መጽሐፈ መዝሙር 60
60
የእግዚአብሔርን ታዳጊነት የሚገልጥ ጸሎት
1አምላክ ሆይ! እስከ አሁን ጣልከን፤ ሰባበርከን፤
እስከ አሁን ተቈጣኸን፤
አሁን መልሰን።
2ምድርን በማንቀጥቀጥ ሰነጣጠቅኻት፤
ስለ ተሰባበረ ፍርስራሹን ጠግን።
3በሕዝብህ ላይ የችግር ቀን አመጣህ፤
እንድንንገዳገድ ያደረገንን የወይን ጠጅንም ሰጠኸን።
4ከጠላት መሣሪያ ማምለጥ እንዲችሉ፥
የሚፈሩህ አይተው የሚጠነቀቁበትን
ምልክት ሰጠሃቸው።
5የምትወደው ሕዝብህ ከጒዳት እንዲድን
በኀይልህ ታደገን፤ ጸሎታችንን ስማ።
6እግዚአብሔር በመቅደሱ ሆኖ እንዲህ አለ፦
“ድል አድርጌ ሴኬምን እሸነሽናለሁ፤
የሱኮትንም ሸለቆ ለሕዝቤ አከፋፍላለሁ። #60፥6 በመቅደሱ፦ ወይም በቅድስናው።
7ገለዓድና ምናሴ የእኔ ናቸው፤
ኤፍሬም የራሴ መከላከያ ቊር ነው፤
ይሁዳም በትረ መንግሥቴ ነው።
8ሞአብ መታጠቢያዬ ነው፤
ኤዶም የእኔ መሆኑን ለማረጋገጥ ጫማዬን አኖርበታለሁ፤
በፍልስጥኤማውያንም ላይ።”
9ወደተመሸገችው ከተማ ማን ይወስደኛል?
እስከ ኤዶምስ ማን ይመራኛል?
10አምላክ ሆይ! አንተ ጥለኸናል፤
ከሠራዊታችንም ጋር ወደ ጦር ሜዳ መውጣት ትተሃል።
11የሰው ርዳታ ከንቱ ነው።
ስለዚህ ጠላቶቻችንን ድል እንድናደርግ አንተ እርዳን።
12እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ እናሸንፋለን፤
እርሱ ጠላቶቻችንን ያዋርዳቸዋል። #2ሳሙ. 8፥13፤ 1ዜ.መ. 18፥12።
Currently Selected:
መጽሐፈ መዝሙር 60: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997
መጽሐፈ መዝሙር 60
60
የእግዚአብሔርን ታዳጊነት የሚገልጥ ጸሎት
1አምላክ ሆይ! እስከ አሁን ጣልከን፤ ሰባበርከን፤
እስከ አሁን ተቈጣኸን፤
አሁን መልሰን።
2ምድርን በማንቀጥቀጥ ሰነጣጠቅኻት፤
ስለ ተሰባበረ ፍርስራሹን ጠግን።
3በሕዝብህ ላይ የችግር ቀን አመጣህ፤
እንድንንገዳገድ ያደረገንን የወይን ጠጅንም ሰጠኸን።
4ከጠላት መሣሪያ ማምለጥ እንዲችሉ፥
የሚፈሩህ አይተው የሚጠነቀቁበትን
ምልክት ሰጠሃቸው።
5የምትወደው ሕዝብህ ከጒዳት እንዲድን
በኀይልህ ታደገን፤ ጸሎታችንን ስማ።
6እግዚአብሔር በመቅደሱ ሆኖ እንዲህ አለ፦
“ድል አድርጌ ሴኬምን እሸነሽናለሁ፤
የሱኮትንም ሸለቆ ለሕዝቤ አከፋፍላለሁ። #60፥6 በመቅደሱ፦ ወይም በቅድስናው።
7ገለዓድና ምናሴ የእኔ ናቸው፤
ኤፍሬም የራሴ መከላከያ ቊር ነው፤
ይሁዳም በትረ መንግሥቴ ነው።
8ሞአብ መታጠቢያዬ ነው፤
ኤዶም የእኔ መሆኑን ለማረጋገጥ ጫማዬን አኖርበታለሁ፤
በፍልስጥኤማውያንም ላይ።”
9ወደተመሸገችው ከተማ ማን ይወስደኛል?
እስከ ኤዶምስ ማን ይመራኛል?
10አምላክ ሆይ! አንተ ጥለኸናል፤
ከሠራዊታችንም ጋር ወደ ጦር ሜዳ መውጣት ትተሃል።
11የሰው ርዳታ ከንቱ ነው።
ስለዚህ ጠላቶቻችንን ድል እንድናደርግ አንተ እርዳን።
12እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ እናሸንፋለን፤
እርሱ ጠላቶቻችንን ያዋርዳቸዋል። #2ሳሙ. 8፥13፤ 1ዜ.መ. 18፥12።
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997