መጽሐፈ መዝሙር 65
65
ክብርና ምስጋና ለእግዚአብሔር ማቅረብ
1አምላክ ሆይ! በጽዮን ሆነን አንተን ማመስገን፤
ለአንተ የተሳልነውንም መስጠት ይገባናል።
2አንተ ጸሎትን ሰሚ ስለ ሆንክ
ሰዎች ሁሉ ወደ አንተ ይመጣሉ።
3ኃጢአት በላያችን በርትቶብን ነበር፤
አንተ ግን በደላችንን ሁሉ ይቅር አልክልን።
4አንተ የመረጥካቸውና በተቀደሰ አደባባይህ
እንዲኖሩ ወደ ራስህ ያቀረብካቸው፥ ደስ ይበላቸው፤
እኛም ከቤትህ በሚገኘው መልካም ነገርና
ከመቅደስህ በሚገኘው በረከት እንረካለን።
5ጸሎታችንን ሰምተህ ድልን ታጐናጽፈናለህ፤
እኛንም ለማዳን ብዙ ድንቅ ነገሮችን ታደርጋለህ፤
ሩቅ ከሆነው ባሕር ማዶ ያሉት ሳይቀሩ
የዓለም ሕዝቦች ሁሉ በአንተ ይታመናሉ።
6በኀይልህ ተራራዎችን አጽንተሃል፤
ብርታትንም ታጥቀሃል።
7ከባሕሩ መናወጥ የተነሣ የሚያስገመግመውን
የማዕበል ድምፅ ጸጥ ታደርጋለህ፤
የሕዝቦችንም ሁከት ዝም ታሰኛለህ።
8ስላደረግሃቸው ተአምራት ዓለም በሙሉ በፍርሃት ይዋጣል፤
በአንተ ድንቅ ሥራ ምክንያት ከምድር ዳርቻ እስከ ምድር ዳርቻ የእልልታ ድምፅ ይሰማል።
9ዝናብን በማዝነብ ምድርን ትጐበኛለህ፤
ፍሬያማ በማድረግ ታበለጽጋታለህ፤
ምንጮችህን በውሃ ትሞላለህ፤
ለምድርም ሰብልን ትሰጣለህ።
ይህንንም የምታደርገው እንዲህ ነው፤
10ለታረሱ ማሳዎች በቂ ዝናብ ትሰጣለህ፤
ወጣ ገባውን ታስተካክላለህ፤
ዐፈሩንም በካፊያ ታለሰልሳለህ፤
ቡቃያዎችም በቅለው እንዲያድጉ ታደርጋለህ።
11በአንተ ቸርነት የሚገኘው መከር እንዴት ብዙ ነው!
አንተ በምትገኝበት ቦታ ሁሉ ብዙ ሰብል አለ።
12የግጦሽ ስፍራዎች በመንጋ የተሞሉ ይሆናሉ፤
ተራራዎችም ደስታን እንደ ልብስ ይለብሳሉ።
13መስኮች የብዙ በጎች መሰማሪያ ይሆናሉ፤
ሸለቆዎች በሰብል ይሸፈናሉ፤
ሁሉም ደስ ብሎአቸው፥ በእልልታ ይዘምራሉ።
Currently Selected:
መጽሐፈ መዝሙር 65: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997
መጽሐፈ መዝሙር 65
65
ክብርና ምስጋና ለእግዚአብሔር ማቅረብ
1አምላክ ሆይ! በጽዮን ሆነን አንተን ማመስገን፤
ለአንተ የተሳልነውንም መስጠት ይገባናል።
2አንተ ጸሎትን ሰሚ ስለ ሆንክ
ሰዎች ሁሉ ወደ አንተ ይመጣሉ።
3ኃጢአት በላያችን በርትቶብን ነበር፤
አንተ ግን በደላችንን ሁሉ ይቅር አልክልን።
4አንተ የመረጥካቸውና በተቀደሰ አደባባይህ
እንዲኖሩ ወደ ራስህ ያቀረብካቸው፥ ደስ ይበላቸው፤
እኛም ከቤትህ በሚገኘው መልካም ነገርና
ከመቅደስህ በሚገኘው በረከት እንረካለን።
5ጸሎታችንን ሰምተህ ድልን ታጐናጽፈናለህ፤
እኛንም ለማዳን ብዙ ድንቅ ነገሮችን ታደርጋለህ፤
ሩቅ ከሆነው ባሕር ማዶ ያሉት ሳይቀሩ
የዓለም ሕዝቦች ሁሉ በአንተ ይታመናሉ።
6በኀይልህ ተራራዎችን አጽንተሃል፤
ብርታትንም ታጥቀሃል።
7ከባሕሩ መናወጥ የተነሣ የሚያስገመግመውን
የማዕበል ድምፅ ጸጥ ታደርጋለህ፤
የሕዝቦችንም ሁከት ዝም ታሰኛለህ።
8ስላደረግሃቸው ተአምራት ዓለም በሙሉ በፍርሃት ይዋጣል፤
በአንተ ድንቅ ሥራ ምክንያት ከምድር ዳርቻ እስከ ምድር ዳርቻ የእልልታ ድምፅ ይሰማል።
9ዝናብን በማዝነብ ምድርን ትጐበኛለህ፤
ፍሬያማ በማድረግ ታበለጽጋታለህ፤
ምንጮችህን በውሃ ትሞላለህ፤
ለምድርም ሰብልን ትሰጣለህ።
ይህንንም የምታደርገው እንዲህ ነው፤
10ለታረሱ ማሳዎች በቂ ዝናብ ትሰጣለህ፤
ወጣ ገባውን ታስተካክላለህ፤
ዐፈሩንም በካፊያ ታለሰልሳለህ፤
ቡቃያዎችም በቅለው እንዲያድጉ ታደርጋለህ።
11በአንተ ቸርነት የሚገኘው መከር እንዴት ብዙ ነው!
አንተ በምትገኝበት ቦታ ሁሉ ብዙ ሰብል አለ።
12የግጦሽ ስፍራዎች በመንጋ የተሞሉ ይሆናሉ፤
ተራራዎችም ደስታን እንደ ልብስ ይለብሳሉ።
13መስኮች የብዙ በጎች መሰማሪያ ይሆናሉ፤
ሸለቆዎች በሰብል ይሸፈናሉ፤
ሁሉም ደስ ብሎአቸው፥ በእልልታ ይዘምራሉ።
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997