መጽሐፈ መዝሙር 42
42
የስደት ጊዜ ጸሎት
(መዝ. 42—72)
1አምላክ ሆይ!
ዋላ የምንጭ ውሃ ለማግኘት እንደሚናፍቅ
እኔም አንተን ለማየት እናፍቃለሁ።
2ሕያው አምላክ ሆይ!
ውሃ የመጠማትን ያኽል አንተን እናፍቃለሁ፤
ፊትህን ለማየት ወደ አንተ የምመጣው መቼ ነው?
3ቀንና ሌሊት ስለ ማልቅስ
እንባዬ እንደ ምግብ ሆኖኛል፤
ጠላቶቼ “አምላክህ የት አለ?” እያሉ
ዘወትር ይጠይቁኛል።
4እኔ እፊት እፊት ሆኜ እየመራሁ
ከብዙ ሰዎች ጋር ወደ እግዚአብሔር ቤት እሄድ ነበር፤
በዓል የሚያደርጉት ሰዎችም በመዝሙርና
በእልልታ እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ነበር፤
በዚህ ዐይነት ያለፈውን ጊዜ ሳስታውስ
ልቤ በሐዘን ይሰበራል።
5እኔ ለምን ተስፋ እቈርጣለሁ፤
ለምንስ እጨነቃለሁ።
በእግዚአብሔር እተማመናለሁ።
ስለሚረዳኝም እርሱን አመሰግናለሁ።
6አምላኬ ሆይ! ተስፋ ቈርጬአለሁ
ስለዚህም ከዮርዳኖስና ከሔርሞን ምድር
ከሚዛር ተራራ አስብሃለሁ።
7በፏፏቴህ ድምፅ ጥልቁ ጥልቁን ይጠራል፤
ማዕበልህና ሞገድህ በእኔ ላይ አለፈ።
8እግዚአብሔር ዘለዓለማዊ ፍቅሩን በቀን ይሰጣል፤
በሌሊትም የምስጋና መዝሙር አቀርብለታለሁ፤
ወደ ሕይወቴ አምላክ እጸልያለሁ።
9ለአምላኬ! ለአምባዬ!
“ለምን ረሳኸኝ?
በጠላት ስለተጨቈንኩ ለምን እያዘንኩ ልሂድ?” እለዋለሁ።
10ጠላቶቼ “ሁልጊዜ አምላክህ የት አለ?” ብለው
በሚያላግጡብኝ ጊዜ አጥንቶቼ እንኳ ይታመማሉ።
11እኔ ለምን ተስፋ እቈርጣለሁ?
ለምንስ እጨነቃለሁ።
በእግዚአብሔር እተማመናለሁ
ስለሚረዳኝም እርሱን አመሰግናለሁ።
Currently Selected:
መጽሐፈ መዝሙር 42: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997
መጽሐፈ መዝሙር 42
42
የስደት ጊዜ ጸሎት
(መዝ. 42—72)
1አምላክ ሆይ!
ዋላ የምንጭ ውሃ ለማግኘት እንደሚናፍቅ
እኔም አንተን ለማየት እናፍቃለሁ።
2ሕያው አምላክ ሆይ!
ውሃ የመጠማትን ያኽል አንተን እናፍቃለሁ፤
ፊትህን ለማየት ወደ አንተ የምመጣው መቼ ነው?
3ቀንና ሌሊት ስለ ማልቅስ
እንባዬ እንደ ምግብ ሆኖኛል፤
ጠላቶቼ “አምላክህ የት አለ?” እያሉ
ዘወትር ይጠይቁኛል።
4እኔ እፊት እፊት ሆኜ እየመራሁ
ከብዙ ሰዎች ጋር ወደ እግዚአብሔር ቤት እሄድ ነበር፤
በዓል የሚያደርጉት ሰዎችም በመዝሙርና
በእልልታ እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ነበር፤
በዚህ ዐይነት ያለፈውን ጊዜ ሳስታውስ
ልቤ በሐዘን ይሰበራል።
5እኔ ለምን ተስፋ እቈርጣለሁ፤
ለምንስ እጨነቃለሁ።
በእግዚአብሔር እተማመናለሁ።
ስለሚረዳኝም እርሱን አመሰግናለሁ።
6አምላኬ ሆይ! ተስፋ ቈርጬአለሁ
ስለዚህም ከዮርዳኖስና ከሔርሞን ምድር
ከሚዛር ተራራ አስብሃለሁ።
7በፏፏቴህ ድምፅ ጥልቁ ጥልቁን ይጠራል፤
ማዕበልህና ሞገድህ በእኔ ላይ አለፈ።
8እግዚአብሔር ዘለዓለማዊ ፍቅሩን በቀን ይሰጣል፤
በሌሊትም የምስጋና መዝሙር አቀርብለታለሁ፤
ወደ ሕይወቴ አምላክ እጸልያለሁ።
9ለአምላኬ! ለአምባዬ!
“ለምን ረሳኸኝ?
በጠላት ስለተጨቈንኩ ለምን እያዘንኩ ልሂድ?” እለዋለሁ።
10ጠላቶቼ “ሁልጊዜ አምላክህ የት አለ?” ብለው
በሚያላግጡብኝ ጊዜ አጥንቶቼ እንኳ ይታመማሉ።
11እኔ ለምን ተስፋ እቈርጣለሁ?
ለምንስ እጨነቃለሁ።
በእግዚአብሔር እተማመናለሁ
ስለሚረዳኝም እርሱን አመሰግናለሁ።
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997