መጽሐፈ መዝሙር 59
59
የእግዚአብሔርን ጠባቂነት የሚገልጥ ጸሎት
1አምላክ ሆይ! ከጠላቶቼ አድነኝ፤
በእኔ ላይ ከሚነሡ ሰዎችም ጠብቀኝ። #1ሳሙ. 19፥11።
2ከነዚያ ከክፉ ሰዎች አድነኝ፤
ከነዚያም ነፍሰ ገዳዮች ታደገኝ።
3እንዴት እንደ ሸመቁብኝ ተመልከት!
እግዚአብሔር ሆይ! ምንም በደልና ኃጢአት ሳልሠራ
ዐመፀኞች ሰዎች በእኔ ላይ ያሤራሉ።
4ምንም በደል ሳልሠራ ሊያጠቁኝ ተዘጋጅተዋል፤
ይህን ተመልከትና ተነሥተህ እርዳኝ።
5አንተ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የእስራኤል አምላክ ነህ፤
ሕዝቦችን ለመቅጣት ተነሥ፤
ክፉ ከዳተኞችን ያለ ምሕረት ቅጣቸው።
6እነርሱ በከተማይቱ ውስጥ እንደ ውሻ እያላዘኑ
ሲልከሰከሱ ውለው ወደ ማታ ይመለሳሉ።
7ከአፋቸው የሚወጣውን ተመልከት፤
ምላሳቸው እንደ ተሳለ ሰይፍ ነው፤
ነገር ግን ማንም የሚሰማቸው አይመስላቸውም።
8እግዚአብሔር ሆይ!
አንተ ግን በእነርሱ ላይ ትስቃለህ፤
አሕዛብን ሁሉ ትንቃለህ።
9አምላክ ሆይ! መጠጊያዬ ስለ ሆንክ
በአንተ እተማመናለሁ።
10አምላኬ በዘለዓለማዊ ፍቅሩ በፊቴ ይሄዳል፤
ጌታዬ፥ ጠላቶቼን በንቀት ዐይን እንድመለከታቸው ያደርገኛል።
11መከታችን እግዚአብሔር ሆይ!
ወገኖቼ የአንተን ተበቃይነት እንዳይረሱ፥ አትግደላቸው፤
ነገር ግን በኀይልህ በትናቸው፤ አዋርዳቸውም።
12ከአንደበታቸው ኃጢአት አይጠፋም፤
ንግግራቸው ሁሉ ኃጢአት የሞላበት ነው፤
እነርሱ ስለሚራገሙና ስለሚዋሹ
በትዕቢታቸው ይያዙ!
13በቊጣህ አጥፋቸው፤
ፈጽመህም ደምስሳቸው፤
በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር እስራኤልን እንደሚያስተዳድርና
ግዛቱም በምድር ሁሉ እንደ ተንሰራፋ፥
ሰው ሁሉ ያውቃል።
14ጠላቶቼ በከተማይቱ ውስጥ
እንደ ውሻ እያላዘኑ ሲልከሰከሱ ውለው፥
ወደ ማታ ይመለሳሉ።
15እነርሱ ምግብ ለማግኘት እንደሚቅበዘበዙና
በቂ ምግብ ካላገኙም እንደሚያላዝኑ ውሾች ናቸው።
16በመከራዬ ቀን መጠጊያዬና ምሽጌ ስለ ሆንክ
ስለ ኀያልነትህ ክብርና ስለ ዘለዓለማዊ ፍቅርህ
ዘወትር በማለዳ እዘምራለሁ።
17አምላክ ሆይ! አንተ ብርታቴ ነህ፤
አንተ መጠጊያዬ ነህ፤ ዘለዓለማዊ ፍቅርህንም ታሳየኛለህ፤
ስለዚህ የምስጋና መዝሙር አቀርብልሃለሁ።
Currently Selected:
መጽሐፈ መዝሙር 59: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997
መጽሐፈ መዝሙር 59
59
የእግዚአብሔርን ጠባቂነት የሚገልጥ ጸሎት
1አምላክ ሆይ! ከጠላቶቼ አድነኝ፤
በእኔ ላይ ከሚነሡ ሰዎችም ጠብቀኝ። #1ሳሙ. 19፥11።
2ከነዚያ ከክፉ ሰዎች አድነኝ፤
ከነዚያም ነፍሰ ገዳዮች ታደገኝ።
3እንዴት እንደ ሸመቁብኝ ተመልከት!
እግዚአብሔር ሆይ! ምንም በደልና ኃጢአት ሳልሠራ
ዐመፀኞች ሰዎች በእኔ ላይ ያሤራሉ።
4ምንም በደል ሳልሠራ ሊያጠቁኝ ተዘጋጅተዋል፤
ይህን ተመልከትና ተነሥተህ እርዳኝ።
5አንተ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የእስራኤል አምላክ ነህ፤
ሕዝቦችን ለመቅጣት ተነሥ፤
ክፉ ከዳተኞችን ያለ ምሕረት ቅጣቸው።
6እነርሱ በከተማይቱ ውስጥ እንደ ውሻ እያላዘኑ
ሲልከሰከሱ ውለው ወደ ማታ ይመለሳሉ።
7ከአፋቸው የሚወጣውን ተመልከት፤
ምላሳቸው እንደ ተሳለ ሰይፍ ነው፤
ነገር ግን ማንም የሚሰማቸው አይመስላቸውም።
8እግዚአብሔር ሆይ!
አንተ ግን በእነርሱ ላይ ትስቃለህ፤
አሕዛብን ሁሉ ትንቃለህ።
9አምላክ ሆይ! መጠጊያዬ ስለ ሆንክ
በአንተ እተማመናለሁ።
10አምላኬ በዘለዓለማዊ ፍቅሩ በፊቴ ይሄዳል፤
ጌታዬ፥ ጠላቶቼን በንቀት ዐይን እንድመለከታቸው ያደርገኛል።
11መከታችን እግዚአብሔር ሆይ!
ወገኖቼ የአንተን ተበቃይነት እንዳይረሱ፥ አትግደላቸው፤
ነገር ግን በኀይልህ በትናቸው፤ አዋርዳቸውም።
12ከአንደበታቸው ኃጢአት አይጠፋም፤
ንግግራቸው ሁሉ ኃጢአት የሞላበት ነው፤
እነርሱ ስለሚራገሙና ስለሚዋሹ
በትዕቢታቸው ይያዙ!
13በቊጣህ አጥፋቸው፤
ፈጽመህም ደምስሳቸው፤
በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር እስራኤልን እንደሚያስተዳድርና
ግዛቱም በምድር ሁሉ እንደ ተንሰራፋ፥
ሰው ሁሉ ያውቃል።
14ጠላቶቼ በከተማይቱ ውስጥ
እንደ ውሻ እያላዘኑ ሲልከሰከሱ ውለው፥
ወደ ማታ ይመለሳሉ።
15እነርሱ ምግብ ለማግኘት እንደሚቅበዘበዙና
በቂ ምግብ ካላገኙም እንደሚያላዝኑ ውሾች ናቸው።
16በመከራዬ ቀን መጠጊያዬና ምሽጌ ስለ ሆንክ
ስለ ኀያልነትህ ክብርና ስለ ዘለዓለማዊ ፍቅርህ
ዘወትር በማለዳ እዘምራለሁ።
17አምላክ ሆይ! አንተ ብርታቴ ነህ፤
አንተ መጠጊያዬ ነህ፤ ዘለዓለማዊ ፍቅርህንም ታሳየኛለህ፤
ስለዚህ የምስጋና መዝሙር አቀርብልሃለሁ።
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997