘለዓለም ታኖረኛለህ።
13ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም
የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን! #መዝ. 106፥48።
አሜን! አሜን!
ክፍል ሁለት
Currently Selected:
መጽሐፈ መዝሙር 41: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997
መጽሐፈ መዝሙር 41
41
የሕመም ጊዜ ጸሎት
1ድኾችን የሚረዱ የተባረኩ ናቸው፤
እነርሱም በተቸገሩ ጊዜ እግዚአብሔር ይረዳቸዋል።
2እግዚአብሔር ይጠብቃቸዋል፤
በሕይወትም ያኖራቸዋል፤
በምድር ላይ ይባርካቸዋል፤
ለጠላቶቻቸውም አሳልፎ አይሰጣቸውም።
3ታመውም በተኙበት አልጋ ላይ እግዚአብሔር ይረዳቸዋል፤
ጤንነታቸውንም ይመልስላቸዋል።
4እኔም “እግዚአብሔር ሆይ!
አንተን ስለ በደልኩ ምሕረትን አድርግልኝ፤
ከሕመም ፈውሰኝ” አልኩ።
5ጠላቶቼ ብዙ ክፉ ነገር በእኔ ላይ በመናገር
“መቼ ይሞታል? መቼስ ስሙ ተረስቶ ይቀራል?” ይላሉ።
6እኔን ለመጐብኘት የሚመጡት ከልባቸው አይደለም፤
በእኔ ላይ መጥፎ ወሬ ይሰበስባሉ፤
በየቦታውም እየዞሩ ስሜን ያጠፋሉ።
7የሚጠሉኝ ሁሉ በእኔ ላይ በሹክሹክታ ይናገራሉ፤
ክፉ ነገር እንዲደርስብኝም ያቅዳሉ።
8“ጽኑ ደዌ አድሮበት ለመሞት ተቃርቦአል፤
ከእንግዲህ ወዲህ ከተኛበት አልጋ አይነሣም” ይላሉ።
9እንጀራዬን ከእኔ ጋር አብሮ የበላ
ከልብ የምተማመንበት ወዳጄ እንኳ
በእኔ ላይ በጠላትነት ተነሥቶአል። #ማቴ. 26፥23፤ ማር. 14፥18፤ ሉቃ. 22፥21፤ ዮሐ. 13፥18።
10እግዚአብሔር ሆይ! ማረኝ፤
በጠላቶቼም ላይ ብድሬን እመልስ ዘንድ
ጤንነቴንም መልስልኝ፤
11እኔን ድል በማድረጋቸው እንደ ተደሰቱ አይቀሩም፤
አንተም በእኔ ደስ እንደ ተሰኘህ ዐውቃለሁ።
12ስለ ቅንነቴ እኔን ትረዳኛለህ፤
በፊትህም ለዘለዓለም ታኖረኛለህ።
13ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም
የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን! #መዝ. 106፥48።
አሜን! አሜን!
ክፍል ሁለት
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997