መጽሐፈ መዝሙር 61
61
የመማጠኛ ጸሎት
1አምላክ ሆይ! ጩኸቴን አድምጥ፤
ጸሎቴንም ስማ።
2ተስፋ ቈርጬ ሳለ
ከሩቅ አገር ወደ አንተ እጮኻለሁ፤
ከእኔ በላይ ወደ አለው
ከፍተኛ አምባ ምራኝ።
3አንተ ጠባቂዬና ከጠላቶቼ የምከለልብህ
ብርቱ መጠጊያዬ ነህ።
4በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በቤትህ እንድኖርና
በጥበቃህ ሥር
መጠለያ እንዳገኝ ፍቀድልኝ።
5አምላክ ሆይ! ስእለቴን ሰማህ፤
አንተን ለሚፈሩ ሰዎች ያዘጋጀኸውን በረከት
ለእኔም ሰጠኸኝ።
6በንጉሡ ዕድሜ ላይ ብዙ ዓመቶች ጨምርለት፤
ለብዙ ዘመንም እንዲኖር አድርገው!
7አምላክ ሆይ! በፊትህ ለዘለዓለም እንዲነግሥ አድርገው፤
በዘለዓለማዊው ፍቅርህና በታማኝነትህ ጠብቀው።
8ለአንተ የተሳልኩትን በየቀኑ በማቅረብ
ዘወትር የምስጋና መዝሙር እዘምርልሃለሁ።
Currently Selected:
መጽሐፈ መዝሙር 61: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997
መጽሐፈ መዝሙር 61
61
የመማጠኛ ጸሎት
1አምላክ ሆይ! ጩኸቴን አድምጥ፤
ጸሎቴንም ስማ።
2ተስፋ ቈርጬ ሳለ
ከሩቅ አገር ወደ አንተ እጮኻለሁ፤
ከእኔ በላይ ወደ አለው
ከፍተኛ አምባ ምራኝ።
3አንተ ጠባቂዬና ከጠላቶቼ የምከለልብህ
ብርቱ መጠጊያዬ ነህ።
4በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በቤትህ እንድኖርና
በጥበቃህ ሥር
መጠለያ እንዳገኝ ፍቀድልኝ።
5አምላክ ሆይ! ስእለቴን ሰማህ፤
አንተን ለሚፈሩ ሰዎች ያዘጋጀኸውን በረከት
ለእኔም ሰጠኸኝ።
6በንጉሡ ዕድሜ ላይ ብዙ ዓመቶች ጨምርለት፤
ለብዙ ዘመንም እንዲኖር አድርገው!
7አምላክ ሆይ! በፊትህ ለዘለዓለም እንዲነግሥ አድርገው፤
በዘለዓለማዊው ፍቅርህና በታማኝነትህ ጠብቀው።
8ለአንተ የተሳልኩትን በየቀኑ በማቅረብ
ዘወትር የምስጋና መዝሙር እዘምርልሃለሁ።
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997